Wednesday, February 22, 2017

እኔ ለነጻነቴ ! የአንድነትና የዲሞክራሲ የትግል ድጋፍና ውይይት በበርገን ከተማ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ዝግጅት፡


Sat -March፡ 4፡ 2017
Time፡ ከ 2 ፡ 00 PM ጀምሮ
የስብሰባውን ቦታ በቅርቡ እናስታውቃለን፡
የክብር እንግዳ ተጋባዥ የንቅናቄው አመራሮች በቅርቡ የምናሳውቅ ይሆናል..
በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ለአንድነትና ለዴሞክርሲ የሚደረገው ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል።Image may contain: one or more people

ይህ ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በመግባቱ ምክንያት ከመቸውም ግዜ ይልቅ የሚያስከፍለው ዋጋ እየጨመረ መጥቷል። በየዕ
ለቱ በርካታ ታጋዮች የወያኔን ዘረኛ አምባገነን ቡድን አስወግዶ ፍትህ በሰፈነበት እኩልነት ያረጋገጠ የዲሞክራሲ ስርዓት ለመተካት በሚደረገው ትግል የመጨረሻውን የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ።
በዚህ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖም ምንም አማራጭ በሌለው ትግል ውስጥ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 የሕዝብን ትግል በማስተባበርና በመምራት የሚቻለውን ጥረት ሁሉ እያደረገ ይገኛል።
በውጭ ሀገር የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን የህዝብ ወገኖች ለትግሉ ልናደርግ የምንችለውን አስተዋጽዖ መሃል ትግሉን በገንዘብ መደገፍ ነው።
ይሄንንም አስተዋጽዖ ተግባራዊ ለማድረግ በከተማችን በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ በመገኘት አገራዊ ግዴታዎን ይወጡ ዘንድ አዘጋጅ ኮሚቴው ሲያስታውቅ በአክብሮት ነው። 
*እኔ ለነጻነቴ ! ዓለም አቀፍ የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ * ዝግጅት
የበርገን አርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ፡
አዘጋጅ ፡ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርጫፍ
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር !

No comments:

Post a Comment