Friday, February 3, 2017

ሰበር ዜና አባይ ወልዱ ደም በደም እስኪሆኑ ተደበደቡ



የትግራይ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ አባይ ወልዱ የአንፍጫው ደም በደም እስኪሆንና አንድ ዓይኑ እስኪያብጥ ድረስ ከፍተኛ የቦክስ ድብደባ ደረሰበት፡፡Image may contain: 1 person
ድብደባው የደረሰበት በትግራይ ክልል የማር ምርት እያቀረበ የሚገኝበት ብዙ ሚሊዮን ብር ያወጣበት ኢንቨስትመንቱ አደጋ ላይ በመውደቁ እንዲታደግለት ለአባይ ወልዱ ጥያቄ ሲያቀርብ አጥጋቢ ምላሽ አላገኘሁም ባለ ዲያስፖራ ነው።
ዲያስፖራም አቶ አባይ ወልዱ ላይ ከፍተኛ የቦክክስ ጥቃት በሁለት እጆቹ ሲያደርስበት መሬት ላይ ወደቀ፡፡ መሬት ላይ ወድቆም ሊተወው አልቻለም፡፡ በእግሩ ረገጠው፡፡ ይህን ሁሉ ሲሆን ፀሀፊዎቹ በእሪታ ሲያቀልጡትና ዘበኞቹ ወደ ሰማይ ሲተኩሱ ነበር፡፡
እንደ ምንጮቹ ገለጻ በአሁን ሰዓት ዲያስፖራው እስር ላይ ይገኛል፡፡ (የዜናው ምንጪ ወዳጃችን ፍስሀ ደስታ ሀጎስ ነው) 
(ትናንት ማታ 9 የህወኃት ካድሬዎች ባህርዳር ላይ ክፉኛ በትር ቀምሰው ሆስፒታል እንደተኙ መዘገቡ ይታወሳል)
Dereje Habtewold

No comments:

Post a Comment