(ዘ-ሐበሻ) የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ዳይሬክተር ጀዋር መሐመድ እና የኢሳት ቴሌቭዥን ዳይሬክተር አበበ ገላው የትግራይ ነጻ አውጪ መንግስት ትናንት በቢሾፍቱ ከ500 በላይ የ እሬቻ በዓልን ለማክበር የወጡ ኦሮሞዎችን እና አማሮችን ከገድሉ በኋላ በሚኒሶታ የኦሮሞ ኮምዩኒቲ አስቸኳይ ስብሰባ ተደርጎ ነበር:: በዚህ ስብሰባ ላይ ሕዝብ ቁጣውን ሲገልጽ ነበር:: ለኢሳት 6ኛ ዓመት በዓል ወደሚኒሶታ መጥቶ የነበረው አበበ ትናንት በኦሮሞ ኮምዩኒቲ አስቸኳይ ስብሰባ ሲጠራ የወገኖቼ ህመም አሞኛል በሚል ተገኝቶ ነበር:: በዚህ ስብሰባ የተለያዩ እንግዶች ንግግር ያደረጉ ሲሆን ጀዋር መሐመድ በኦሮሚኛ አበበ ገላው በአማርኛ ቋንቋ ያደረጓቸውን ታሪካዊ ንግግሮች ከኦሮሞ ሚድያ ኔትወርክ አግኝተን አቅርበንላችኋል:: ትናንት በቢሾፍቱ አንድ ወጣት በእሬቻ በዓል ላይ Down Down TPLF እያለ መፈክር ሲል በቭዲዮ ተለቆ ነበር:: ተመሳሳዩን ተቃውሞ መፈክር አበበ ገላውም በኦሮሞ ኮምዩኒቲ ከሕዝቡ ጋር ብሎታል:: ይመልከቱት::
No comments:
Post a Comment