Monday, February 13, 2017

የኢሳት ሬዲዮ ''በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአባይን ግድብ ለመጠበቅ በመተከል ዞን ወንበራ ወረዳ ዋና ከተማ ደብረዘይት አልፎ ቦጎንዲ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከፍተኛ ቦታ የተተከለው ራዳር በስርዓቱ በተማረረ የፈጥኖ ደራሽ ፌድራል ፖሊስ አባል መመታቱ ተሰምቷል። በራዳሩ የቴክኒክ ባለሙያወች ላይ ያነጣጠረው ጥቃቱ በራዳሩ ሲስተሚክ ክፍሎች ላይ ጉዳት እንዳደረሰ ና አንድ የራዳሩ የአይሲቲ ባለሙያ በፈጥኖ ደራሽ የፌድራል አባል መገደሉ ታውቋል። በአከባቢው ከፈጥኖ ደራሽ ልዩ ሃይል የፌድራል ወታደሮች በተጨማሪ የ12 ክ/ጦር እንዲሁም የ7 ክ/ጦር በተለያዩ ሬጂመንቶች በተለያዩ የግድቡ ክፍሎች ና አከባቢው እንደተሰማሩ ይታወቃል።ራዳሩን የሚጠብቀው የፌድራል ልዩ ሃይል እርስ በርሱ መተማመን አቅቶታል ሁሉም እርስ በርሱ እየተጠባበቀ ይገኛል።ይሄንን ጉዳት ተከትሎ በሁለት በኩል ወታደሮችና የቴክኒካል ባለሙያወች ወደ አካባቢው ለመሄድ ያደረጉት ጥረት በአንደኛው በኩል በሸመቁ ሃይሎች በደረሰባቸው የደፈጣ ውጊያ በመኪናው ላይ ከነበሩት ወታደሮች 4ቱ ተገድለው ጉዟቸው ሳይሳካ ቀርቷል።'' የኢሳት ምንጮች የላኩት ዘገባ ዝርዝሩን ከዛሬው የኢሳት ሬዲዮ መከታተል ይቻላል https://ethsat.com/2017/02/esat-radio-mon-feb-13-2017/

No comments:

Post a Comment