Monday, April 25, 2016

ሰበር ዜና.... በመከላከያ ሰራዊቱ ላይ ሙሉ ለሙሉ እምነቱ እየተሸረሸረ የሚገኘዉ የትግራይ ነጻ አዉጪ ቡድን እራሱን በራሱ እየበላ ይገኛል ።


 
ባሳለፍነዉ ሳምንት የመከላከያ ሚኒስቴር መዳፍ የሆነዉ ወታደራዊ ፍርድ ቤት በመካከለኛዉ እዝ እና በሰሜኑ እዝ ዉስጥ ለረጅም አመታት ያገለገሉ ሌተናል ኮረኔል ማእረጉ እና ሻምበል ዳርጌ በተባሉ መኮንኖችን ላይ በተደጋጋሚ በቀረበባቸዉ መረጃ በማዉጣና መመሪያዎችን በአግባቡ ባለመፈጸም እንዲሁም የመከላከያ አባላትን በብሄር በመከፋፈል በሚል ክስ ተንተርሶ በቁጥጥር ስር እንዲዉሉ አድርጓል ።
በተለይም በሰሜኑ እዝ ዉስጥ ከፍተኛ አለመተማመን እንዲሰፍን እና የሚከዱ ወታደሮች በተበራከቱበ በዚህ አጣብቂኝ ወቅት ላይ ይጠፋሉ ተብለዉ የተጠረጠሩ አባላትን አስታጥቆ ዋርድ ( የዝውዉር ጥበቃ ) ሆን ብሎ በመላክ ለበርካታ አባላቱ መክዳት ምክንያት ነዉ በተባለ አንድ ተጨማሪ የሰሜኑ እዝ መኮንን ላይ ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ክስ ለመመስረት ደፋ ቀና በማለት ላይ መሆኑን ምንጫን አክሎ ጠቅሷል።
በተያያዘ መረጃ በሶማሌያ የነበረዉን የ 43ተኛ ክፍለ ጦር ይዘዉ ወደ ሐገር ቤት በመግባት ከሰራዊቱ የተሰናበቱት እና በአሁኑ ወቅት በአስመጪና ላኪ የንግድ ስራ ላይ ተሰማርተዉ ሚሊየነር ባለሐብት የሆኑት ኮረንል ወዲ አባተ ላይ የቀረበዉን የአስተዳደር ብክለትና የጦር ወንጀል ክስ ወታደራዊ ፍርድ ቤቱ ዉድቅ አስርጎታል።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ ! !
( ጉድሽ ወያኔ )

No comments:

Post a Comment