Thursday, December 31, 2015

ለኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ከኦሮሞ ፌድራላዊ ኮንግረስ ዋና ፀሀፊ አቶ ‪#‎በቀለ_ነጋ‬ የተላለፈ መልዕክት በአሁን ሰዓት በደህንነት ኃይሎች ከቤታቸውም እንዳይወጡ ስልክም እንዳያናግሩና ለሚድያም ቃለ መጠይቅ እንዳይሰጡ ታግደው በመኖሪያ ቤታቸው በቁም እስር ላይ ይገኛሉ። ================



Dear All,
This morning, on my way to work, 4 men in civilian clothes greeted me by my name; identified themselves as ‘police’ and asked me to get in a car parked next to where they stopped me. When I refused, they grabbed me by my arms left and right; forced me into the backseat of their car and started driving. Once the car started moving, they started to hit me: the two guys in my left and right continued to punch me while the one sitting in the front-seat kept touching my face with his gun.
While they were hitting me, they kept saying that they were doing this because I was talking to the media despite their warnings not to do so. After they stopped the beating, they took away my phone at gun point and threatened that I do as they say or they would come for me and my family. They told me that not only mine but also my family’s lives were in danger: “If you step out of your house or talk to any media, you will take responsibility for what may happen to you or your children” (“ከዛሬ ጀምሮ ከቤትህ ብትወጣ ወይ ሚዲያ ብታናግር በአንተም ሆነ በቤተሰቦችህ ላይ ለሚሆነው ነገር ሃላፊነቱ ያንተ ነው”). Before they let me go, they also made it clear that they would resort to killing if I don’t do as they say “we no longer have a place to keep you, if you don’t do as you’re told killing you or paralyzing you is what is left to do.” (“ከእንግዲህ ወዲህ እናንተን የምናስርበት ቦታ የለንም:: ወይ እንገድልሃለን ወይ በመኪና ገጭተን ፓራላይዝ እናደርግሃለን ”)
The Ethiopian government has turned deaf ears to the many peaceful pleas to stop the violent crackdown all over Oromia, and continues to intimidate, arrest and kill citizens with no accountability. More than 4,000 of our party’s members including Bekele Gerba, Dejene Tafa, Addisu Bulala, and Desta Dinka are currently imprisoned incommunicado. It is my hope that the government and those who are silently watching understand that arresting and killing of innocent individuals has never silenced Oromos and will never be a solution to a legitimate demand of millions, and move quickly to rectify this situation. Until then, I, as an individual and member of OFC, will continue to peacefully voice the concerns of the Oromo people, because the peaceful struggle for the freedom and dignity of our people is a cause that millions of Oromos including me are prepared to sacrifice our lives for.
Regards,
Bekele Nega
General Secretary, Oromo Federalist Congress (OFC)

የአገራችን መሬት ሲቆረስ ፣ ህዝባችን ሲጐዳ እጆቻችንን አጣምረን አንቀመጥም !

የአገራችን መሬት ሲቆረስ ፣ ህዝባችን ሲጐዳ እጆቻችንን አጣምረን አንቀመጥም !

የአገራችን መሬት ሲቆረስ ፣ ህዝባችን ሲጐዳ እጆቻችንን አጣምረን አንቀመጥም ! ከቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት አርበኞች ማህበር የቀረበ ወቅታዊ ጥሪ

   እኛ የቀድሞው የኢትዮጵያ የሀገር የመከላከያና የፖሊስ ሠራዊት ዓባላት ለአለፉት 25 ዓመታት በውድ የሃገራችን ሕዝብ ላይ ወያኔ/ህውሃት መራሹ ቡድን የፈፀመውና እየፈፀመ ያለውን ግፍ ፣ በደልና ሰቆቃ እንዲቆም የሁሉም ኢትዮጵያዊ የጋራ ትግል መሆን እንዳለበት እናምናለን ። ይሁን እንጅ የሕዝባችንን ሰቆቃና መከራ፣ ስደትና ዕልቂት ከምንም ባለመቁጠር ይባስ ብለው የሃገሪቷን ልዑላዊነት ለታሪካዊ ጠላቶቻችን አሳልፈው ለመስጠት ሽር ጉድ በማለት ላይ ይገኛሉ። በኢትዮጵያ የረጅም ታሪክ ውስጥ የሃገሪቷን ዳር ድንበር ለባዕድ አሳልፎ ለመስጠት የተደራደረ መንግስት ታይቶም ተሰምቶም አይታወቅም ፣ ሃገሩንና ድንበሩን እንዲጠብቅ አደራ የተሰጠውም ወታደርና የፖሊስ ሠራዊት የዚህ እኩይ ተግባር ተባባሪ የሆነበት ዘመን አልታየም። ከሁሉም በላይ የህውሃት አቀንቃኝ ካድሪዎች በየጊዜው ከሚጎነጉኑት የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የሃገሪቷን ታላላቅ ብሄረሰቦች እርስ በርስ በማናቆር የጥላቻ ዘር በማህከላቸው በመበተን ስልጣኑን ለማራዘም ሁነኛ መሳሪያ አድርጎት ይገኛል። እንደእኛ እምነት ይህ ተንኮል በርግጥም ይህን ግፈኛ ሥርዓት ሃያ አምስት ዓመት እንዲቆይ ረድቶታል ብለን እናምናለን

Wednesday, December 30, 2015

የትላንቱ የአይሱዙ መኪና ረዳት የዛሬው ቢሊየነር አለም ፍጹም የሃብት እንቆቁልሽ በፒስ ለሀገሬ

በኦሮሚያ ክልል በኢሊባቡር ዞን ጉሬ ከተማ ከትግራይ ክልል መጥተው ነዋሪ የነበሩት አቶ ብርሃኔ ወልደጊዪርጊስ ወደ ኦሮሚያ ያቀኑት ከኢህአዴግ በፊት በነበረው ስርአት ነው፡፡
One of the TPLF robbers, billionaire Alem Fitsum
አቶ ብርሃኔም እንደማንኛውም ኢትዪጲያዊ ከኦሮሞ ተወላጆች ጋር እየነገዱ ይኖሩ የነበሩ ግለሰብ ናቸው፡፡ ግለሰቡ አይሱዙ የጭነት መኪና በገዙ ሰአት ንብረታቸውን የሚጠብቅላቸው ገንዘብ የሚቆጣጥርላቸው የቅርብ ሰው በማስፈልጉ የሚስታቸው ወ.ሮ አበባን ወንድም የሆነውን አቶ አለም ፍጹምን ከትግራይ የገጠር ክፍል ወደ ጎሬ ያስመጡታል፣ አቶ አለም ፍጹምም ኢሊባቡር ዞን ጎሬ ከተማ ከመጡ በሁላ በአይሱዚ መኪና ረዳትነት ስራቸውን ቀጠሉ ይህም በ1985 -1989 ባለው ገደማ አካባቢ መሆኑ ነው፡፡ ከዚያ በሁላ አቶ ብርሃነ ወልደጊዪርጊስ ከነ ባለቤታቸው በአሁኔ ጊዜ በህይዎት የሉም።

የኢትዮጵያ ድንበር ኮሚቴ ሊቀመንበር ለኃይለማርያም ደሳለኝ ምላሽ ሰጡ – በኢትዮጵያና ሱዳን ድንበር ማከለል ዙሪያም ተናግረዋል

የኢትዮጵያ ድንበር ለሱዳን ተላልፎ ሊሰጥ ጫፍ ላይ የደረሰ ይመስላል። የአገዛዙ <<ጠቅላይ>> ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ባለፈው ወር ይሄንኑ ተግባራዊ የሚያደርግ ስምምነት ካርቱም ላይ ተገኝተው ፈርመዋል። ሕወሃት በትጥቅ ትግል ወቅት ወደ ስልጣን ለመውጣትና ከወጣም በሁዋላ በዛ በኩል ለስልጣኑ የሚያሰጉት እንዳይመጡ በአገር ጥቅም እስከመደራደር፣ አሳልፎ እስከመስጠት እየሄደ ነው የሚል ጠንካራ ስሞታ ይቀርባል። አቶ ሀይለማሪያም ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን በኩል ይሄን ሩጫቸውን በመቃወም የአገራችንን ድንበር አትስጡ የሚል ወቀሳ ለማጣጣል ከመሞከር አልፈው <<ተቆርሶ የሚሰጥ መሬት የለም>> ከማለት አልፈው ለሱዳን ጥብቅና ቆመዋል። በዚህ ጉዳይ ላይ ኢትዮጵያውያንን በማስተባበር ድንበሩ ተቆርሶ እንዳይሰጥ ላለፉት ዓመታት ድምጹን በየመድረኩ የሚያሰማው የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ምላሽ አለው። ከአቶ አለሙ ያይኔ የኮሚቴው ሊቀመንበር ጋር ቆይታ አድርገናል።http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49559Hiber Radio

Hiber Radio Interview with Chairman of Ethiopia Border Committee

በዛሬዋ የወያኔው ኢትዮጵያ ውስጥ አማራን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን ሰው መሆንን እንጅ በጎሳ ማሰብን አይጠይቅም !!

በወልቃይት ሕብረተሰብ ላይ የሚደረገውን መንግሥታዊ ሽብር፥ የግፍ ግድያ፣ የጅምላ ጭፍጭፋና ዓፈና፥ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የዜጎችን ማፈናቀል የወያኔ ሴራwelkayt
ከዛሬ 25 ዓመታት በፊት በነበረችው ኢትዮጵያ ሐገርነቷ የዜጎቿ የራሳቸው ሐብት ስለነበረች ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ግዛት ተዘዋውረው የሚኖሩባትhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/49563 ፤ሐብትና ንብረት ያፈሩባት፤ ደስታንና መከራን የተጋሩባት፤ ተጋብተውና ተዋልደው ተተኪ ትውልድ የፈጠሩባት፤ ባሕልና ቋንንቋ የተለዋወጡባት፤ በእምነት የተሳሰሩባት በአጠቃላ የሰው ዘር ምንጭ የሆኑት ውህዳን ነገዶችና ጎሳወች ኢትዮጵያዊ ሆነው ለረጅም ዘመናት የኖረባት ታላቅና ታሪካዊት ሐገር ነበረች። በዚህ አይነት የህዝባችንና የሐገራችን የታሪክ ትውስታ ሲዘከር መዘንጋት የማይገባው የአማራው ውህዳዊ ኢትዮጵያዊነት አስተወፅኦ ነው።በዛሬዋ የወያኔው ኢትዮጵያ ውስጥ አማራን ከፈፅሞ ጥፋት ለማዳን ሰው መሆንን እንጅ በጎሳ ማሰብን አይጠይቅም !! ከዛሬ 25 ዓመታት በፊት በነበረችው ኢትዮጵያ ሐገርነቷ የዜጎቿ የራሳቸው ሐብት ስለነበረች ዜጎች በየትኛውም የሀገሪቱ ግዛት ተዘዋውረው የሚኖሩባት ፤ሐብትና ንብረት ያፈሩባት፤ ደስታንና መከራን የተጋሩባት፤ ተጋብተውና ተዋልደው ተተኪ ትውልድ የፈጠሩባት፤ ባሕልና ቋንንቋ የተለዋወጡባት፤ በእምነት የተሳሰሩባት በአጠቃላ የሰው ዘር ምንጭ የሆኑት ውህዳን ነገዶችና ጎሳወች ኢትዮጵያዊ ሆነው ለረጅም ዘመናት የኖረባት ታላቅና ታሪካዊት ሐገር ነበረች። በዚህ አይነት የህዝባችንና የሐገራችን የታሪክ ትውስታ ሲዘከር መዘንጋት የማይገባው የአማራው ውህዳዊ ኢትዮጵያዊነት አስተወፅኦ ነው። የአማራው ውህድ ኢትዮጵያዊነት፤-በመሰረቱ አማራ የተባለው ነገድ በማንኛውም ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቀው ምስራቅ አፍሪካዊት ሐገር ውሰጥ ከመሐል እስከ ዳር (ጠረፍ) ከሌሎች ነገዶች ጋር አብሮ ኢትዮጵያዊ ሆኖ ለረጅም ዘመናት የኖረ የህብረተሰቡ ክፍል ነው። አማራ በምስራቅ የሐገሪቱ ግዛት ከአፋር፣ ከኢሳ፣ ከሱማሌ፤ከሃደሬና ከኦሮሞ ጋር ተቀላቅሎ ምስራቃዊ ግዘትን አስከብሮና ባለቤት ሆኖ ከኖረው ሕዝባችን ውስጥ አነዱ ነው

ጩኸቴን ማን ይስማኝ? እንኳን አትስማ የተባለው የሚሰማው አያዳምጠኝ።


ህወሃት ከጫካ ስትነሳ "አማራ"ን ጠላት ብላ ነበር፡ ውሎ አድሮ ሲታይጸ በአጽንዓት ሲመረመር ግን ጠላትነቷ ከአማራ አልነበረም፡ ከአማርኛ እንጂ።
በርግጥ ስትበላ የበለጠ የሚርባት፤ ስትለብስ የበለጠ የሚበርዳት፤ በልታም፤ ጠጥታም፤ አግኝታም የማትረካዋ ህወሃት በጎንደርና በወሎ ያለውን ለም መሬት ለመውሰድ እዛ አካባቢ ያሉ ገበሬዎችን፤ ታሪክ ጠገብ አባቶችን በሙሉ ጨፍጭፋለች፡ ያ ሁሉ ሆኖ ግን ጠላትነቷ ከአማራ አልነበረም ከአማርኛ እንጂ።
በቋንቋ የሚግባባ ህዝብ ችግርም ቢኖር ተነጋግሮ መፍትሄ ያገኛል፡ በደለም ቢኖር ተነጋግሬ የበደለ ይክሳል፡ ተበዳይ ይካሳል፡ በደለኛም ይቀጣል፡ ግን የጋራ ቋንቋ ከሌለ፡ እንኳን በደልን፤ ጥፋትን ተነጋግሮ ወደመፍትሄ ለመድረስ ይቅርና መውደድንና ፍቅርን እንኳ ለመግለፅ አይቻልም። አንድን ማህበረሰብ ለመበታተን፤ ለማለያየት፤ ፈጽሞ እንዳይግባባና በጋር አብሮ እንዳይመክር፤ እንዳይዘክር ለማድረግ ቋንቋን ማለያየት ቁልፍ መፍትሄ መሆኑን ህወሃት ቀደም ብላ የተረዳችው ይመስላል።
በታሪክ አጋጣሚ ሆኖ አማርኛ የብሄራዊ መግባቢያ ቋንቋ ነበር፡ ብዙ ህዝብ የሚናገረው፤ የሚግባባበት መገናኛ ድልድይ ነበር።
ህወሃት ግን ያደረገችው የመጀመሪያ መሰሪ ሴራ ይህን መገናኛ ድልድይ መስበር፤ አማርኛ ቋንቋን ማዳከም ነበር። ሁሉንም ማህበረሰብ በየክልሉ አጥራ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ እንዳይኖር፤ አግዳ ተነጋግሮ የማይግባባ ትውልድ መፍጠር ነበር።
ይህ ሴራ ዘርን መሰረት ካደረገ ክልሏ ጋር በሚገባ ሰርቶላታል፡ 
የጎንደርና ወሎን ነዋሪዎችን አፈናቅላ፤ አሳዳ፤ በጅምላ ፈጅታ የህወሃትን ሰራዊት ስታሰፍር ያጠቃችው አማራን ሰለነበር የአማራን ጩኸት የሚሰማ አልነበረም፡ መግባባት የለማ፡ የተጨፈጨፈው "አማራ" እንጂ ኢትዮጵያዊ አልነበረማ፡ የጋራ ቋንቋ የለማ፤ የሚያስተሳስረን ድርና ማግ ተበጣጥሷላ፡

የጎንደርና ወሎ መሬት አልበቃ ብሎ የጋምቤላን መሬት ለመቀራመት አኝዋክን ሲትፈጅ፡ ሰሚ አልነበረም፡ የተጨፈጨፈው "አኝዋክ" ነዋ፡ ኢትዮጵያዊ አደለማ፡ የጋራ ቋንቋ የለ፤ የጋራ ሃገር የለ በጋራ የሚያስተሳስር ድር የለ፡
ጋምቤላ አልበቃ ብሎ ኦጋዴን መሬት ፍለጋ ስትሄድና "ኦጋዴኖችን" ስትፈጅ የ"ኦጋዴንን" ጩኸት የሰማ አልነበረም፤ ምክንያቱም የጋራ ቋንቋ፡ የጋራ ሃገር፡ የጋራ ድርና ማግ የለማ፡
እሱም አልበቃ በአፋር ለመስፋፋትና መሬትና የተፈጥሮ ሃብት ለመዝረፍ አፋሮችን ስትጨፈጭፍ የ"አፋርን" ጩኸት የሰማ አልነበረም፤ ምክንያቱም የሚጨፈጨፉት "አፋሮች" ናቸዋ፡ የሚያስተሳስረው ድርና ማግ ተበጣጥሷላ፡ ድልድዩ ተሰብሯላ፡ "አፋሮች" እንጂ ኢትዮጵያን አይደሉማ፡
አሁን ደግሞ ተረኛና ብዙ ሃብት ለማጋበስ የሚያስችለው ኣዲስ አበባ ዙሪያ ያለ መሬት ነው ስለዚህ በዙሪያው ለዘመናት የኖሩ ገበሬዎች መባረር አለባቸው፡ መሬቱን የህወሃት ባለስልጣናት ይፈልጉታላ፤ ህንጻ ይሰሩበታላ፤ ሸጠው ገንዘብ ያከማቹበታላ፡፡ ይህንን የተቃወሙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ልክ መግባት ስላለባቸው በጅምላ እየተጨፈጨፉ ነው። ጩኸታቸው ግን አይሰማም፤ ምክንያቱም የ"ኦሮሞ" ተማሪዎች ናቸዋ፡ ኢትዮጵያውያን አይደሉማ፤ የጋራ ቋንቋ የለማ፤ የሚያስተሳስረን ሃረግ ተበጣጥሷላ፡
ግን እስከመቼ፡ ለዚህ ለህወሃት ሴራ መሳካት ደግሞ ምሁራኖች ከፍተኛውን ድርሻ መውሰድ አለባቸው ብዬ በድፍረት ለመናገር እገደዳለሁ። የስርዓት ጥላቻን ከቋንቋ ጋር አገናኝቶ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ እንዳይኖር፡ ተቀራርቦ ተነጋግሮ ታሪካዊ ስህተቶች ቢኖሩ እንዛን ፈር ባለው መንገድ አስተናግዶ የጋራ በጋራ ተቆርቋሪነት መንከባከብ ሲቻል፡ የመጠፋፋት፡ የዘራፌዋ፡ ጉዞ ተመርጦ ስለነበር ለዚህ በቅተናል፡
አሁን በየዩኒቨርሲቲው የሚጨፈጨፉ ወጣቶች የማናቸው? የነ ጀነራል ጃጋማ ኬሎ ልጆች አደለም? የነ አብዲሳ አጋ ልጆች አደለም? የነ ሃብተጊዮርጊስ ዲነግዴ ልጆች አደሉም፡ ነገን ተረካቢ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች አደሉም? ግን ጩኸታቸው የኢትዮጵያን ተማሪዎች ሳይሆን የ "ኦሮሞ" ልጆች ጩኸት ተደርጎ ሌላው በታዛቢነት እያዳመጠ ነው።
አይበቃም? 
ጅምሩ ጥሩ ነው ሊባል ይችል ይሆናል ግን በቂ አደለም፡ ዛሬም ወጣቶች ከመታፈን አልዳኑም፤ ዘሬም በዱር በቀል የህወሃት አጋዚ ከመጨፍጨፍ አልተረፉም፡ 
የፈረሰውን ድልድይ የምንገነባው መቼ ነው፡ የተበጣጠሰውን ድርና መማግ የሚንቀጥለው መቼ ነው?
ጊዜ የለም በአራቱም ማዕዘናት ነገን ተረካቢ ወጣቶቻችን እየረገፉ ነው።
ህወሃትና ዱር በቀል አጋዚ ሰራዊቷ ባስቸኳይ ሊገቱ ይገባል፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ የጋራ ቋንቋ፡ የጋራ ሃገር አለን ብለን ስናምንና የሚያስተሳስረን ድርና ማግ አሁንም ጠንካራ መሆኑን ስንገነዘብ ነው፡

ለሁላችንም ልቦና ይስጠን!!

Monday, December 28, 2015

ፕ/ር መረራ ጉዲና ኢሕ አዲግ በኦሮሚያ ከልላዊ መንግስት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ አመጽ ሊያዳፈነው እንደማይችል ገለጹ፣ የአምቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የአገዛዙ አጋዚ ወታደሮች በዩኒቨርስቲው ውስጥ ገብተው የሚያደርሱባቸውን ጥቃት በመቃወም ወደ ቤተሰቦቻቸው ሄዱ፣ሴት ተማሪዎች መደፈራቸው ተገለጸ፣

ኤርትራ የየመኑን አካባቢያዊ ጦርነትን መቀላቀሏን በይፋ አሰታወቀች፣ሸንጎ የአገዛዙ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ የድንበሩን ጉዳይ ጨምሮ ያቀረቡትን የተምታታ ሪፖርት አጣጣለ ፣አገዛዙ የቅማንት ብሔር የማንነት ጥያቄን ውዝግብን ለማብረድ ልዩ ኮሚቴ አዋቅርኩ ይላል፣ የቅማንት የማንነት ጥያቄ ህወሃት ሆን ብሎ ተጨማሪ መሬት ለመውሰድ ያለመበት አጀንዳ ነው የሚሉ አሉ፣የነገረ ኢትዮጵያ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው እና ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ የአገዛዙ ፍርድ ቤት 28 ቀን ፈቀደ፣ ዛሬ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ለመወያየት ወደ ካርቱም የተጓዙት የኢትዮጵያ ልዑካኖች ከሰብሰባው ቦታ አርፍደው ደረሱ እና ቃለ መጠይቅ ቃለ መጠይቅ ከአቶ አለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር እና ከጋዜጠኛ አናኒያ ሶሪ ጋር እና ሌሎችም አሉንየህብር ሬዲዮ ታህሳስ 17 ቀን 2008 ፕሮግራም
<…አቶ ሀይለማሪያም የሚሉት የሚታመን ቢሆን ኖሮ ድንበር ለሱዳን አይሰጥም ነበር። ይሄን ስርዓት ላለፉት ሃያ አምስት ዓመታት አይተነዋል ።የማይታመን የአገሪቱን ጥቅም አሳልፎ የሚሸት ነው። የሳቸው የተምታታ ንግግርን ትተን ኢትዮጵያውያን ለሱዳን ቆርሰው ሊሰጡ በሩጫ ላይ ያሉበትን የአገራችንን ለም መሬት ለመስጠት የሚደረግ ማንኛውም ውል እንቃወማለን…ከኢትዮጵያ የትኛውም ግዛት አካባቢ ተቆርሶ የሚሄድ መሬት ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የሚመለከት ነው። ዛሬ የአገራችን መሬት ተላልፎ ለሱዳን እንዳይሰጥ በርካታ ኢትዮጵያውያን ድርጅቶች፣የአንድነትም ሆነ የብሄር ፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መገናኛ ብዙሃን፣በርካታ የሀይማኖትና የሲቪል ማህበራት የአገሪቱ ድንበር ለሱዳን ተላልፎ እንዳይሰጥ ተቃውመዋል።ይህንኑ ፒቲሽን ሁሉም እንዲፈርመውና ፊርማው ለተባበሩት መንግስታት …> የአቶ ዓለሙ ያይኔ የኢትዮጵያ የድንበር ጉዳይ ኮሚቴ ሊቀመንበር ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ መጠይቅ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

Sunday, December 27, 2015

ፋሺስታዊ ቅኝ አገዛዝ


ትናንት ከጥቂት ወዳጆቼ ጋር ስለ ህወሃቶች አዲዎሎጂ ውይይት አድርገን ነበር። ብዙዎቻችን የተስማማንበት ጉዳይ የህወሃት ዋነኛ አዲዎሎጂ በዘረኝነት ላይ የተመሰረተ ፋሺዝም መሆኑን ነው። የፋሺዝም ዋነኛ መገለጫ ባህሪ በብዙሃን ስም የጥቂቶችን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ወታደራዊ የበላይነት በብዙሃኑ ላይ በሃይል መጫን ነው። ፋሺዝም በሰው ልጆች እኩልነት፣ ነጻነት እና ፍትሃዊ ብልጽግና እና አስተዳደር ፈጽሞ አያምንም። 
ከተቋቋመ ከ፵ አመታት በሁዋላም ህወሃት አሁንም የትግራይ ህዝብ ነጻ አውጪ ነኝ ብሎ እራሱን ያታልላል። ህወሃት በነጻነት ስም በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ፋሺስታዊ ቅኝ አገዛዝን ካሰፈነ ፪፭ አመታት ተቆጠሩ። የትግራይን ህዝብ ከማን ነጻ እንደሚያወጣ ቢጠየቅ እንኳ መልስ በአግባቡ ሊሰጥ አይችልም። 
እውነታው ግን ህወሃት የኢትዮጵያን ህዝብ ገባር አድርጎ በዘር ሃረግ ከፋፍሎ ለጥዊቶች መጠቀሚያ የሆነች ኢትዮጵያ የምትባል የጥገት ላም እያለበ እንደመዥገር ደም እየመጠጠ ለመኖር ሲታገል ይህንን አጸያፊ ወንጀል ለማስፈጸም በኢትዮጵያዊያን ላይ እጅግ አስከፊ በደል እና ግፍ እየፈጸመ ከንቱ እድሜውን እየገፋ ይገኛል። ይሄ የማፍያ ድርጅትና መሪዎች ለኢትዮጵያ ህዝብ ያላቸውን ጥላቻ ዘውትር በሚፈጽሙት ግፍና በደል ከበቂው በላይ አስመስክረዋል። 
አንድ የቅኝ አገዛ (internal colonialism) ሰለባ የሆነ ህዝብ ያለውን ነባራዊ እውነታ ተገንዝቦ ክብሩን፣ ነጻነቱን፣ ታሪኩን እና ማንነቱ ዘውትር እያረከሱ በጭካኔ እረግጠውና ቀጥቅጠው ሊገዙት የሚግተረተሩትን ወያኔዎች በቀጥታና በተዘዋዋሪ መንገድ ሊዋጋቸው ያስፈልጋል። ስለዚህም ነው ወያኔን እና ቅጥረኛ የቅኝ አገዛዝ አስፈጻሚዎች ላይ ህዝባችን በህብረትና በአንድነት ከዳር እስከዳር ተነስቶ የጫኑበትን የቅኝ አገዛዝ ቀንበር ሰባብሮ ለመጣል በቃ ብሎ መነሳት ያላበት። 
እነሱ አሳሪ እኛ ታሳሪ፣ እነሱ ገዳይ እኛ ተገዳይ፣ እነሱ ዘራፊ እኛ ተዘራፊ፣ እነሱ ጌታ እኛ ሎሌ፣ እነሱ አባራሪ እኛ ተባራሪ፣ እነሱ ቅኝ ገዢ እኛ ቅኝ ተገዢ ሆነን መቀጠል ፈጽሞ አንችልም።
አበበ ገላው

ኢትዮጵያ የማን ናት? (ከአንተነህ መርዕድ) ከአንተነህ መርዕድ

“ኢትዮጵያ የማን ሆና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው” ( ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳ)
“ኦሮሞ ግንድ ነው አይገነጠልም” (ጄኔራል ጀጋማ ኬሎ)

ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት የብዙ አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የልብ ህመም ሆኖ የቆየው የኦሮሞ ጥያቄ ነው። ዛሬም በኢትዮጵያ ህልውና ወሳኝ ጥያቄ ቢኖር የኦሮሞ
Map of Ethiopia
ጥያቄ ነው። ኢትዮጵያን ለማጥፋት ሆነ በጨለማ ለመግዛት የተነሱት ጣልያንም ሆነ ወያኔ ለአላማቸው ማስፈፀምያ የዚህን ታላቅ ህዝብ ጥያቄ ነበር ኢትዮጵያን ለመጉዳት የሚጠቀሙበት። ከላይ በጥቅስ ያስቀመጥኋቸውን ሃሳቦች የተናገሩት በኦሮሞ ህብረተሰብ ውስጥ ትፅዕኖ ፈጣሪና ታላቅ ኢትዮጵያውያን ናቸው። ከአስራ አራት ዓመት በፊት በሞት የተለዩን ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳን ንግድ ማተምያ ቤት አጠገብ ባለው መኖርያ ቤታቸው ለጦቢያ መጽሄት ቃለ መጠይቅ ልናደርግላቸው አንጋፋው ጋዜጠኛ አቶ ሙሉጌታ ሉሌ ጋር ሄደን ነበር። ሜጫና ቱሉማን በመመስረትና ለኦሮሞ መብት በመታገል ኢትዮጵያዊ መፍትሄ እንዲያግኝ በመልፋት የሚታወቁት እኒህ አንጋፋ አባት አመሻሽ እድሜአቸው ላይ ሆነው ያዩት ሁሉ አላስደሰታቸውም።

አክራሪ ፅንፍ የያዙ የኦሮሞ ኤሊቶች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን መለየትን እንደመፍትሄ በግልፅ በሚሰብኩበትና ለተግባራዊነቱ በሚገፉበት፤ ወያኔም ይህንኑ አጀንዳ አስጨብጦ በሚያራግብበት ፈታኝ ወቅት ነበር የሄድንባቸው። አምቦ አካባቢ ግንደበረት ተወልዶ ከማደጉም በላይ የኦሮሞን ህብረተሰብ ጠንቅቆ የሚያውቀው ጋሽ ሙሉጌታ ከኮሎኔሉ ጋር ያላቸውን መግባባትና መከባበር ስመለከት ተገርሜያለሁ። በርካታ አገራዊና የግል ጥያቄዎችን ያቀረብንላቸው ቢሆንም በቁጣ ስሜት የመለሱት ለኦሮሞ ችግር ከኢትዮጵያ መገንጠል መፍትሄ ይሆናልን? የሚለውን ጥያቄአችንን ነበር። “ኢትዮጵያ የማን ሆና ነው ኦሮሞ የሚገነጠለው?” በማለት ነበር ጥያቄአችንን በጥያቄ የመለሱት።
ኦሮሞ የኢትዮጵያ እምብርት ብቻ ሳይሆን ከሰሜን ጫፍ እስከ ትግራይ፣ በደቡብ እስከ ኬንያ፤ በምስራቅ ኦጋዴንን ነክቶ በምዕራብ ሱዳን ድረስ ሲያጣቅስ በመሃል ከአብዣኛው ኢትዮጵያውያን ተዛንቆ፣ ተዋልዶ፣ ተዋህዶ በመኖሩ እድሉ የኢትዮጵያ ባለቤት መሆን እንጅ ጊዜው እንደወለዳቸው ፖለቲከኞች ቁራሽ መሬት ይዞ መወሰን አይደለም የህዝቡ ፍላጎት። ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳም የገለፁት ይህንኑ የኦሮሞ ህዝብ ፍላጎት ነበር። ቃለ መጠይቁን ለህትመት አብቅተን ኮሎኔል ዓለሙን ደግመን ስናገኛቸው ያየሁትና የሰማሁት ለብዙ ጊዜ አሳዝኖኛል። የጊዜው የፖለቲካ አራጋቢዎች ትልቅ የመንፈስ ስብራት ፈጥረውባቸው ነበር። “ዛሬ በሽምግልናዬ ቤት ውስጥ ተወስኜ ሞቴን በጸጋ በምጠብቅበት ሰዓት የአገር ጉዳይ ጠልቆ ያልገባቸው ወንድሞቼ በእኔና በቤተሰቤ ያሳደሩብኝ ጫና ቀላል አይደለም። ቀሪ ጊዜዬን በሃዘን እንዳልቋጨው ታገሱኝ” አሉን። እኛም ታገስናቸው።
ዛሬ ኮሎኔል ዓለሙ ቂጤሳና አንጋፋው ጋዜጠኛ ሙሉጌታ ሉሌ በህይወት የሉም። ጋሽ ሙሉጌታ ሊለየን ትንሽ ሰዓታት ሲቀረው “ለዘመናት ወጣቱ ላይ የነበረኝን ወቀሳ አንስቻለሁ፤ አገሩን የሚታደግ ወጣት በማየቴ ኮርቻለሁ። በሉ ተነሱ ሰልፍ የጀግና ነው፣ ድል የእግዜብሄር ነው” ሲል ተስፋውንና ጥሪውን ገልፆ አልፏል። የኦሮሞ ህዝብና ቀሪው ኢትዮጵያዊ ባንድ ቁሞ ታላቋን ኢትዮጵያን የመገንባቱ ተስፋ እየለመለመ ነው። የኦሮሞ ህዝብ የኢትዮጵያ ባለቤት ለመሆን አገራዊ አጀንዳ ይዞ እየተነሳ ነው። የኦሮሞ ፖለቲከኞች (ኤሊቶች) እንደ ኦሮሞ ህዝብ ሰፊ ልቦናና ኢትዮጵያዊ ባለቤትነትን ካላቀፉ ለጠባቡና ለጊዜአዊ የፖለቲካ ፍጆታ ራሳቸውን ወስነው መነሳት እንደማያዋጣቸው የተረዱ ይመስላል። ከአንጋፋ ፖለቲከኞች ሌንጮ ለታና ጓዶቻቸው፣ ከወጣቶቹም ጁአር ሞሃመድና ሌሎችም ሰሞኑን ያሳዩት ሁሉን አቃፊ (አኮሞዳቲቭ) አቋም ያየ፤ የኦሮሞ ፖለቲከኞች የኦሮሞን ህብረተሰብ በሚመጥን ደረጃ ለመገኘት መንቀሳቀሳቸውን ወይንም መፈለጋቸውን ይገነዘባል። ያድርግልን። ከሰሞኑ የህዝብ አመፅ በኋላ የአማራውና የኦሮሞው አንድነት ጥሪ በሰፊው ተሰብኳል። አመፁን ተከትሎ የመጣ በረከት ይመስላል (ፈረንጆች ኤ ብሌሲንግ ኢን ዲስጋይዝ እንደሚሉት)። አመፁን ወደ እውነተኛ አንድነት እንዲያድግ ከተፈለገ አጀንዳው ከክልላዊነት ወጥቶ ወደ አገራዊነት መለወጥ አለበት።

Saturday, December 26, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)



‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ በአገር ውስጥ በገጠመው እጅግ በጣም አስጊ ሁኔታ ምክንያት በሶማሊያ ተሰማርቶ የነበረውን የአየር ኃይል ቡድን ወደ ኢትዮጵያ የመመለስ ውሳኔ ላይ ደርሶ ቡድኑ የጉዞ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ታወቀ፡፡
====================================================
በሶማሊያ ከአሚሶም ጎን ለግዳጅ ተሰማርቶ የነበረው የህወሓት አየር ኃይል ቡድን እዚህ ግቡ የማይባሉ ሰባት አሮጌ ሄሊኮፕተሮች የነበረው ሲሆን ሶስቱ ወደ ደቡብ ሱዳን ሊሄዱ ተብሎ ከጥቂት ሳምንታት በፊት ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል፡፡ ሆኖም እስካሁን ምንም አይነት እንቅስቃሴ አላደረጉም፤ የደቡብ ሱዳኑ ጉዞም መሰረዙ ተሰምቷል፡፡ ቀሪዎቹን አራት የሾቁ ሄሊኮፕተሮች የታጠቀው የአየር ኃይል ቡድን ደግሞ አሁን ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ዝግጅቱን አጠናቆ የጉዞ እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡ 
የህወሓት አገዛዝ በኦሮምያ የተቀሰቀሰውን ህዝባዊ ተቃውሞ በጉልበት አፍኖ ለማርገብ በሱሉሉታ የተጠቀማቸው "የትራንስፖርት" ሄሊኮፕተር አብራሪዎች በጣም ዝቅ ብለው በመብረር ጭነዋቸው በነበሩት የአግአዚ ኮማንዶ አልሞ ተኳሾችና መትረየስ ታጣቂዎች ህዝቡን እንዲጨፈጨፍ አላደረጉም በሚል በግምገማ ተወጥረው እንደሚገኙ ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡

Friday, December 25, 2015

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃዥተዋል “መሬት ቆርሰን አልሰጠንም… ነገር ግን ሱዳን ድንበር ውስጥ ገብተው የሚያርሱ የኢትዮጵያ ገበሬዎች አሉ

ዛሬ ፓርላማ ላይ የቀረቡት አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ “ድንበር ቆርሰን አልሰጠንም… ግን በሱዳን መሬት ውስጥ ገብተው እያረሱ ያሉ የኢትዮጵያ ገበሬዎች አሉ” ሲሉ ተናገሩ:: በቅርቡ የድንበር ማካለል እናደርጋለን ያሉትና የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው የቀረቡት አቶ ኃይለማርያም በሱዳን መሬት ላይ ገብተው እያረሱ ያሉትን ባለሃብቶች ድንበሩ እስከሚካለል ድረስ አትንኩብን ስንል የሱዳን መንግስትን ጠይቀናል ብለዋል:: ::
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/49454

Hailemaria

የ11ኛው ሰዓት ጥሪ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ይመለከታል! December 25, 2015


የንቅናቄያችን መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባደረጉት የትግል ጥሪ በ11ኛው ሰዓት ላይ እንደምንገኝ ገልጸዋል ። የ 11ኛው ሰዓት መልዕክት፣ አንደኛ፣ ወደ 12ኛው ሰዓት ወይም ወደ ፍጻሜው እየተቃረብን መሆኑን የሚነገረን ነው። የ11ኛው ሰዓት የትግል ጥሪ የአንድን የትግል ምዕራፍ ለመዝጋት እና አዲስ የትግል ምዕራፍ ለመጀመር የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል የምናደርግበት ጊዜ ላይ መድረሳችንን የሚገልጽ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጥሪው ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚፈጠረው አዲስ ስርዓት ከአሁኑ ማሰብ መጀመር እንዳለብን የሚያነቃን ደወል ነው። 11ኛው ሰዓት ላይ ቆመን ከ12ኛው ሰዓት በሁዋላ ስለሚፈጠረው ነገር መጨነቅ ካልቻልንና በጊዜ ቤታችንን ካላሰናዳን ፣ ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ሊገጥሙን የሚችሉትን ተግዳሮቶች በጊዜና ብቃት ባለው መልኩ ለመፍታት መቸገራችን አይቀርም ። አንድ በእድሜ የገፋ ሰው 11ኛው ሰዓት ላይ መሆኑን ሲያውቅ ከህይወቱ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚኖረው ህይወት ማሰላሰሉ ተፈጥሯዊ ነው። የ11ኛው ሰዓት ጥሪም የአንድን አገዛዝ እርጅናና ፍጻሜ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ በቦታው የሚወለደውን አዲስ ስርዓት ምንነትም የሚያሳይ ነው።

የ11ኛው ሰዓት ጥሪ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ይመለከታል! December 25, 2015


def-thumb
የንቅናቄያችን መሪ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ህዝብ ባደረጉት የትግል ጥሪ በ11ኛው ሰዓት ላይ እንደምንገኝ ገልጸዋል ። የ 11ኛው ሰዓት መልዕክት፣ አንደኛ፣ ወደ 12ኛው ሰዓት ወይም ወደ ፍጻሜው እየተቃረብን መሆኑን የሚነገረን ነው። የ11ኛው ሰዓት የትግል ጥሪ የአንድን የትግል ምዕራፍ ለመዝጋት እና አዲስ የትግል ምዕራፍ ለመጀመር የመጨረሻ የሞት ሽረት ትግል የምናደርግበት ጊዜ ላይ መድረሳችንን የሚገልጽ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ጥሪው ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚፈጠረው አዲስ ስርዓት ከአሁኑ ማሰብ መጀመር እንዳለብን የሚያነቃን ደወል ነው። 11ኛው ሰዓት ላይ ቆመን ከ12ኛው ሰዓት በሁዋላ ስለሚፈጠረው ነገር መጨነቅ ካልቻልንና በጊዜ ቤታችንን ካላሰናዳን ፣ ከትግሉ ፍጻሜ በሁዋላ ሊገጥሙን የሚችሉትን ተግዳሮቶች በጊዜና ብቃት ባለው መልኩ ለመፍታት መቸገራችን አይቀርም ። አንድ በእድሜ የገፋ ሰው 11ኛው ሰዓት ላይ መሆኑን ሲያውቅ ከህይወቱ ፍጻሜ በሁዋላ ስለሚኖረው ህይወት ማሰላሰሉ ተፈጥሯዊ ነው። የ11ኛው ሰዓት ጥሪም የአንድን አገዛዝ እርጅናና ፍጻሜ የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን፣ በቦታው የሚወለደውን አዲስ ስርዓት ምንነትም የሚያሳይ ነው።

The so call Ethiopia prime minister confirmed again that they will give away Ethiopians land to Sudan by saying a number of our farmers and investors are cultivating long deep in Sudan's land. ሰበር ዜና: አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የኢትዮጵያ መሬት ለሱዳን የመሰጠቱን ጉዳይ ዳግም አረጋገጡ።ንግግራቸው የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር አስመስሏቸዋል።''በታሪካችን ያላየነው ረሃብ ላይ ነን'' አቶ ኃይለ ማርያም (ጉዳያችን ዜና)


ከግማሽ ክፍለዘመን በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ፓርላማ ማማ
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ዛሬ ታህሳስ 15/2008 ዓም በኢትዮጵያ ፓርላማ ቀርበው በሰጡት ማብራሪያ ላይ በተለይ በኦሮምያ ክልል ለተነሳው ሕዝባዊ አመፅ እና በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው የድንበር ጉዳይ ላይ የተለመደ አወዛጋቢ እና የበለጠ አወሳሳቢ ንግግሮችን ተናግረዋል።
በኦሮምያ የተነሳውን ሕዝባዊ አመፅ ችግሩን፣መነሻውን እና መፍትሄውን የጠቆሙበት አገላለፅ የእራሳቸውን እና የመንግስታቸውን መፍትሄ ቢስነት በአደባባይ በድጋሚ ያጋለጠ ነው።ችግሩ ገበሬው መረጃ አለማግኘቱ ነው ማለታቸው እና በውጭ ኃይሎች ቅስቀሳ ነው የሚለው እርስ በርሱ የተቃረነ አነጋገር በእራሱ ለእራሳቸውም በአግባቡ የገባቸው አይመስልም።ችግሩን መንግስት ስለ ፕላኑ አለመንገሩ ነው ያሉት እና አሁን መንግስታቸው እያናገረ ያለው በጥይት መሆኑን ለሚያስተውለው የኢትዮጵያ ሕዝብ ንግግራቸው በሕዝቡ ላይ ከመዘባበት ያለፈ አንዳች የሚሰጠው ፋይዳ የለም።በመፍትሄነት ያስቀመጡትም ምንም አዲስ ነገር የሌለው እና አሁንም መልሰን እንነግረዋለን የሚለው አባባል ንግግሩ በጥይት እንደሆነ አመላካች ነው።ሕዝብ የሚባለው እና የሚደረገው ስላልገባው ነው የሚለው አባባል በእራሱ ለሕዝብ ያለን የንቀት ደረጃ አመላካች ነው።በሰላማዊ ሰልፍ እጆቻቸውን ወደ ሰማይ እየሰቀሉ ድምፃቸውን ያሰሙ ታዳጊዎችን በጥይት አረር ከመቱ (እንደ አቶ ኃይለማርያም አነጋገር 'ካናገሩ') በኃላ አሁንም እናናግራለን እያሉ መዘባበት በእራሱ ህዝብን የአላዋቂነት ጥግ ነው።
በሌላ በኩል የሱዳን እና የኢትዮጵያን የድንበር ማካለል ጉዳይ ላይ የጀመሩበት አረፍተ ነገር እና በመካከል እና በመጨረሻ ላይ የደመደሙበት ንግግር ኢትዮጵያ በእዚህ አይነት ደረጃ የባዕዳንን ጉዳይ የሚያስፈፅም መንግስት ኖሯት እንደማያውቅ በግልፅ የሚያሳይ ነው።
''በመሬት ጉዳይ ላይ የተደረገ ድርድር የለም። በኢትዮጵያ እና በሱዳን መሃል ያለው ድንበር በደንብ ስላልተስተካከለ በእርሱ ላይ ነው እየሰራን ያለነው'' ካሉ በኃላ የሱዳን ጠቅላይ ሚንስትር የሚናገሩ እስኪመስል ድረስ የኢትዮጵያን ክብር በሚነካ መልኩ ሱዳንን እየረበሽን ያለነው የእኛ ገበሬዎች ናቸው።አሁን የሚያርሱት መሬት የሱዳን መሬት ነው ብለው ለመከራከር ሞክረዋል።ይህ ማለት ባጭሩ ኢትዮጵያውያን ለዘመናት ሲያርሱት የነበረው መሬት በእራሳቸው አገር ጠቅላይ ሚኒስትር መሬቱ የሱዳን ነው እየተባሉ ነው ማለት ነው።በተለይ የሱዳን ወታደሮች ለስራ በወሰዷቸው ኢትዮጵያውያን ላይ ባለፉት ሶስት ወራት ውስጥ ብቻ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ስለመገደላቸው አንዳች ያልተነፈሱት አቶ ኃይለማርያም ይልቁንም የኢትዮጵያን ገበሬዎች በሱዳን ተገብተው ሲወቅሱ እንዲህ ብለዋል- 

Thursday, December 24, 2015

ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ መንግስት ወጣቶችን በየአካባቢው እያፈሰ ከማሰሩም በላይ የተቃዋሚ መሪዎችን ሲያስፈራራ ከቆየ በሁዋላ መሪዎችን ይዞ ማሰር ጀምሯል። በቅርቡ ከእስር የተፈቱት የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ተቀዳሚ ም/ል ሊ/መንበር አቶ በቀለ ገርባ እንዲሁም የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ዋና ጸሃፊ የሆኑት የህግ ባለሙያውና ከ10 አመት በፊት በተደረገው ምርጫ የፓርላማ አባል የነበሩት አቶ ደጀኔ ጣፋ ገለታ በጸጥታ ሃይሎች ተይዘው ታስረዋል። ግለሰቡ ከዚህ ቀደም በመንግስት ላይ በሚያደርሱት ጠንካራ ትችት ይታወቃሉ። በተመሳሳይ ዜና በጅማ ሂምና ዩኒቨርስቲ የሚማሩ 13 የኦሮሞ ተወላጆች ተማሪዎችን ለተቃውሞ ቀስቅሰዋል በሚል እየተፈለጉ ነው። የዩኒቨርስቲው የጥበቃና ደህንነት የስራ ሂደት ቢሮ ባወጣው ማስታወቂያ ገመችስ ታከለ፣ አሸናፊ ሌንጂሳ፣ አለማየሁ ገመቹ፣ መብራቱ ጅሬኛ፣ መሃመድ ሸምሲዲን፣ አብዲሳ በንቲ፣ ፋጂ ሙላት፣ አብደላ ተስሳ፣ ዘነበች ጌታቸው ፣በሻቱ ቃናአ፣ ቢራ ነጋሽ ደመቀ እንዲሁም አሰፋ ፋና ታህሳስ 14 በዩኒቨርስቲው ተገኝተው የዲሲፒሊን ኮሚቴው የሚሰጠውን ውሳኔ እንደከታተሉ ተጠርተዋል። በኦሮምያ በተካሄደው ህዝባዊ ተቃውሞ 85 ዜጎች በአጋዚ ወታደሮች ሲገደሉ ከ1 ሺ በላይ የሚሆኑ ደግሞ ታስረዋል።

ከ “ናስ ማሰር – አፍ ማሰር” (ይገረም አለሙ) ይገረም አለሙ

ጊዜው ድሮ ድሮ ነው፡፡ቦታው ደግሞ ዝናር ወይንም ጀበርና ታጥቆ ብረት/ጠብ -መንጃ ትከሻ ላይ ጣል አድርጎ መሄድ አንድም ለአቅመ ወንድነት መድረስ ሁለትም በሀብት ከሌላው የተሻሉ ተደርጎ የሚታይበት አካባቢ ነው፡፡ ደረስኩ ደረስኩ ያለ ጎረምሳ በወቅቱ ተወዳጅና ተመራጭ የነበረውን ናስ ማሰር የተባለ ብረት/ጠመንጃ ይገዛና በሀገር በሰፈሩ አንቱ የተባሉና የተከበሩ ሽምግሌ ጋር በመሄድ አባት እስቲ ይህችን ብረት እዩልኛ ይላቸዋል፡፡ ርሳቸውም እያገላበጡ እያዩ ቀዝቀዝ ባለ ስሜት ጥሩ ናት ሸጋ ብረት ናት ይሉታል፡፡ ከገጽታቸውና ከአነጋገራቸው ጥሩ ስሜት አንዳልተሰማቸው የተረዳው ጎረምሳ ምነው አባት ሆሳ ነች እንዴ ወጥ አይደለችም? ሲላቸው አረም ሸጋ የሆነች ወጥ ብረት ነች ይሉታል፡፡ አሁንም አነጋራቸው ስላላማረው ታዲያ ምነው አነጋገርዎ ቀዝቀዝ ቢላቸው አዎ ልጄ ከናስ ማሰር አፍ ማሰር ነው የሚበጀው ብየ ነው አሉት ይባላል፡፡
Getachew Reda, Press and Publicity State Minister
የህይወትም ሆነ የንብረት ደህንነት የሚጠበቀው በጠመንጃ ሳይሆን እጅ በሚሰራው መልካም ድርጊት ከአንደበት በሚወጡ የታረሙ ቃላት ነው፡፡ በጠመንጃ እየተማመኑና በጡንቻ እያሰቡ የሚሰሩትና የሚናገሩት ሁሉ ጠላት ስለሚያፈራ፡ የህይወትና የንብረት ደህንነት አይኖርም፡፡ ስነ ምግባር የገራውና በራሱ እንዲፈጸምበት የማይፈልገውን በሌሎች የማይፈጽም፤ ፈሪሀ እግዚአብሄርን የተላበሰና አንደበቱ የታረመ ለህሊናው የሚገዛ ሰው ግን ወዳጅ እንጂ ጠላት ስለማይኖረው በቀንም ሆነ በለሊት በሜዳም ሆነ በጫካ ብቻውን ቢጓዝ የሚያሰጋው ነገር አይኖርም፡፡
በጠመንጃ መተማመን ሲጀመር የማሰብንና የመወሰንን ስራ ጡንቻ ስለሚረከብ የሚሰራው ሁሉ የእብሪት የሚነገረው ሁሉ ለከት የለሽ ይሆንና ወዳጅ እያነሰ ጠላት እየበዛ ይሄዳል፡፡ ይህ አድራጎት በፖለቲከኞች ሲፈጸም ደግሞ የሚያስከትለው ጦስ ከድርጊቱ ፈጻሚዎች ይልቅ ሀገርንና ሕዝብን ይሆናል የሚጎዳው፡፡

Breaking: TPLF Arrest Obbo Bekele Gerba

Breaking: TPLF Arrest Obbo Bekele Gerba

ኢሳት ቴሌቪዥን፣ OMN ቴሌቪዥን፣ የአሜሪካ ራድዮ ድምጽ፣ ዘሐበሻ ድረ ገጽ፤ በወያኔ መንግስት በቢሊዮን ዶላር ወጪ በማድረግ በኢትዮጵያ እንዳይታዩ ከፍተኛ የሆነ አፈና እየተደረገባቸው ነው። – ከተማ ዋቅጅራ

ፌድራል ፖሊስ እንደ ሸለምጥማት ጣራ ለጣራ በመንጠላጠል ዲሽ ሲነቅል ማየታችን ስርአቱ ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳለ የሚያሳይ ነው። ዛሬ ዲሻችንን እንደነቀላችሁ ነገ እናንተ ትነቀላላችሁ ዛሬ መብታችንን እንደረገጣችሁ ነገ የእናንተ  እጣ የከፋ እንደሚሆን አትዘንጉ።
አፈናን ዋና አላማው አድርጎ  እየተንቀሳቀሰ ያለው ወያኔ በአገር ቤት ሆነ በመላው አለም በከፍተኛ ሁኔታ አድማጭ እና ተከታዮችን እያፈሩ ያሉትን ነጻ የህዝብ ሚዲያ  አካሎችን የአገሪቱ ንብረት እየዘረፈ በቢሊዮንስ ዶላይ በማውጣት ወንጀል ከመስራት አልፎ ህዝቡ እውነተኛ መረጃን እንዳያገኝ የማፈን ስራዎችን በመስራት ለይ ይገኛል። ወያኔ የሞት ሽረት ትግል በማድረግ ያላቸውን አቅም ሁሉ ለአፈናቸው ተግባር በማሰማራት በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ የሚዲያ አውታሮች እንዳይሰራጭ ከፍተኛ መፍጨርጨር እያደረጉ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ደግሞ  መስማት የሚፈልገው እውነትን ስለሆነ ዛሬ በይፋ ለማፈን የሚንቀሳቀሱባቸው የሚዲያ አውታሮችን ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ በሚባል መልኩ የነጻ ሚዲያ አድማጭ ሆኗል። ህዝቡም  እውነተኛ መረጃዎችን የሚያገኝባቸው በዋነኛነት ኢሳት፣ OMN፣ የአሜሪካ ራዲዮ፣ የጀርመን ራሪዮ፣ ዘ-ሐበሻ፣ ECADF፣ ሳተናው፣ Gadaa.com፤ ከመሳሰሉት የህዝብ ሚዲያዎች ሲሆን ከነዚህ ነጻና  ትክክለኛ ዘገባዎችን በመዘገባቸው የተነሳ ለህዝቡ ከፍተኛ ግንዛቤ በመስጠት ላይ ይገኛሉ። ኢትዮጵያ ውስጥ ምን እየተሰራ እንዳለ በስልጣን ላይ ያለው አካል በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ምን አይነት ጥፋትና በደል በመቀየስ አደገኛ አካሄድ እየሄደ እንዳለ ለህዝቡ በግልጽ በነዚህ የሚዲያ አውታሮች  ሲለሚነገራቸው ሁሉም ኢትዮጵያዊ የነዚህ ሚዲያዎች ተከታዮች እና አድማጮች ሆነዋል።
ኢሳት ከጅምሩ ጀምሮ በወያኔዎች  አፈናዎች እየተደረገበት በኢትዮጵያ ውስጥ መሰማት የለበትም ብለው ቢንቀሳቀሱም ኢሳት ግን ከፍተኛ ርብርቦሽ በማድረግ ዜናዎችን ወደ ህዝቡ እንዲደርስ እያደረገ ነው። ኢሳት ለኢትዮጵያ  ህዝብ  ሲተረጎም ኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን የሚለውን ትርጉም ሲይዝ ለወያኔዎች እና ለሆድ አደር ካድሬዎች ደግሞ እሳት የሚለውን ትርጉም ይሰጠናል።  ምክንያቱም አይስማማቸውም ይፈጃቸዋል በጓራቸው የሰሩትን ደባ በአደባባይ ይበትነዋል በምሲጢር ያወሩትን ተንኮል በህዝብ ፊት ያጋልጣቸዋል የህዝብን ችግር እና ሃሳብ በነጻነት ወደ ህዝብ ያደርሳሉ።  በዚህ አጋጣሚ ለኢሳት ጋዜጠኖች በሙሉ ከፍተኛ ክብር ያለኝ መሆኑን ለመግለጽ እወዳለው።በተለይ ለሲያይ አጌና፣ ለመሳይ መኮንን፣ለፋሲል የኔአለም፣ እንዲሁም ለሌሎቹ ከፍተኛ አድናቆት እና ክብር አለኝ  የእናንተ ክብራችሁ እውነታችሁ፣ ክብራችሁ ኢትዮጵያ አገራችሁ፣ ክብራችሁ ህዝባቹ ነውና በርቱልን እንላለን።

Tuesday, December 22, 2015

Ethiopian Government Kill Protesters To Expand Addis Ababa

Ethiopian Music: “embi bel” Shambel Belayneh’s new song

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) "አማራ ክልል" እየተባለ የሚጠራው ሹም እና የህወሓት ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው ገዱ አንዳርጋቸው በዛሬው ዕለት ወደ አርማጭሆ ሙሴ ባምብ ከተማ አምርቶ የአካባቢውን ህዝብ ለማወያየት ሞክሮ ያለምንም ውጤት በውርደት ተመለሰ፡፡ ====================================================

 
የህወሓቱ አሽከር ገዱ አንዳርጋቸው ዛሬ ጠዋት በከፍተኛ ወታደራዊ አጀብ ከባህር ዳር አርማጭሆ ሙሴ ባምብ ገብቶ የአካባቢውን ህዝብ በሦስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ለማነጋገር ሞክሯል፡፡ 
በስብሰባው ላይ የተነሱት ሦስቱ የመወያያ አጀንዳዎች፦
1. በጎንደር የተከሰተው የእርስበርስ ግጭት
2. የወልቃይት ህዝብ የማንነት ጥያቄ እና
3. የኢትዮ-ሱዳን ድንበርን በሚመለከት ናቸው፡፡
ገዱ አንዳርጋቸውና ሌሎች የብአዴን ካድሬዎች በመሩት ስብሰባ ላይ የተገኘው የአርማጭሆ ህዝብ በጎንደር የተከሰተውን የእርስበርስ ግጭት ህወሓት እንደጠነሰሰው እና የእሱ ዲቃላ የሆነው ብአዴን እጁ እንዳለበት ገልጿል፡፡ ብአዴን የአህያ ባል ሆኖ ህወሓት ለተባለ የቀን ጅብ አሳልፎ ሰጥቶ የወልቃይትን ህዝብ እያስበላው እንደሚገኝም ህዝቡ ጨምሮ ተናገሯል፡፡ 
ድንበሩን በሚመለከት ደግሞ
"እናንተም ሆናችሁ ህወሓት የአገሪቱን ዳር ድንበር ማስከበር ስላልቻላችሁ፣ ህዝቡንም መምራት ስለተሳናችሁ ስልጣናችሁን ልቀቁ አርበኞች ግንቦት 7 ይምራን..." በማለት ድፍረት በተሞላበት ሁኔታ በአንድነት ጠይቋል፡፡ ከእንግዲህ ወዲህ ለሱዳን ተቆርሳ የምትሰጥ አንድ ጋት መሬት እንኳን ብትኖር ህዝቡ ከውስጥም ከውጭም በአንድነት ለመዋጋት ቆርጦ እንደተነሳና ህወሓት ከባድ ዋጋ እንደሚከፍል ማስጠንቀቂያ ጭምር አስተላልፏል፤ ጀግናው የአርማጭሆ ህዝብ፡፡
በአጠቃላይ በአርማጭሆ ሙሴ ባምብ በህወሓት አሽከር ገዱ አንዳርካቸው እና በህዝቡ መካከል በዛሬው ዕለት የተካሄደው ውይይት ከፍተኛ ንትርክና እሰጥ አገባ እንዲሁም የከረረ ቁጣና ተቃውሞ የተሞላበት ሲሆን ከቀኑ 9፡30 ላይ ያለምንም ውጤት በአገዛዙ ውርደት የተላበሰ ሽንፈት ብቻ ተቋጭቷል፡፡

Monday, December 21, 2015

በቅርቡ የምንሰማው ዜና በጥምር ተቀናጅተው ኦነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ወደፊት እየገሰገሱ ወያኔን መቆሚያ እያሳጡት ነው የሚለው ይሆናል። – መርጋ ደጀኔ (ከኖርዌይ)

Tenesuምከረው ምከረው እንቢ ካለ መከራ ይምክረው እንደሚሉት አበው 25 ዓመት ሙሉ ሲመከር ሲለመን ሲዘከር ምክርን እንደ ስድብ ልመናን እንደ ፍራቻ ዝክርን እንደ ማታለል አድርጎ በመቁጠር ዝም በሉ ዝም ካላላችሁ ዝም አደርጋችሃለሁ ረግጫችሁ እገዛችኋል አማራና ኦሮሞን አጋጭቶ በመሃል እኔ ስልጣኔን እያደላደልኩኝ 100 ዓመት እገዛለሁ ብሎ የቀየሰው ስልት ዛሬ በእርግጠኝነት መናገር ወደሚቻልበት ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ  በመግባቱ ታውቋል። ኦነግና  አርበኞች ግንቦት 7 የተቀናጀ ድምጽ አሰምተውን ኦነግ በአሶሳ ፤በሀረር ፤በቦረና ወያኔን እየደመሰሰ ወደ ፊት እየመጣ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 በጎንደር፤ በጎጃም ፤በደቦብ በድሬደዋና በመላው ኢትዮጵያ ብሎም በአዲስ አበባ ትግሉን በማቀጣጠል ወያኔን መቆሚያና መቀመጫ እያሳጡት ነው የሚለውን ዜና እንሰማለን።
ማንም ታጋይ መኖሪያውን በረሃ ላይ እንዲሆን የሚፈልግ የለም፡ ማንም ታጋይ ከሚወደው ቤተሰቡ እና ህዝቡ ተነጥሎ በበረሃ ላይ ከባዱን ኑሮ የሚፈቅድ ያለ አይመስለንም ፡ ማንም ታጋይ በአገሩና በህዝቡ ላይ ጥፋትና ጥቃት ሲፈጸም እያየ ዝም የሚል የለም በረሃ ወርደው አገርን ነጻ ለማውጣት የህብንም ጭቆናና መከራ  ደምሦሶ ለማጥፋት ብረት ያነሱት አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦነግ አንድ የሆኑበትን የጋራ መግለጫ አውጥቶተው እንደሚቀሳቅሱ ተስፋ አደርጋለሁ።
ህዝብን ነጻ ለማውጣት ለህዝብ እኩልነት ለማምጣት ለሚያስቡ እና የሚታገል ታጋይ ከዚህ የበለጠ ትልቅ አጋጣሚ ከወድየትም አይገኝም ።
እናም ታጋዮቻችን አንዱን ጥለን ሌላ ችግር ሊፈጥር የሚችረስ ውጭ እታገልለታለው ለሚለው ህዝብ ደግሞ የበለጠ መከራና ስቃይን እንዲገፋ የማድረግ መብት ለበዳዩ ወያኔ መፍቀድ እንዳይሆንብን አሁን ሰዓት ላይ ነንና በዜና አውታር በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ ነጻ ለማውጣት ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር የጋራ ጥምረት ፈጥረው በወያኔ ላይ የተቀናጀ ጥቃት ለመፈጸም እና ወያኔን ህዝባችን ላይ የበለጠ ጥፋትና ጥቃት ሳያደርስ ለምንወደውና ለምንታገልለት ህዝባችን ለመድረስ ደቂቃዋና ሰዓቷ አሁን ነውና ጥምረታችሁን በይፋ ለህዝብ ንገሩና ወያኔን መግቢያና መውጫ ምድረ ካድሬን ደግሞ የሚናገረውን እንዲያጣ በማድረግ ህዝባችንን እየገደለ እና ንብረታቸውን እያቃጠለ አማራውን ይሄንን ያደረገብህ ኦነግ ነው ብለው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እንዲነሳ የኦሮሞ ህዝብ እየገደለ እና ንብረቱንም እያቃጠለ ያለውን አማራ ነው ብለው የኦሮሞን ህዝብ አማራው ላይ እያነሳሳ የከሰረ 25 ዓመት ሲሰራበት የነበረውን ህዝብን ከህዝብ እያጣሉና እያፋጀ ስልጣኑን የማራዘም ስራ ሁሉም ህብረተሰብ በይፋ እንዲያውቀው ፖለቲካውን በበላይ የሚመሩት አካሎች ትልቅ ድርሻ አላቸው በተለይም ደግሞ ብረት አንስተው ስለህዝባቸው እና ስለ ሃገራቸው የሚታገሉት የፖለቲካ አመራሮች ለህዝቡ ነጻነት የናንተንም የበረሃ ላይ ትግል በአጭር ግዜ ወደ አሸናፊነት የሚያመጣችሁ አንድነት ሲኖራቸው ነውና የአንድነት ዜናዎችን በቅርቡ እንደምታሰሙን ተስፋ አለኝ።

በቅርቡ የምንሰማው ዜና በጥምር ተቀናጅተው ኦነግ እና አርበኞች ግንቦት 7 ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ወደፊት እየገሰገሱ ወያኔን መቆሚያ እያሳጡት ነው የሚለው ይሆናል። – መርጋ ደጀኔ (ከኖርዌይ)

ምከረው ምከረው እንቢ ካለ መከራ ይምክረው እንደሚሉት አበው 25 ዓመት ሙሉ ሲመከር ሲለመን ሲዘከር ምክርን እንደ ስድብ ልመናን እንደ ፍራቻ ዝክርን እንደ ማታለል አድርጎ በመቁጠር ዝም በሉ ዝም ካላላችሁ ዝም አደርጋችሃለሁ ረግጫችሁ እገዛችኋል አማራና ኦሮሞን አጋጭቶ በመሃል እኔ ስልጣኔን እያደላደልኩኝ 100 ዓመት እገዛለሁ ብሎ የቀየሰው ስልት ዛሬ በእርግጠኝነት መናገር ወደሚቻልበት ትግል የኢትዮጵያ ህዝብ  በመግባቱ ታውቋል። ኦነግና  አርበኞች ግንቦት 7 የተቀናጀ ድምጽ አሰምተውን ኦነግ በአሶሳ ፤በሀረር ፤በቦረና ወያኔን እየደመሰሰ ወደ ፊት እየመጣ ነው። አርበኞች ግንቦት 7 በጎንደር፤ በጎጃም ፤በደቦብ በድሬደዋና በመላው ኢትዮጵያ ብሎም በአዲስ አበባ ትግሉን በማቀጣጠል ወያኔን መቆሚያና መቀመጫ እያሳጡት ነው የሚለውን ዜና እንሰማለን።
ማንም ታጋይ መኖሪያውን በረሃ ላይ እንዲሆን የሚፈልግ የለም፡ ማንም ታጋይ ከሚወደው ቤተሰቡ እና ህዝቡ ተነጥሎ በበረሃ ላይ ከባዱን ኑሮ የሚፈቅድ ያለ አይመስለንም ፡ ማንም ታጋይ በአገሩና በህዝቡ ላይ ጥፋትና ጥቃት ሲፈጸም እያየ ዝም የሚል የለም በረሃ ወርደው አገርን ነጻ ለማውጣት የህብንም ጭቆናና መከራ  ደምሦሶ ለማጥፋት ብረት ያነሱት አርበኞች ግንቦት 7 እና ኦነግ አንድ የሆኑበትን የጋራ መግለጫ አውጥቶተው እንደሚቀሳቅሱ ተስፋ አደርጋለሁ።
ህዝብን ነጻ ለማውጣት ለህዝብ እኩልነት ለማምጣት ለሚያስቡ እና የሚታገል ታጋይ ከዚህ የበለጠ ትልቅ አጋጣሚ ከወድየትም አይገኝም ።
እናም ታጋዮቻችን አንዱን ጥለን ሌላ ችግር ሊፈጥር የሚችረስ ውጭ እታገልለታለው ለሚለው ህዝብ ደግሞ የበለጠ መከራና ስቃይን እንዲገፋ የማድረግ መብት ለበዳዩ ወያኔ መፍቀድ እንዳይሆንብን አሁን ሰዓት ላይ ነንና በዜና አውታር በዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ የኢትዮጵያን ህዝብ ከወያኔ ነጻ ለማውጣት ከአርበኞች ግንቦት 7 ጋር የጋራ ጥምረት ፈጥረው በወያኔ ላይ የተቀናጀ ጥቃት ለመፈጸም እና ወያኔን ህዝባችን ላይ የበለጠ ጥፋትና ጥቃት ሳያደርስ ለምንወደውና ለምንታገልለት ህዝባችን ለመድረስ ደቂቃዋና ሰዓቷ አሁን ነውና ጥምረታችሁን በይፋ ለህዝብ ንገሩና ወያኔን መግቢያና መውጫ ምድረ ካድሬን ደግሞ የሚናገረውን እንዲያጣ በማድረግ ህዝባችንን እየገደለ እና ንብረታቸውን እያቃጠለ አማራውን ይሄንን ያደረገብህ ኦነግ ነው ብለው በኦሮሞ ህዝብ ላይ እንዲነሳ የኦሮሞ ህዝብ እየገደለ እና ንብረቱንም እያቃጠለ ያለውን አማራ ነው ብለው የኦሮሞን ህዝብ አማራው ላይ እያነሳሳ የከሰረ 25 ዓመት ሲሰራበት የነበረውን ህዝብን ከህዝብ እያጣሉና እያፋጀ ስልጣኑን የማራዘም ስራ ሁሉም ህብረተሰብ በይፋ እንዲያውቀው ፖለቲካውን በበላይ የሚመሩት አካሎች ትልቅ ድርሻ አላቸው በተለይም ደግሞ ብረት አንስተው ስለህዝባቸው እና ስለ ሃገራቸው የሚታገሉት የፖለቲካ አመራሮች ለህዝቡ ነጻነት የናንተንም የበረሃ ላይ ትግል በአጭር ግዜ ወደ አሸናፊነት የሚያመጣችሁ አንድነት ሲኖራቸው ነውና የአንድነት ዜናዎችን በቅርቡ እንደምታሰሙን ተስፋ አለኝ።
ወያኔ አሁን እየተንቀሳቀሰ ያለው በመከላከያ ሰራዊቱ ውስጥ ያሉትን በተለይ ሁለቱን ብሄሮች የማጣላት ስራን ለመስራት ማንንም ሳያሳትፉ የሕወአት ሰዎች ብቻ ተሰብስበው መመሪያ አስተላልፈዋል። ከተላለፉት መመሪያ ውስጥ አደገኛውና በህዝባችን ጥፋት ላይ ያነጣጠረው በኦሮሚያ ክልል ውስጥ አማራ ያልሆኑ፡ ነገር ግን አማርኛ ተናጋሪዎችን በማስፈራራት አማረነታቸውን እየገለጹ  በኦሮሞ ህዝብ ላይ ጥላቻ እንዳላቸው እየተናገሩ ህዝቡን እንዲገሉ በማድረግ እና  የኦሮሞ ህዝብ በአማራው ላይ እንዲነሳ ..በአማራው ክልል ውስጥ የኦሮሞኛ ቃንቃ የሚናገሩ ነገር ግን ኦሮሞ ያልሆኑትን የመከላከያ ሰራዊት በማሰለፍ የአማራን ህዝብ በመጨፍጨፍ አማራን እንደሚጠሉ በመንገር በኦሮሞ ህዝብ ላይ እንዲነሱ የማድረግ ስራ ሰርተው ህዝባችንን ለመጨፍጨፍ ወያኔ የመጨረሻውን የመፍጨርጨር የሞት ሽረት ትግል ለማድረግ ቆርጦ ተነስታል።

Sunday, December 20, 2015

የአቡነ እንጦስ በኖርዌይ ቆይታ ሃይማኖታዊ ወይንስ ፖለቲካዊ ተልዕኮ?

በለንደን በማበጣበጥ የተባረሩት አቡነ እንጦስ ኖርዌይ ምእመንን ለመከፋፈል ገብተዋል ፤አስቸካይ እርምጃ የሚጠይቅ ጉዳይ ነውና አንብበው በንቃት ተሳተፉ!!! ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ10፣ቁጥር 1 ላይ ''እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው'' ዮሐ ምዕ 10፣1 ብሎ አስተምሮናል።ይህ ቃል የሚያስተምረን ትልቅ ቁም ነገር አለ።በሃይማኖታዊ ተግባር ላይ የተሰማሩ የሚመስሉ ነገር ግን ተግባራቸው የቆሙለትን የዘር ዘውግ ወይንም የንዋይ ጥማት ለማርካት ብቻ የሚፈልጉ አባት ያልሆኑ ነገር ግን በአባትነት ስም ቤተ ክርስቲያንን የሚያምሱ እንደሚነሱ ሲነግረን እነኝህ ሌባ ወንበዴ እንደሚባሉ እራሱ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል። [ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]Abune Entose in Norway
http://ecadforum.com/Amharic/archives/15986/የአቡነ እንጦስ በኖርዌይ ቆይታ ሃይማኖታዊ ወይንስ ፖለቲካዊ ተልዕኮ? '' በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው'' ዮሐ ምዕ 10፣1 በለንደን በማበጣበጥ የተባረሩት አቡነ እንጦስ ኖርዌይ ምእመንን ለመከፋፈል ገብተዋል ፤አስቸካይ እርምጃ የሚጠይቅ ጉዳይ ነውና አንብበው በንቃት ተሳተፉ!!! ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ ወንጌል ምዕ10፣ቁጥር 1 ላይ ''እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ወደ በጎች በረት በበሩ የማይገባ በሌላ መንገድ ግን የሚወጣ እርሱ ሌባ ወንበዴም ነው'' ዮሐ ምዕ 10፣1 ብሎ አስተምሮናል።ይህ ቃል የሚያስተምረን ትልቅ ቁም ነገር አለ።በሃይማኖታዊ ተግባር ላይ የተሰማሩ የሚመስሉ ነገር ግን ተግባራቸው የቆሙለትን የዘር ዘውግ ወይንም የንዋይ ጥማት ለማርካት ብቻ የሚፈልጉ አባት ያልሆኑ ነገር ግን በአባትነት ስም ቤተ ክርስቲያንን የሚያምሱ እንደሚነሱ ሲነግረን እነኝህ ሌባ ወንበዴ እንደሚባሉ እራሱ ፈጣሪያችን ኢየሱስ ክርስቶስ አስተምሮናል። አቡነ እንጦስ አገር ቤት በሚገኘው በወያኔ በሚታዘዘው ሲኖዶስ ስር ሆነው በእንግሊዝ የሚኖሩ ምእመናንን በከፍተኛ ደረጃ ሲያበጣብጡ ከርመው ወደ ኖርዌይ በበሩ ሳይሆን በሌላ መንገድ ማለትም ምእመናን ሳያውቁ እና ጥቂት የጥቅም እና የጎጥ ዘውግ ተጋሪዎች እንዲሰሙ ተደርጎ ገብተዋል።ኖርዌይ ከገቡም ቀናት አስቆጥረዋል።ለመሆኑ አንድ በሊቀ ጳጳስ ደረጃ ያለ አባት ከምእመናን ተደብቆ መግባት እና እራስን መሽሸግ ለምን አስፈለገ? በበር ለመግባት እና እንደ ሌባ ወይንም ወንበዴ እራስን መሰወር ለምን አስፈለገ? አቡነ እንጦስ በአገር ቤት ባሉ አባቶችም ጭምር በደህንነት ሰራተኛነት እንጂ በክህነት ስራቸው አይታወቁም አቡነ እንጦስ የታላቁን አባት የግብፁን ፃድቅ አባ እንጦስ ስም ይያዙ እንጂ ተግባራቸው ሌላ ነው። የአቡነ እንጦ

Saturday, December 19, 2015

Human Right Watch asks UN and AU to intervene on the current situation of Ethiopia - See more at: http://www.zehabesha.com/human-right-watch-asks-un-and-au-to-intervene-on-the-current-situation-of-ethiopia/#sthash.rGhtPCFt.dpuf

Obang-800x445Military Deployment, Terrorism Rhetoric Risk Escalating Violence
Ethiopian security forces have killed dozens of protesters since November 12, 2015, in Oromia regional state, according to reports from the region. The security forces should stop using excessive lethal force against protesters.Police and military forces have fired on demonstrations, killing at least 75 protesters and wounding many others, according to activists. Government officials have acknowledged only five deaths and said that an undisclosed number of security force members have also been killed. On December 15, the government announced that protesters had a “direct connection with forces that have taken missions from foreign terrorist groups” and that Ethiopia’s Anti-Terrorism Task Force will lead the response.

ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባቀረቡት ጥሪ ኢትዮጵያ ውሰጥ ያለው የአርበኞች ግንቦት 7 መዋቅር ቅድሚያ ሰጥቶ ሊተገበራቸው የሚገቡ ስድስት ተግራት።






አርበኞች ግንቦት 7 በሚከተሉት ስድስት ነጥቦች ዙርያ የተቀናጀ ትግል እንዲካሄድ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የትግል ጥሪ ያደርጋል።
1. በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች እየተካሄደ ያለው ትግል ከአሁኑ በተሻለ ተጠናክሮ እንዲቀጥል! ለዚህም በነኝህ አካባቢዎች ያለው የነኝህ ማህበረሰብ አባላት ብቻ ሳይሆን ባካባቢዎቹ የሚገኙ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ትግሉን በስፋት እንዲቀላቀሉ እንጠይቃለን! በትግሉ ሂደትም በአሮሞና በአማራ ሕዝብ መካከል የትግል አጋርነትና የግብ ተመሳሳይነት መኖሩን ማጉላት ይገባናል። በአሁኑ ሰዓት ግፉና ስቃዩ እጅግ ለበረታበት የኦሮሞ ሕዝብ “አለንልህ፣ ከጎንህ ነን” ማለትና በርግጥም ከጎኑ ተሰልፎ መገኘት ይኖርብናል።
2. በሌሎች ክልሎች ያሉ ኢትዮጵያውያን ትግሉን በያሉበት ባስቸኳይ እንዲቀላቀሉ ጥሪ እናደርጋለን! ሌሎች ክልሎችና አካባቢዎች የሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች በየአካባቢያቸው ባሉ የአስተዳደር በደሎችና የነጻነት ፍላጎት ላይ ያተኮሩ እንዲሆን ማድረግ ይገባል፤ ሆኖም ግን ለአካባቢያዊ ችግሮች ዘላቂ መፍትሄ ማግኘት የሚቻለው የአገራችን የፓለቲካ ሥርዓቱ ሲለወጥ ብቻ መሆኑ በትግሉ ሂደት ማሳየት ይጠበቅብናል!
3. የኢትዮጵያ መከላከያና ፖሊስ ሰራዊት እንዲሁም በያካባቢው ስርዓቱን እንዲያገለግሉ የተመለመሉ ሚሊሺያዎች ከኢትዮጵያ ህዝብ አብራክ የወጡ፤ ራሳቸውም የወያኔ አገዛዝ ሰላባ የሆኑ መሆኑን ሁሌም ማስታወስ ይገባል። አርበኞች ግንቦት 7 ይህ የኢትዮጵያ ሰራዊት በወንድሞቹ፣ እህቶቹና ወላጆቹ ላይ እንይተኩስ ይልቁንም አፈሙዙን በዚህ እኩይ ስርዓት ላይ እንዲያዞር በደተደጋጋሚ ጥሪ አድርጓል፤ አሁንም በዚህ ባስራ አንደኛው ሰዓት ይህንን ህዝባዊ ጥሪ በድጋሚ እናደርጋለን! በትግሉ ውስጥ የምትሳተፉ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን ጥሪ በየትግሉ አደባባይ ማስተጋባት፤ በጎናችን ለምናገኘው ጎረቤታችን፤ ዘመዳችን ወይንም ጓደኛችን ለሆነ የዚህ ያፈና መዋቅር አባል ሁሉ በተደጋጋሚ መንገር አንርሳ!
4. ለኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደህዴድና ህወሓት መካከለኛና አነስተኛ ካድሬዎች እንዲሁም ዝቅተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ለሆናችሁ ሁሉ! እናንተ ዛሬ ከሕዝብ ትግል ጎን ቆማችሁ ራሳቸሁንም ሆነ አገራችሁን መታደግ የምትችሉበት ወቅት መሆኑን እወቁ። ዛሬ የሕዝብን ጥሪ ሳትሰሙ ሥርዓቱን ለመታደግ ግፍ መፈፀማቸሁን ከቀጠላችሁ ነገ ዘራፊ አለቆቻቸሁ የዘረፉትን ለመብላት ሲሮጡ እናንተን የማያስጥሏችሁ መሆኑን መረዳት ለራሳችሁም ሆነ ለቤተሰባችሁ ዘለቄታዊ ጥቅም ይበጃል። አሁኑኑ ሰልፋችሁን አሳምሩ! ነገ አብሮአችሁ ከሚኖረው ህዝብ ጋር አትጣሉ! በትግሉ ውስጥ የምትሳተፉ ኢትዮጵያውያንም ከሕዝብ ትግል ጎን ለመቆም ለሚፈልጉ ለነኝህ ወገኖች መንገዱን አመቻቹላቸው!
5. ደም እየበዛ ሲሄድ ሀሞት እየመረረ እንደሚሄድ የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጊዜው ሳይመሽ ቢገነዘቡት ይበጃቸዋል! የኢህአዴግ ባለሥልጣናት አገራችን መመለሻ የሌለው ቀውስ ውስጥ ከመግባቷ በፊት እና የዘረፉትን ንብረት በሰላም ለመብላት በፍጹም የማይችሉበት ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት እየሄዱበት ያለውን የእውር ድንብር መንገዳቸውን ቆም ብለው እንዲያስቡ እንመክራቸዋለን! ለሀገራችን ችግሮች ፖለቲካዊ መፍትሄ ለመስጠት ወደ እውነተኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚያሻግር ሁሉንም ያሳተፈ ድርድር አሁኑኑ ቢጀምሩ ለራሳቸውም ላገሪቱም እንደሚበጅ ልናሳስባቸው እንወዳለን! ይህን ለማድረግ ደግሞ በቅድሚያ ሰላማዊ ሰዎች መግደልና ማፈንን በአስቸኳይ እንዲያቆሙ፤ የፓለቲካ እስረኞችን በሙሉ ባስቸኳይ እንዲፈቱና አፋኝ ህጎችን በመሰረዝ ለእንዲህ አይነት ሰላማዊ ሽግግር ዝግጁ መሆናቸውን በተግባር እንዲያሳዩ እንጠይቃቸዋለን!
6. በመጨረሻም በመሳሪያም ሆነ በሌላ መንገድ ለዴሞክራሲያዊ ሥርዓት የሚታገሉ ኃይሎች ሁሉ እንዲሰባሰቡና ይህን ስርዓት ለማንበርከክም ሆነ በይበልጥም ከዚህ ስርዓት ባሻገር የጋራ ቤታችን የሆነችውን ኢትዮጵያ አገራችንን በእውነተኛ እኩልነት፤ በፍትህና በዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንደገና የምትታነጽበትን መንገድ በጋራ ለመተለም ባስቸኳይ ውይይት እንዲጀመር ጥሪ እናደርጋለን!.
ዶር/ታደሰ ብሩ

ወያኔዎች በግራ የተደገፉት ከዷቸው በቀኝም የተመረኮዙት ጣሏቸው ወደኋላ እንዳይመለሱ የተከሉት እሾህ ወጋቸው ወደፊትም እንዳይጓዙ የቆፈሩት ጉድጓድ አስፈራቸው ወደላይ ቀና እንዳይሉም አምላክ ይፈርድባቸዋል። – ከተማ ዋቅጅራ

ወያኔዎች በግራ የተደገፉት ከዷቸው በቀኝም የተመረኮዙት ጣሏቸው ወደኋላ እንዳይመለሱ የተከሉት እሾህ ወጋቸው ወደፊትም እንዳይጓዙ የቆፈሩት ጉድጓድ አስፈራቸው ወደላይ ቀና እንዳይሉም አምላክ ይፈርድባቸዋል። – ከተማ ዋቅጅራ

Friday, December 18, 2015

Demonstration In Oslo Decemeber 18

በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ አደረገ

በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ አደረገ
በዛሬው እለት በኖርዌይ ኦስሎ 18, December, 2015 (ታህሳስ 8, 2008 ዓ.ም ) በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን የወያኔ መንግስት በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ያደረሰውን ግድያ እና በምዕራብ ኢትዮጵይ በጎንደር ክልል ለሱዳን ተላልፎ የሚሠጠውን መሬት ምክንያት በመቃወም ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ፣ ኦስሎ ተደረገ ።
ይህንንም ተከትሎ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አዘጋጅነት ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ በኦስሎና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች የድጋፍ ድርጅቱ ባደረገላቸው ጥሪ መሰረት ሰልፉ በተጀመረበት ቦታ በመገኛት በግፍ ለሞቱት የኦሮሞ ተማሪዎች ዘረኛውና አንባገነኑ የወያኔ መንግስት በመቃወም ድምጻቸውን አሰምታዋል ::
ሰላማዊ ሰልፉ በኖርዌይ የሰአት አቆጣጠር ከቀኑ 14:00 ጀምሮ እስከ 15:30 የተደረገ ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተገኙ ኢትዮጵያኖች በሰላማዊ መንገድ ጥያቄያቸውን ሲጠይቁ በነበሩ የኦሮሞ ተማሪዎች ላይ ጥይትን በማዝነብ ኢሰብሃዊ ድርጊት የፈጸመውን ግድያ እንዲሁም ለሱዳን ያለ አግባብ በሚስጥር ተላልፎ ሊሠጥ ስለታሰበው መሬት የተነሳ በጎንደር ሕዝብ ላይ እየተደረገ ያለውን የዘር ማጥፋት ወንጀል እና በጎንደር እስር ቤት ውስጥ ለተገደሉ ወገኖቻችን በመቃወም ቡዙዎችን የገደለውን የወያኔን መንግስት የሚያወግዙ የተለያዩ መፈክሮችን በማያዝ እና በማሰማት ተቃውሞቸውን በሀይል ገልጸዋል::
በሰልፉ ላይ ሰልፈኞቹ ያሰሟቸው ከነበሩ

Thursday, December 17, 2015

ትግላችንን ተጠናክሮ በአንድነት ይቀጥል! December 17, 2015


def-thumb
የኢትዮጵያ ህዝብ ለመብቱ በያቅጣጫው መነሳቱ የሚያኮራ ነው። ባለፉት 3 ዓመታት ብቻ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ያደረጉትን የመብት ትግል ጨምሮ በደቡብ፣ አማራ፣ አፋር፣ ጋምቤላና በሌሎችም አካባቢዎች በርካታ የነጻነት ትግሎች ተካሂደዋል። አሁን በኦሮምያ እና በአማራ በተለይም በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች እየተካሄዱ ያሉት የነጻነት ትግሎች የአጠቃላዩ የነጻነት ትግል አካሎች ናቸው። በእነዚህ የነጻነት ትግሎች ገዢው ፓርቲ ከህዝብ ጋር ለምንጊዜውም መለያየቱን ለማየት ችለናል። ስልጣኑን ለማስጠበቅ ሲልም፣ አቅሙ ቢፈቅድለትና ማግኘት ቢችል በምድር ላይ ያሉትን ጅምላ ጨራሽ መሳሪያዎችን ሁሉ በገዛ ህዝቡ ላይ ለመጠቀም ወደ ሁዋላ የማይል የአረመኔዎች ስብስብ መሆኑን አረጋግጠናል። በጭካኔውና በፍርሃቱ ብዛት የተነሳ በርካታ ሙስሊሞች፣ ክርስቲያኖች፣ መብታቸውን በሰላም ለመጠየቅ ወደ አደባባይ የወጡ ወጣቶች ተገድለዋል፤ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎችና ጋዜጠኞች በእስር ተንገላተዋል፤ በእስር ቤትም ማንነታቸውን ከማዋረድ ጀምሮ የተለያዩ አካላዊ ጥቃቶች ተፈጽሞባቸዋል።

Wednesday, December 16, 2015


በኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
ኢሳት (ታህሳስ 6 2008)
ከሶስት ሳምንታት በፊት በምዕራብ ሸዋ ጊንጪ ላይ የተጀመረውና በመላው ኦሮሚያ ክልል የተቀጣጠለው ተቃውሞ ከአዲስ አበባ 60 ኪ/ሜ ጊንጪ ተባብሶ መቀጠሉን ብሉምበርግ ዘገበ። 
የብሉምበርግ ዘጋቢ ዊሊያም ዴቪድሰን ከስፍራው እንደዘገበው መንገድ ተዘግቷል፣ የመንግስት ሃይሎችን ጥቃት በማውገዝ፣ በሺ የሚቆጠሩ ፈረሰኞች ወደሆለታ ከተማ ተንቀሳቅሰዋል። 
የአዲስ አበባና ኦሮሚያ ልዩ ዞን ማስተር ፕላን አርሶአደሮችን ያፈናቅላል፣ ህገመንገስቱን ጭምር ይጻረራል በሚል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጀመሩትና ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል እያካተተ የቀጠለው ተቃውሞ፣ በተለይ በአዲስ አበባ አቅራቢያ እየተጠናከረ መገኘቱ የዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ትኩረት ስቧል። 
በአዲስ አበባና በአምቦ መካከል የምትገኘውና ከአዲስ አበባ በ60 ኪሎሜትር ላይ የምትገኘው ወለንኮሚ ከተማ 4 ሰላማዊ ሰዎች ትናንት መገደላቸውን ከስፍራው የዘገበው የብሎምበርግ ዊሊያም ዴቪድሰን፣ ከተማዋ በመከላከያ ሰራዊት መያዟን ገልጿል። 
ሰው ተደብቆ እንደሚገኝና በየሰከንዱ የማያቋርጥ ተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ የገለጸው ዊሊያም ዴቪድሰን፣ ከጤና ጣቢያና ትምህርት ቤት በስተቀር ሁሉም ተቋማት ላለፉት 4 ቀናት በሰልፈኞቹ ተይዘው መቆየታቸውን ጽፏል። 
የቶታል ነዳጅ ማደያ ተሳቢ መኪናን እንዲሁም የዳሸን ቢራ ፋብሪካ የጭነት መኪና በመጠቀም ወደ አምቦ የሚወስደውንና ወደ አዲስ አበባ የሚወስደውን መንገድ የዘጉት ሰልፈኞች የቀበሌ ፅ/ቤት ጠረጴዛዎችንና መደርደሪያዎችን ጭምር ለመንገድ መዝጊያነት እንደተጠቀሙ ከስፍራው ተዘግቧል። 
ይህ በእንዲህ እንዳለ በኦሮሚያ ክልል ተባብሶ የቀጠለውንና ብዙዎችን እየተገደሉበት ሁኔታ ያስቆጣቸው የሜታ ሮቢ ፈረሰኞች ዛሬ ረቡዕ ወደ ሆለታ ተንቀሳቅሰው ተቋውሟቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ወደ አዲስ አበባ ለመንቀሳቀስ ሞክረው እልቂት ይከሰታል በሚል ማግባቢያ መመለሳቸው ተወስቷል። 
በኢትዮጵያ በኦሮሚያ ክልል በተቀጣጠለው ህዝባዊ ቁጣ የመንግስት ሃይላት የአጸፋ ጥቃት የቀጠለ ሲሆን፣ ህዝባዊ እምቢተኝነትቱም ጨምሯል። እሳት እየተከታተለ ዝርዝሩን ያቀርባል።
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
====================================================
‪#‎የህወሓት‬ አገዛዝ ከፍተኛ ባለስልጣናት በዛሬው ዕለት በጎንደር ወረዳዎች ከህዝቡ ጋር ሲያደርጉት የዋሉት ስብሰባ ያለምንም ውጤት ተበተነ፡፡
====================================================
በእነ አባይ ፀሐዬ እና በረከት ስምዖን እየተመራ ከአዲስ አበባ ጎንደር የገባው የአገዛዙ ከፍተኛ ሹሞች ልዑክ በጎንደር ከተማ፣ በመተማ ሸዲ፣ በጭልጋ እና በአርማጭሆ ከህዝብ ጋር ያደረገው ስብሰባ የባሰውኑ ተስፋ እንዲቆርጥ አድርጎታል፡፡ በተለይም የመተማ ሸዲ ህዝብ "ቅማንትና አማራ ብላችሁ ከፋፍላችሁ እርስበርስ ልታጫርሱን ከመቀሌ የጦር መሳሪያ አስጭናችሁ አምጥታችሁ አከፋፍላችኋል..." በማለት በጥያቄ አፋጧቸዋል፡፡ 
በመጨረሻም ህዝቡ "እኛ የአርበኞች ግንቦት 7 ደጋፊዎች ነን!" ሲል በአንድነት አቋሙን ገልፆ ከስብሰባው ፈርሶ ወጥቷል፡፡.
ሰበር ዜና በጎንደር!
የህወሃት ሰዎች ጎንደርን አጥለቅልቃዋታል።
እነ በረከተ መርገምት እና እነ ደመቀ መኮነን እንዲሁም ሌሎች ባለስልጣናት የሚመራ ብዛታቸው ሰባት የሚሆኑ ልዑካን ወደ መተማ ከተማ ትናንት ከቀኑ ሰባት ሰዓት ላይ ሂደዋል በስምንት የፌዴራል ፓሊስ ፓትሮል እየታጀቡ አቅንተዋል ። ከሱዳን ጋር በተሸጠው መሬት ሊመክሩ እንደሆነ የውስጥ አዋቂ በሆኑ ሰዎች መረጃው ደርሶኛል ። በዚህ ጉዳይ ላይ የመተማ ከተማ እና የሸህዲ ከተማ ነዋሪዎች በግፍ በጭነት አውሱዙ እየተጫኑ ወደ ጎንደር ከተማ በመግባት ላይ ይገኛሉ ።
ግጭቱ እንደ ቀጠለ ነው ።
አራት የቀይ መስቀል አንቡላንሶች እና ሁለት የመንግስት አንቡላንሶች በፍጥነት እየነዱ ወደ መተማ ከተማ አምርተዋል ።
በተያያዘ በሁሉም ከተሞች ሽምግልና ሲካሄድ የሰነበተ ሲሆን አሁን ላይ ሁሉም በአንድነት አፈሙዛቸው ወደ ህወሃት በማዞር ህወሃትን በመግጠም ላይ ይገኛሉ ። በቆራ ከተማ፣ በሽንፋ ከተማ ፣ በመተማ ከተማ፣ እና በሽህዲ ከተማ ላይ የህወሃት ሰላይ እና ካድሬ ናቸው ብሎ ህዝቡ በጠረጠራቸው ሰዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ ላይ ይገኛል ። ሁለት ትግሬዎች ሲገደሉ ከሃያ በላይ የሚሆኑ ትግሬዎች ወደ እስር ተግዘዋል እስር ቤታቸውም የተሰወረ እንደሆነ ከተለያዮ ሰዎች በስልክ ለማረጋገጥ ችያለሁ። በትግሬዎች ላይ የተነሱበት ዋና ምክንያታቸው የሆነው ለህወሃት ትሰልላላችሁ በሚል እና አንዳንድ ካድሬዎች መረጃ ሲያቀብሉ እና ህዝቡን ወደ እርስ በዕርስ ግጭት የመሩትን እየፈለገ ድባቅ እየመታቸው ይገኛል ። ንብረታቸውንም በማውደም እና በማቃጠል እንዲሁም በመዝረፋ ላይ ይገኛል ። በተለይም ብዛት ያላቸው ሱቆች ፣ ቡቲኮች እንዲሁም ሆቴሎች በከፍተኛ ሁኔታ የተጠቁ ናቸው።ይህን እየፃፍኩ ባለበት ሰዓት ትግሬ የተባለ ከተገኘ እርምጃ እየተወሰደባቸው ይገኛል.
Adjama Dejene's photo.
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
‪#‎በጎንደር‬ የሚገኙት የህወሓት አገዛዝ ከፍተኛ ባለስልጣናት በአሁኑ ሰዓት ለሁለት ተከፍለው ወደ መተማ ሸዲና አርማጭሆ አቅንተው ህዝቡን በመማፀን ላይ ናቸው፡፡
====================================================
በትናንትናው ዕለት በጎንደር ጎሃ ሆቴል በነበረው ስብሰባ ላይ ገዱ አንዳርጋቸው የጎንደር ህዝብ በስርዓቱ ላይ ማመፁን ባፋጣኝ የማያቆም ከሆነ የክልሉ ልዩ ኃይል እና ፌደራል ፖሊስ ጦር ተቀናጅተው የማያዳግም የኃይል እርምጃ እንደሚወስዱ እሱ የሚመራውን ክልል አስተዳደር አቋም አስታውቋል፡፡
በዛሬው ዕለት አባይ ፀሐዬ፣ ደመቀ መኮንን እና አምባቸው /የክልሉ ምክትል አስተዳዳሪ/ ወደ መተማ ሸዲ አምርተው በቦታው ያገኙትን ጥቂት ህዝብ ከአንገት በላይ የሆነ ጉንብስ ለመዋረድ እየጣሩ ይገኛሉ፡፡
በተመሳሳይ ሁኔታም እንዲሁ በረከት ስምዖን፣ ገዱ አንዳርጋቸው፣ ሙሉጌታ ወርቁ /የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር/ እና የክልሉ ልዩ ሃይል አዛዥ የሆነው ሰው ወደ አርማጭሆ ዘልቀው ከህዝብ ጫማ ስር በመውደቅ ላይ ናቸው፡.

፡.

Tuesday, December 15, 2015

ሰሞኑን በሃገራችን የተለያዩ ግዛቶች በኢትዮጵያዉያን ላይ እየደርሰ ያለዉ ጥቃት ከመቼዉም ጊዜ በላይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሶአል።ሕዝባችን ይኸዉ ከወያኔ የሚደርስበትን ጥቃት በመቋቋም ተቃዉሞዉንና አልገዛም ባይነቱን በገሃድ በተለይ በመላዉ ኦሮሚያና በጎንደር የተለያዩ ወረዳዎች እያሳየ ይገኛል።


ይህ የወገኖቻችን የአልገዛም ባይነትና የዲሞክራሲያዊና ሰብዓዊ መብት ጥያቄዎችን ህወሃት/ወያኔ በተለመደዉ የእብሪተኛ ድርጊቱ የሕዝቡን ድምጽ ለማፈን ተማሪዎች በሚማሩበት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶችና ዩንቨርስቲዎች ድረስ ዘልቆ በመግባት በመግደል፤በመደብደብና በማሰር የሕዝቡን ቁጣና ብሶት በሃይል ለማፈን ቢሞክርም ዉጤት ሳያገኝ ማፈን ከማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሶአል።ተቃዉሞዉም ከእለት ወደ እለት እየተባባሰ የሄደ ሲሆን የወያኔም ጥቃት ከእለተ ወደ እለት አስከፊ ደረጃ ላይ እየደረሰ ይገኛል።
የአዲስ አበባን ከተማን ለማስፋት በሚል ህወሃት/ወያኔ ድብቅ አጀንዳዉን ከአንድ ዓመት በፊት ባቀደዉ የማስተር ፕላን በርካታ ወገኖቻችን ለሞት፤ እንግልትና እስር ምክንያት በመሆን ሂደቱ ቢጠናቀቅም በእብሪት የተሞሉት የህወሃ/ወያኔ ዘረኛ ቡድን እናስተዳድርሃለን በሚሉትና በኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ነዉ የተመረጥነዉ የሚለዉን ሕዝብ ምርጫዉ ባለቀ ማግስት የዘረኛ መሪዎቹ ቁንጮ በማን አለብኝነት ማስተር ፕላኑን የሚቃወሙትን ልክ እናስገባችኋለን በማለት በአደባባይ ለሕዝባችን ያላቸዉን ጥላቻና ንቀት በግልጽ አሳይተዋል።
እብሪተኛዉ የህወሃት/ወያኔ ቡድን ይህን ማስተር ፕላን የሚለዉን እቅድ ከመነሻዉ የቀደዉና የነደፈዉ እዉነት የከተማዋ መስፋት አስፈላጊነት ለሕዝቡ የሚሰጠዉ ጥቅምና ጉዳቱ ሕዝብ ተወያይቶበትና መክሮበት ሳይሆን በሙስናና ብልሹ አሰራር ለተዘፈቁት የህወሃት ሹመኞችና የእነሱ ቡችሎች በከተማዋ በሕገወጥ መንገድ ከያዙት ንብረት በተጨማሪ ሌላ ንብረት ለማስገኘት ሆን ተብሎ ታስቦ የተሸረበ ድብቅ ሴራ እንደሆነ ድርጅታችን ያምናል። ህወሃት/ወያኔ ትላንት በአቃቂ በሚገኙት የአቡ ጨፌ፤ገላን፤ቂሊንጦና ቀርሳ እንዲሁም በቦሌ ቡልቡላ የረር በርና ጎላ ሰፈር የነበሩትን ወገኖቻችንን በማፈናቀል የፈጸሙት በደልና የዘር ማጥፋት ድርጊት ቁስላችን ሳይሽር በድጋሚ ይህንኑ ለመፈጸም የሚደረገዉን ሕገ ወጥ ድርጊት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በፅኑ ሊያወግዘዉ ይገባል። 
በሌላ በኩል በዘረኛነትና የተለከፈዉ ሥልጣን በሃይል የያዘዉ የህዋሃት/ወያኔ ቡድን በሕግ ጥላ ስር በጎንደር እስር ቤት ታስረዉ በሚገኙ ወገኖቻችን ላይ በእስር ቤቱ ላይ በተነሳዉ የእሳት ቃጠሎ እስረኛዉ የታሰረበትን ክፍል በመቆለፍ በእሳት ያስፈጃቸዉ ሲሆን ከእስር ቤቱ ሕይወታቸዉን ለማትረፍ የሚወጡ እስረኞችን ዙሪያዉን ከቦ በጥይት ፈጅቷቸዋል። ይህ የወያኔ ድርጊት በሁለተኛዉ የዓለም ጦርነት ወቅት ፋሺስቶች እንኳን ያልፈጸሙትን ይህ ዘረኛ ቡድን በወገኖቻችን ላይ ይህን አሰቃቂና የጭካኔ ድርጊት ፈጽሞአል።
(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)
‪#‎የአርበኞች‬ ግንቦት 7 ሰራዊት በዛሬው ዕለት መተማ አካባቢ በህወሓት የመከላከያ ኃይል ላይ ድንገተኛ የሽምቅ ውጊያ ጥቃት ከፍቶ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ፡፡
====================================================
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት ሰሞኑን በዋል ድባ እና በአድ-እርቃይ ተከታታይ የሽምቅ ውጊያ እንቅስቃሴዎችን አድርጎ የህወሓትን መከላከያ፣ ፌደራል ፖሊስና ሚሊሻ ኃይል በገፍ በመግደልና በማቁሰል ክፉኛ አሽመድምዶታል፡፡ 
ዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈፀመው ለሚገኘው ጭፍጨፋ የአፀፋ እርምጃ መተማ አካባቢ ተከማችቶ በሚገኘው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የመከላከያ ኃይል ላይ ዛሬ ከሰዓት በኋላ መጠነ ሰፊና የተቀናጀ የሽምቅ ውጊያ ጥቃት ከፍቶ በሰው ኃይል፣ በትጥቅና ስንቅ ላይ እጅግ በጣም የከፋ ጉዳትና ኪሳራ አድርሷል፡፡ 
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በዛሬው ዕለት በህወሓት አገዛዝ ላይ በወሰደው ከባድ እርምጃ ከቀኑ 8፡00 እስከ 10፡00 ሰዓት ለሁለት ተከታታይ ሰዓታት በመተማ አካባቢ ሰፍሮ የቆየውን የመከላከያ ኃይል እያራወጠ በእሳት በትር ገርፎታል፡፡ 
የአርበኞች ግንቦት 7 ሰራዊት በመተማ ወረዳ በዘረኛውና ፋሽስቱ የህወሓት አገዛዝ መከላከያ ኃይል ላይ በወሰደው እርምጃ የህዝብ ወገን መሆኑን እንዳስመሰከረ የአካባቢው ነዋሪዎች በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ‪#‎የህወሓት‬ ከፍተኛ ባለስልጣናት በትናንትናው ዕለት ወደ ጎንደር ከተማ አምርተው ከዞኑ የካቢኔ አባላትና ከአንዳንድ የስርዓቱ ደጋፊ የሆኑ የከተማው ነዋሪዎች ጋር በጎሃ ሆቴል ውይይት ለማድረግ ሞክረው ጠንከር ያለ ተቃውሞና ውርደት ገጥሟቸዋል፡፡ ====================================================


ከአዲስ አበባ ጎንደር የገቡት የአገዛዙ ባለስልጣናት የህወሓቱ አባይ ፀሀዬ፣ የህወሓት ተላላኪ የሆነው ብአዴን ቁንጮዎች በረከት ስምዖንና አዲሱ ለገሰ ናቸው፡፡ የክልሉ ሹም ገዱ አንዳርጋቸውም በአጃቢነት ተገኝቷል፡፡
አባይ፣ በረከትና አዲሱ በትናንትናው ዕለት የዞኑን ካቢኔ አባላትና ጥቂት የስርዓቱ ደጋፊ የሆኑ የከተማው ነዋሪዎችን በጎሃ ሆቴል ሰብስበው በጎንደር ስለሰፈነው አለመረጋጋት፣ አመፅና ጦርነት ለማነጋገር ሞክረው "ይህ ሁሉ ችግር ከደረሰና ሁኔታው ከቁጥጥር ውጭ ከሆነ በኋላ ምትመጡ እስከ ዛሬ የት ነበራችሁ? የህዝብ ቁጣ ጫፍ ደርሷል አሁን እናንተ መጣችሁ አልመጣችሁ የምትፈይዱት ቅንጣት ታክል ነገር የለም..." የሚል ምላሽ ያለበት ከወትሮው ለየት ያለና ጠንካራ ተቃውሞ ከተሰብሳቢው ተሰንዝሮባቸዋል፡፡ በተለይም በባለስልጣናቱና በካቢኔው መካከል የተፈጠረው እሰጣገባና ንትርክ ወደ ከረረ ያለመግባባት ውስጥ እንደከተታቸው ታውቋል፡፡
እነበረከትና አባይ የጎንደርን ነዋሪዎች በየክፍለ ከተማው ሰብስበው ለማነጋገር መድረክ እንዲያመቻቹላቸው የዞኑን ካቢኔ አባላት ጠይቀው የካቢኔ አባላቱ በአሁኑ የትኩሳት ወቅት ህዝብ መሰብሰብ ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ እና ባለስልጣናቱ ራሳቸው ወርደው ያሻቸውን ማድረግ እንደሚችሉ ቁርጥ ያለ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በመሆኑም እነ በረከትና አባይ ፀሀዬ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ወድቀው የሚያደርጉት ጭንቅ ጥብብ ብሏቸው አሁንም በጎንደር ከተማ ጎሃ ሆቴል ውስጥ ይገኛሉ፡፡