የሱዳን ዕለታዊ ጋዜጣ የዕለተ አርቡን የማለዳ ወረራ በማስመልከት ባቀረበው የዜና ዘገባ ወረራውን በመፈጸም የጅምላ ግድያ የፈጸሙት ከደቡብ ሱዳን ቡማ ክልል የተነሱ የሙልሬ ጎሳ አባላትና በመንግስት ወታደሮች ታግዘው መሆኑን ቢያወሳም ሳተናው ያጋገረቻቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ወራሪዎቹ ሱዳናዊያን መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡
ለወራሪዎቹ የጭካኔና ድንገተኛ ወረራ ምላሽ ለመስጠት በሚያስችላቸው ዝግጁነት ላይ ያልነበሩት ኢትዮጵያዊያኑ ባልሞት ባይ ተጋዳይነት ባደረጉት የመልስ ምት 70 ሱዳናዊያንን መረፍረፋቸውን የመረጃ ምንጮቻችን ይጠቁማሉ፡፡፡
ሱዳን ትሪቡን በዘገባው በህይወት መትረፍ የቻሉትን አንድ የኑዌር ነዋሪ መጠየቁን በመግለጽ ‹‹ሰዎቹ የሙርሌ ማህበረሰብ አባላት መሆናቸውን ከተገደሉት ሰዎቻቸው ማረጋገጥ ችለናል፡፡ከ170 በላይ ሰዎቻችንን ገድለውብናል፡፡ከተገደሉት ውስጥ የሚበዙት ሴቶችና ህጻናት ናቸው፡፡ብዛት ያላቸውን ልጆችም አግተው ወስደውብናል፡፡ወራሪዎቹን መከላከል ለእኛ በጣም አስቸጋሪ ነበር ምክንያቱም መሳሪያ አልነበረንም፡፡ሙርሌዎች የመጡት በከፍተኛ ደረጃ ታጥቀውና የደቡብ ሱዳንን የወታደሮች ዩኒፎርም ለብሰው ነው››ማለቱን አስፍሯል፡፡
ወረራው የተካሄደበትን መንደሮች የሚያስተዳድረው የጋምቤላ ክልል መንግስት የድረሱልን ጥሪ ቢደረግለትም ያልታጠቁትን ኑዌሮች ሊያስጥላቸው አልቻለም፡፡በአካባቢው ግጭቶችና ድንገተኛ ጥቃቶች ሲሰነዘሩ የአሁኑ የመጀመሪያው ባይሆንም የዕለተ አርቡ የሱዳኖች ወረራ በወታደራዊ ኃይል የታገዘና ብዙዎች ለሞት የተዳረጉበት በመሆኑ ከፍተኛው በመሆን ይተቀሳል፡፡
የሱዳናዊያኑ ወረራ፣የጅምላ ግድያ፣አፈና እና ዘረፋ ከተከናወነ 24 ሰዓታት ያለፉ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ የክልሉ መንግስት ምንም አይነት መግለጫ አለመስጠቱ ታውቋል፡፡
No comments:
Post a Comment