Wednesday, April 6, 2016

የግድያው ተዋናይ መለስ ዜናዊ ናቸው ያሉት የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕ/ት ጥፋተኛ ተባሉ



ልክ የመን አንዳርጋቸው ጽጌን ሕወሓት ለሚመራው መንግስት አሳልፋ እንደሰጠችው ሁሉ የደቡብ ሱዳን መግስትም አቶ ኦኬሎ አኳይን ለዚሁ መንግስት አሳልፎ መስጠቱን በተደጋጋሚ በዘ-ሐበሻ ላይ ስንዘግብ ቆይተናል::
ዛሬ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው የኖርዌይ ዜግነት እንዳላቸው የሚነገረው የቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ኦኬሎ አኳይ በተከሰሱበት የሽብር ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል::
በአኙዋክና ኑዌር ጎሳዎች መካከል ከተፈጠረው ግጭት ጋር ተያይዞ ከሀገር የተሰደዱት አቶ ኦኬሎ፣ የብዙዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት የተቀናበረውና በግድያውም የተሳተፉት የመንግስት ወታደሮች እንደነበሩ ለተለያዩ የዜና አውታሮች መግለፃቸው ይታወሳል።
ከአቶ ኦኬሎ ጋር በአባሪነት የከሰሱ ሌሎች 5 ግለሰቦችም ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን የካንጋሮው ፍርድ ቤት ውሳኔ ለመስጠት ከ20 ቀናት በኋላ ቀጥሯቸዋል ተብሏል::
አቶ ኦኬሎ የጋቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳደር በነበሩበት ወቅት ከ 400 በላይ ሰዎች በመንግስት ወታደሮች በግፍ ተገለው 60 ሰዎች ብቻ ናቸው እንድል ታዝዤ ፍቃደኛ ሳልሆን ቀርቻለው ማለታቸውን; ከ 10 አመት በፊት የተፍፀመውን ግድያ ዋነኛ ተዋናዮች አቶ መለስ ዜናዊ አቶ አዲሱ ለገሰና አቶ በረከት ስምዖን እንደሆኑና በዛን ግዜ የፌደራል ፖሊስ ጉዳዮች ሚንስትር ዴኤታ የነበሩት ዶክተር ገብረአብ ባላባራስ ወንጀሉን በቀዳሚነት አስፍፃሚ እንደነበሩ በፍርድ ቤት የክስ ክርክር ወቅት መናገራቸውን ዘ-ሐበሻ መዘግቧ አይዘነጋም:
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/53061ኦኬሎ አኳይ

No comments:

Post a Comment