Tuesday, April 26, 2016

በቅርቡ ከእስር ለተፈታው ወጣቱ ታጋይ ሃብታሙ አያሌው ለኩላሊት ሕክምና የሚሆን ገንዘብ በኢንተርኔት መሰባሰቡ ቀጥሏል፣ ሁሉም የአቅሙን እንዲያዋጣ ጥሪ ቀርቧል

ወጣቱ ታጋይ ሃብታሙ አያሌው
ወጣቱ ታጋይ ሃብታሙ አያሌው
በስልጣን ላይ ባለው አገዛዝ በፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶበት በ እስር ቤት ከቆየ በኋላ በቅርቡ ጉዳዩን በውጭ ሆኖ እንዲከታተል የተፈታው የቀድሞ የአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወጣቱ ፖለቲከኛ  ሃብታሙ አያሌው በ እስር ቤት እያለ የጀመረው የኩላሊት እና የሄሞሮይድስ በሽታ እየጠናበት በመሄዱ ለህክምና የሚሆን ገንዘብ በመላው ዓለም የሚገኙ አገር ወገን ወዳድ ኢትዮጵያውያን በኢንተርኔት የበኩላቸውን እያዋጡ እንደሚገኙ ታውቋል።
“ሃምሳ ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ…” በሚል መርህ ወጣቱን ታጋይ ሃብታሙ አያሌውን ሕይወት ለማትረፍና በተለይም እያሰቃየው ካለው የሁለቱም የኩላሊት ሕመሙ እንዲድና ይህም ለከፋ ሁኔታ ሕይወቱን ከማጋለጡ በፊት የተጀመረው የኢንተርኔት ገንዘብ ማሰባሰብ ይህ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ በ94 ሰዎች ልገሳ 7453 ዶላር መድረሱ ሲሆን  ታውቋል:: ይህን በጎ ተግባር ላይ ከሚገኙት የዘ-ሐበሻ ድረገጽ አዘጋጆች መረጃ ማግኘት እንደተቻለው ለሃብታሙ አያሌው የህክምና ወጪ ሕዝብ እንዲያዋጣ የታሰበው ከ$30,000 በላይ ነው::
ሃብታሙ አያሌው ከሁለቱም ኩላሊቶቹ ህመም በተጨማሪም በሄሞሮይድስ ህመምም እየተሰቃየ ሲሆን በአስቸኳይ ህክምና የሚያስፈልገው በመሆኑ ሕዝብ ማንኛውንም የፖለቲካ ልዩነቱን ትቶ በሰብዓዊነት ሕይወቱን ለማትረፍ እንዲሯሯጥና ያለውን እንዲያዋጣ አስተባባሪዎቹ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል::
በኢንተርኔት በሚከተለው ሊንክ ውስጥ በመግባት ገንዘብ ማዋጣት የሚቻል ሲሆን ስማቸውን መጥቀስ የማይፈልጉም የብዕር ስም መጠቀም እንደሚችሉ አስተባባሪዎቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::
https://www.gofundme.com/2zgseemk
ከሊንኩ በታች የሃብታሙ አያሌውን ንግግር ከስር አስቀምጠነዋል:: ዛሬውኑ የተቻለዎትን በማድረግ ይህን ወጣት ሕይወት እንታደገው

No comments:

Post a Comment