#Ethiopiaይህ በዚህ ሰሞን የተፈፀመው ክህደት ዝርዝሩ እንደሚከተለው ነው፡የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ከማህበረሠቡ እና ከእንስሳት ግጦሽ የራቀ የሚያስደምም በአረንጓዴነቱ ለምነቱ እና የዱር እንስሳት መስህብነቱ ልዮ የሆነ ሞቃታማ መጠነ ሰፊ የሆነ በሰሜን ምስራቅ የአማራ ክልል አዲሱ አላጢሽ ብሄራዊ ፓርክ በምዕራብ የደቡብ ሱዳን ዲንደር ብሄራዊ ፓርክ የሚያዋስነው ነው፡፡ ታድያ የእናት ሀገራችንን ስትራቴጅክ መሬቶ እንደ ባእዳን የኢትዮጵያን የህዝብ ዉሳኔ እና እውቅና ወደ ጎን በማለት የሌብነት ብቻ ሳይሆን በቀጣይ የሚኖረውን ህዝብ ሰላምና ህልውና የሚያሳጣ ክህደት ነው የተፈፀመው።
የወያኔን ሰይጣናዊ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት ለማሳካት ብቻ በማሰብ ከሳምንት በፊት የክልሉ መንግስት በድብቅ አጀንዳ አራማጆች በተሰጣቸው አቅጣጫ መሠረት የክልሉ መንግስት በአቅራቢያው ከሚገኙ የዞንና የወረዳ የተወጣጣ ባለሙያዎች አንዲሁም 27 ገደማ የሚሆኑ የክልሉ ልዩ ኃይል ወታደሮችን በመያዝ የማካለል ስራውን ሲያካሂዱ ሰንብተዋል። በባለሙያዎች የGPS መሳርያ በመጠቀም እስከ አላጢሽ ብ.ፓርክ አዋሳኝ እና በደቡብ ምዕራብ ቀጥሎም ወደ ምስራቅ ከአባይ እና አይማ ወንዝ በጣም ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በጋራ መስማማት ካካለሉ በኃላ ወሳኝ ወደ ሆነው የምዕራብ አቅጣጫ ተሸጋግረዋል።
ባካባቢው ውስን የቀበሌ ታጣቂ እና አመራሮች በመታገዝ ወደ ዲንደር ብ.ፓርክ ድረስ ያለውን ለማካለል በሚጓዙበት ወቅት በበላይነት የድብቅ አጀንዳ አራማጆች አንዳንድ ባለሙያወችና አመራሮች ከዚህ በኃላ በቃን በማለት ማንገራገራቸው ታውቋል።
ምክንያቱም በርካታ ኪ.ሜ ይቀረናል እስከ ደ.ሱዳን ዲንደር ብ.ፓርክ ድረስ በግምት በርዝመቱ ብቻ በግምት 85 ኪ.ሜ ይቀረናል ቢባልም ቀሪው ከደ.ሱዳን ጋር የጋራ መግባባት የሚሻ ነው ተብሏል። አይ እንቀጥላለን ከተባለ ከፊታችን የሚገጥመን ችግር ይኖራል ሲባሉ ባለሙያዎችም በቁጭት እና በንዴት እየተቆረቆሩ ቀናቶችን ፈጅተው ተመልሰዋል፡፡
ታድያ ቁም ነገሩ እስካሁን ከተሰጠው ሳይካለል የቀረው መሬትም እንደተለመደው የወያኔ የእድሜ ማራዘሚያ ይሆን ዘንድ መሰጠቱ አይቀሬ ነውና ህዝቡ እየተፈፀመበት ያለውን ክህደት አውቆ እንዲያስቆም ጥሪው ተላልፏል።
ሙሉነህ ዮሃንስ
No comments:
Post a Comment