Monday, February 13, 2017

“ወደ ትጥቅ ትግሉ የገባሁት እንደ ኢትዮጵያዊነቴና ለመላው ኢትዮጵያዊ እንጂ እንደ ህውሃት የጠበበ የዘር ፓለቲካ አንግቤ አይደለም” ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ

አባይ ሚዲያ ዜና በዘርይሁን ሹመቴ
http://amharic.abbaymedia.com/%
ባሳለፍነው ቅዳሜና እሁድ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር በቀጥታ በኔት ወርክ በ46 የአለማችን ከተሞች ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ንግግር ማድረጋቸውና ለቀረበላቸው ጥያቄዎችም ምላሽ መስጥታቸው ታወቀ።
ከሊቀመንበሩ በተጨማሪም በበርሃ ለነጻነት የሚታገሉ አርበኞችም የትግሉን መንፈስ ፣ ትግሉን ፍሬያማ ለማድረግ የሚያስፈልገውን ቁርጠኝነትና ርብርቦሽ ከበረሃ በቪዲዮ የተቀረጸ መልክታቸውን ለተሰብሳቢዎች ማስተላለፋቸውንም መገንዘብ ተችሏል ።
ይህ በአይነቱ አዲስና ለየት ያለ ቁጥራቸው የበዛ በተለያዩ የአለም ክፍል የሚገኙ ከተሞችን በኔት ወርክ በቀጥታ በማገናኘት የተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በተሳካ መልኩ እንደተጠናቀቀ አዘጋጆቹ ገልጸዋል።

የንቅናቄው ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተለያዩ ከተሞች ይህንን ህዝባዊ ስብሰባ ከተካፈሉት ኢትዮጵያውያን የቀረበላቸውን ወቅታዊ ጥያቄዎች ረዘም ያለ ሰአት በመውሰድ  ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በስብሰባው የተካፈሉት ኢትዮጵያውያን ከዚህ በፊት እንደዚህ ያለ በቁጥር በዛ ያሉ ከተሞችን በተመሳሳይ ሰአት ያካተተ ስኬታማ ስብሰባ አድርገው እንደማያውቁ አስተያየታቸውን ሲሰጡ ተሰምተዋል።
ወደ ትጥቅ ትግሉ የገባሁት እንደ ኢትዮጵያዊነቴና ለመላው ኢትዮጵያዊ እንጂ እንደ ህውሃት የጠበበ የዘር ፓለቲካ አንግቤ አይደለም በማለት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ታዳሚዎችን በአድናቆት የማረከ ንግግር ሲያደርጉ ተደምጠዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በተጨማሪ አገር የምትገነባው በሆደ ሰፊነት እንጂ በጠባብና በትእቢት አካሄድ እንዳልሆነ በቀጥታ ለሚከታተሉዎቸው ታዳሚዎች አስረድተዋል።
እሳቸው የሚመሩት ድርጅት የዘር ኩታን መሰረት በማድረግ የተዋቀረ እንዳልሆነ የተናገሩት ፕሮፌሰሩ ድርጅቱን ለመቀላቀል ዋንኛውና ድርድር የሌለው መስፈርት የሆነው ኢትዮጵያዊ መሆንና ኢትዮጵያ የሁላችን እንደሆነች መስማማት እንደሆነም አረጋግጠዋል።
የድርጅቱ በተለያዩ የስራ ሃላፊነት የሚገኙ አመራሮችም ከታዳሚዎች ጋር በመሆን የሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ቀጥታ የጥያቄና መልስ ዝግጅት በተጋባዥነት እንደተከታተሉና ተጨማሪ ማብራሪያዎች እንደሰጡም ሪፓርቶች አመልክተዋል።
በተለያየ አገራትና ከተሞች የታደሙት ተሰብሳቢዎች የወያኔን አገዛዝ ለማስወገድ የተጀመረውን የነጻነት አርበኞች ቁርጠኛና እልህ አስጨራሽ ትግል ለመደገፍ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሞች ማድረጋቸውም ተጠቅሷል።
ሁሉም ከተሞች በእያንዳንዱ ከተማ እየተደረገ ያለውን የጨረታና የገቢ ማሰባሰቢያዎች በቀጥታ የኔት ወርክ ዘዴ በስክሪን እንዲከታተሉ የተደረገው ጥረት ስኬታማ እንደነበረም ተገልጻል ።
የገቢ ማሰባሰቢያ ጨረታው በአንድ መሰብሰቢያ አዳራሽ በተገኙ ታዳሚዎች መካከል ከመሆን አልፎ በበተለያዩ የአለም ከተሞች በሚገኙ ኢትዮጵያውያን መካከል በሚያስደንቅ የፉክክር መንፈስ በስኬት መደረጉ በርግጥም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ድርጅታዊ መዋቅሩ እጅግ ጠንካራ እንደሆነ ያሳየ ነበር።
የድርጅቱ በድስፕሊን መብሰል ፣ በትጋት ለአንድ አላማ በጸናት መቆምና ወጥ የሆነ ድርጅታዊ አሰራር ሂደት ይህንን ከዚህ በፊት ተተግብሮ የማይታወቀውን በተለያዩ የአለም አገራት ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንን በተመሳሳይ ሰአት ያሳተፈ ስኬታማ ህዝባዊ ስብሰባ እንዲደረግ እንዳስቻለው የዝግጅቱ ግብረ ሃይል ገልጸዋል።

No comments:

Post a Comment