ዛሬ በሐገር ሐብት በተገዛና በተደራጀ ሠራዊት ትጥቅ ሰላማዊና ያልታጠቀን ሕዝብ በመጨፍጨፍ የተለየ ጀብዱ እንደፈፀመ እያቅራራና እየተመጻደቀ ያለው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር ጉጅሌ የመጨረሻው ሰዓት ላይ ሆኖም ዕውነታውን ላለመቀበል ሲውተረተር ይታያል። ነገር ግን ከህውአት ጋር ካለው አረመኔ አግአዚ ሰራዊት እና ጥይት ይልቅ ሕዝብ ጋር ያለው የፍትህና የእውነት መንፈስ አሸናፊ መሆኑ የማያጠራጥር ሐቅ ነው። ምክንያቱም አምባገነኖች እና ፋሺሥቶች ሕዝብን ማሸበር እንጂ ማሸነፍ አይችሉምና!!!
No comments:
Post a Comment