Saturday, April 9, 2016

ጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ ሰላማዊ ሰልፍ?ወይስ ሽብር?


“ወልቃይት የትግራይ ነው!” የሚል “ሰላማዊ” ሰልፍ ላይ አንዳንድ የዳንሻ ከተማ እናቶች እንዲህ ክላሽ ይዘው ነበር የወጡት።
ተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲሁም የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሲያደርጓቸው በነበሩ ሰልፎች “ ኮከብ የሌለው ባንዲራ ይዛችሁ ወጥታችኋል” በማለት አገር ይያዝልኝ ሲል የሰማነው ከህግ በላይ የኾነው ገዥ ፓርቲ፤ እነኚህን እናቶች ክላሽ አስጨብጦ ሰልፍ አስወጥቷል። (ይች ክላሽ በተቃዋሚዎች ሰልፍ ላይ ብትታይ ይሠራባት የነበረውን ዶክመንተሪ አስቡት።) በሰላማዊ ሰልፍ ሽፋን ፦ «ጠብ ያለሽ በዳቦ…” እያሉ የሚፎክሩ የሚመስሉ ሰዎች፦ ሌላውን ነዋሪ ለነገር በጫሩበትና ባስፈራሩበት(ባሸበሩበት) በዚህ ሰልፍ ላይ ግጭት ቢከሰት ኖሮ ፤ እየተመረጡ ይታሰሩ ወይም ይገደሉ የነበሩት እነማን ይሆኑ እንደነበር ግልጽ ነው። ተጋብቶና ተዋልዶ በፍቅር በኖረ ህዝብ መካከል የዚህ ዐይነት እሣት መጫርስ ዕብደት ካልሆነ በስተቀር ምን ይባላል?

No comments:

Post a Comment