30+ ከተሞች በአንድ ላይ ቅዳሜና እሁድ ፌብሯሪ 11 እና 12 2017 ዓ.ም
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ለአንድነትና ለዴሞክራሲ የሚደረገው ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል፣ ይህ ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በመግባቱ ምክንያት ከመቼው ጊዜ ይልቅ የሚያስከፍለው ዋጋ እየጨመረ መጥቷል። በየዕለቱ በርካታ ታጋዮች የወያኔ ዘረኛ አምባገነን ቡድን አስወግዶ፣ ፍትህ በሰፈነበት፣ እኩልነትን ባረጋገጠ የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ለመተካት በሚደረገው ትግል፣ የመጨረሻውን የሕይወት መሰዋትነት ዋጋ እየከፈሉ ይገኛሉ። በዚህ እጅግ አስቸጋሪ፣ ሆኖም ምንም አማራጭ በሌለው ትግል ውስጥ፣ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7፣ የሕዝቡን ትግል በማስተባበርና በመምራት የሚቻለውን ጥረት ሁሉ እያደረገ ይገኛል። በውጭ ሀገር የምንገኝ ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ወገኖች፣ ለትግሉ ልናደርገው ከምንችለው አስተዋጽዖ መሀል፣ ትግሉን በገንዘብ መደገፍ ነው። ይሄንንም አስተዋጽዖ ተግባራዊ ለማድረግ በመላው ዓለም በሚገኙ ከ30 በላይ ከተሞች ውስጥ “እኔ ለነጻነቴ!ዓለም አቀፍ የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ ዝግጅት” በሚል ዝግጅት ተዘጋጅቷል። የዚህ ዝግጅት፣ የከተማ ዝርዝሮች፣ የአድራሻዎች እና መሰል መረጃዎች ከዚህ በታች ቀርቧል።
አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ
No comments:
Post a Comment