Monday, February 27, 2017

ፈረንጁን በካልቾ! ማን?- ፕሮፍ


“ይህች ወሬ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም አንድ ቀን እቤታቸው ለተገኘን ወጣቶች ያጫወቱን ጨዋታ ናት፦
...ኬንያ ናይሮቢ አንዲት መዝናኛ ቤት ተገኝቼ እየተዝናናሁ ነው። ቤቱ እንደ ፓርቲ ቤት ያለ ነው። ባንዱ ጥግ መጠጤን ይዤ፣ የዳንሱ ወለል ላይ ጥንድ ጥንድ ሆነው የሚደንሱ ወጣቶችን አያለሁ።Bilderesultat for ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
በዚህ መሃል የባሕር ኃይል የደንብ ልብስ የለበሱ እንግሊዛዊያን ነጮች ገቡ። አንዱ እንግሊዛዊ ቀጥታ ወደ ዳንስ ወለሉ ሄደና ከወዳጁ ጋር እየደነሰ ያለውን ኬንያዊ በካልቾ መታው። ኬንያዊው ተርበድብዶ የሴት ወዳጁን ጥሎ ገሸሽ አለ። እንግሊዛዊውም ከዛች ኬንያዊት ጋር መደነስ ጀመረ።
በእንግሊዛዊው ድርጊት በጣም ተናደድኩ። ከመቀመጫዬ ተስፈንጥሬ ተነሳሁና ወደ ዳንስ ወለሉ አመራሁ። እኔም እንግሊዛዊውን በካልቾ ጠልዤ ኬንያዊቷን ተቀበልኩ። ጥቂት ካስደነስኳትም በኋላ ለተቀማው ኬንያዊ አስረከብኩ። ይህን ፈፅሜ ወደ መቀመጫዬ ሳመራ እንግሊዛዊው የጠየቀኝ አንድ ጥያቄ ነበር ፦ "ኢትዮጵያዊ ነህ?" የሚል።
~ ~ ~
የዓድዋ ድልን ባሰብኩ ቁጥር ልቤን የሚያሞቀው እውነት፦ቅኝ ተገዥነት ሌላው ጥቁር ሕዝብ ላይ ካሳደረው የስነልቦና መኮስመን እኛ ኢትዮጵያውያንን ነፃ ማድረጉ ነው!ይለናል - ይህችን የፕሮፍን ጨዋታ ያካፈለን በኃይሉ ገብረእግዚአብሔር።
Dereje Habtewold

No comments:

Post a Comment