Sunday, February 26, 2017

አድዋ የነጻነት ድል



Image may contain: 2 people, people standing and outdoorየካቲት ወር የአፍሪካውያን ወር ይባላል፡፡ ይህን ወር የአፍሪካውያን ወር ያሰኘው ብቸኛ ምክንያት የዓድዋ ድል ነው፡፡ ነጮች አፍሪካውያንን በግፍ በሚረግጡበት፣ በባርነት በሚገዙበት፣ ያሻቸውን ያለከልካይ በሚፈፅሙበት በዚያን ወቅት ” እምቢኝ! ሀገሬን በቅኝ አላስገዛም ” ብሎ በጀግንነት የተነሳ፣ ተነስቶም የቅኝ ገዢዎችን በትር በሀይል መስበር የተቻለበት ወር ይህ የካቲት ወር ነው፡፡
::ኢትዮጵያዊያን የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም በወራሪው የጣሊያን ጦር ላይ ድል የነሱበት ታሪካዊ በዓል በወቅቱ የነበረውን ፍጹም የነጭ የበላይነት አስተሳሰብ በመስበር "የእንችላለን እናሸንፋለን" የሚል መንፈስን ያላበሰ የመላው ጥቁሮች ህዝብ ድል ነው።ኢትዮጵያ ከቅኝ ግዛት ተፅዕኖ ነፃ ሃገር በመሆን ህዝቦቿ የነፃነትን አየር እንዳሻቸው የሚምጉ የአፍሪካ ብሎም የአለም ተምሳሌት ነበረች፡፡ አሁን ግን በወያኔ መራሹ ፀረ ኢትዮጵያ ቡድን ነፃነትን ተነፍጋ ነፃነት አይታ የማታዉቅ ይመስል ነፃነትን አማትራ እያየች የምትገኝ ምስኪን አገር ሁና ትታያለች፡፡

ህዝባችን አገር በቀል በሆኑ አሳማ መሪዎች ሥር ወድቀዉ ተነግሮ ለማያልቅ መከራ ተዳርገዋል፡፡ እነዚህን ሃገር በቀል ፋሽስቶች በአድዋ የታየውን የአንድነትና የድል አድራጊነት መንፈስ ተላብሰን ድባቅ በመምታት ህዝባችን ዳግም ታሪክ ፅፎ በመጭው ትውልድ የሚወደስበትን አሻራ ጥሎ እንደሚያልፍ ጥርጥር የለውም፡ የክተቱ ነጋሪትም የሚጐሰምበት ጊዜ ሩቅ አደለም።

ልዩነቶቻችሁን ሁሉ ወደጎን ገፍታችሁ… ስለሰውነት ክብር፣ ስለሀገር ነፃነትና ሉዓላዊነት፥ ሕይወታችሁን አሳልፋችሁ የሰጣችሁ አባቶቻችንና እናቶቻችን፥ ክብር ለናንተ ይሁን!!!
ኢትዮጵያ በልጆቿ ተጋድሎ በነጻነት ለዘለአለም ትኑር !!

No comments:

Post a Comment