Tuesday, February 28, 2017

ኦስሎ፡ እስታቫገር እና ትሮንደላግ ከተሞችና ዙርያው ለምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን፤ እኔ ለነጻነቴ ! በታላቌ የኖርዌይ ከተማ በሆነችው በርገን ከተማ ይካሄዳል ። Sat -March፡ 4፡ 2017 Time፡ ከ 2 ፡ 00 PM ጀምሮ የስብሰባውን ቦታ በቅርቡ እናስታውቃለን፡ ተጋባዥ እንግዳዶች፦ የአርበኞች ግንቦት 7 የውጭ አመራር አባላት የሆኑት፤ ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም እና አቶ ብዙነህ ጽጌ ክህዝቡ ጋር ይወያያሉ። በአሁኑ ወቅት በሀገራችን ለአንድነትና ለዴሞክርሲ የሚደረገው ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ እየተሸጋገረ ይገኛል። ይህ ትግል ወደ ወሳኝ ምዕራፍ በመግባቱ ምክንያት ከመቸውም ግዜ ይልቅ የሚያስከፍለው ዋጋ እየጨመረ መጥቷል። በየዕለቱ በርካታ ታጋዮች የወያኔን ዘረኛ አምባገነን ቡድን አስወግዶ ፍትህ በሰፈነበት እኩልነት ያረጋገጠ የዲሞክራሲ ስርዓት ለመተካት በሚደረገው ትግል የመጨረሻውን የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ። በዚህ እጅግ አስቸጋሪ ሆኖም ምንም አማራጭ በሌለው ትግል ውስጥ ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 የሕዝብን ትግል በማስተባበርና በመምራት የሚቻለውን ጥረት ሁሉ እያደረገ ይገኛል። በውጭ ሀገር የምንገኝ ኢትዮጵያዊያን የህዝብ ወገኖች ለትግሉ ልናደርግ የምንችለውን አስተዋጽዖ መሃል ትግሉን በገንዘብ መደገፍ ነው። ይሄንንም አስተዋጽዖ ተግባራዊ ለማድረግ በከተማችን በተዘጋጀው ዝግጅት ላይ በመገኘት አገራዊ ግዴታዎን ይወጡ ዘንድ አዘጋጅ ኮሚቴው ሲያስታውቅ በአክብሮት ነው። *እኔ ለነጻነቴ ! ዓለም አቀፍ የአንድነትና የዴሞክራሲ ትግል ድጋፍ * ዝግጅት information ....47 40979331 /47 96815092 አዘጋጅ ፡ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ሰጪ ድርጅት በኖርዌይ የበርገን ቅርጫፍ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር ! AG7 Public Meeting in Bergen - Norway - 4 March 2017

No comments:

Post a Comment