Tuesday, February 28, 2017
ሰሞኑን ከአንዲት የልብ ወዳጄ ጋር ስለ ውስብስቡ የኢትዮጵያ ፖለቲካና - የኢትዮጵያዊ ሕይወት በረጅሙ አወጋን። የወዳጄን ስም አልነግራችሁም። ለጊዜው አያስፈልግም ብላለች። እናላችሁ፦ በወጋችን መካከል - ቆም ብዬ እንዳስብ የሚያደርግ አንድ ጥያቄ ወርወር አደረገች። ጥያቄው ምን መሰላችሁ? “ኢትዮጵያውያንን በጋራ - “አሁን ገና በዐይኔ መጣህ” የሚያስብላቸው እሴት የትኛው ነው?” የሚል ነበር። ትንሽ እንደማሰብ አልኹና፦ “በሉዓላዊነታቸው ላይ ያላቸው . . . ” ብዬ ሐሳቤን ሳልቋጭ . . . . “ምንም እንኳ የTerritorial Integrity ጉዳይ ተስፋ የማይቆረጥበት ጉዳይ ቢኾንም” ብላ - በግራ መጋባት ዝምታ - በስልኩ ውስጥ ለሰከንድ ያህል ጠፋች። ወዲያው፦ “ለመናገር የተሻለ መረጃና ዕድል ያላቸው ሰዎች - ኢትዮጵያ በታሪኳ እስካሁንም ድረስ ባልታደለችው “ሕዝብን የሥልጣን ባለቤት ማድረግ ጉዳይ ላይ” ማተኮር አለባቸው” አለችኝ። ለወዳጄ ከምንም በላይ ያሳሰባት ነገር፤ እናውቅልኻለን የምንለው - የተሻለ ዕድልና መረጃ ያለን ሰዎች - መሬት ላይ ያለው ወጣትና አጠቃላዩ ማኅበረሰብ - ከእኛ ትንታኔ በተለየ የራሱን ዕይታና እውነታ በሚገለጽበትና - በሚረዳበት የመነጽር ስፋትና መጠን - ሐቁ ወደ ፖለቲካ ማዕከሉ እንዲመጣ ማድረግ አለመቻላችን ነው። MaMa - ማማ - በማስረሻ ማሞ ESAT Mama Feb 28 , 2017
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment