Thursday, February 9, 2017

ይሄ ሰንደቅ የጥቁር ህዝብ ኩራት ፣የነፃነት ቀንዲሉ የአሸናፊነት ምልክቱ ነው ሲባል ዝም ብሎ አይደለም።


Image may contain: one or more people, people on stage and people standing
ይህችን ውብ ሰንደቅ የትግላቸው ብቻ ሳይሆን የአምልኳቸውም መለያ እስከማድረግ የደረሱ አሉ።
ባህር አቋርጦ መላው ጥቁር ህዝብን ከእንቅልፍ አንቅቶ ከሰው ያላነሰ ፍጥረት መሆኑን እንዲያውቅ ያደረገ የልባምነት መለያ ነው።
ይህ ሰንደቅ ለመብት አታግሎ ብዙዎችን ነፃ ያወጣ አርማ ነው።
ከኢትዮጵያውያን ለመላው ጥቁር ህዝብ የተበረከተ የአሸናፊነት ሽልማት።
ዛሬም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የሚዘምሩለት።
አዎ ለኢትዮጵያዊነት ይዘፍናሉ፣ይገጥማሉ፣ይስላሉ፣ያወራሉ ..!!!
በኢትዮጵያ ፍቅር ተለክፈው በመንፈሷ ተመስጠው በቅድስናዋ ተቀድሰው በእምነቷ ተማምነው ይኖራሉ።
ኢትዮጵያዊነት እንዲህ ነው።ይህ የማይገባህ እነዚህን የካረቢያን ህዝቦችን ሄደህ ጠይቃቸው።
ጊታራቸውን እየመቱ በሬጌ ስልት እየጨፈሩ አንተ ሰምተህ የማታውቀውን ብዙ ብዙ ነገር ይተርኩልሃል....በጥበብ ከሽነው !!!!!! ስለኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን !!!!
Yoseph Yitna

No comments:

Post a Comment