Thursday, April 28, 2016

በዚህ ሳምንት በርከት ያሉ ወጣቶች… ለፀረ ህዝብ የኢህአዴግን ስርአት በመቃወም ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል መቀላቀላቸው ታወቀ።


በዚህ ሳምንት ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ ማሰልጠኛ ማእከል ከተቀላቀሉት ወጣቶች መካከል የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል…
ጋይም ዓይነይ ከትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ። ዞን ላዕላይ ኣድያቦ ወረዳ ዓዲ ሚልዮን ቀበሌ ገሊላ አከባቢ
ሸዊት ገብረኪዳን ከማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ዓዲ ፍታው ቀበሌ ሓዱሽ ዓዲ አከባቢ
ዕሉም ኪዳነማርያም፤ ከማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ማይ ወዲ ዓምበራይ ዓዲ ገባ ቀበሌ
ኣማኒኤል ኣብርሃ ከምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ ወርዓትለ ቀበሌ
ባራኺ ጉዑሽ ከማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ማይ ወዲ ዓምበራይ ዓዲ ጋባ ቀበሌ
ክፍላይ መዓሾ ከሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ዓዲ ዳዕሮ ወረዳ ጤረር ቀበሌ ዓዲ ዓይኖም ሲሆኑ
ወጣቶች ወደ ትህዴን ትግል ጎራ ለመሰለፍ ካስገደዳቸው ምክንያት ሲገልፁ በስርአቱ የሚፈፀሙትን የሰብኣዊ መብት ጥሰት፤ ህዝብ የገጠመወን የኑሮ ችግር ፤ ሰርተህ ለመኖርም ስራ ባለመኖሩ መሆኑን ገልፀዋል፣፣

በተለይ ጋይም ዓይነይ እንደገለፀው እሱ በሑመራ ከተማ ይስራበት በነበረበት ግዜ የስርአቱ ካድረዎች ምክንያት በመፍጠር እያሰሩ ሰላኣስቸገሩት ይህን በመስጋት ወደ ተወለደበት ኣካባቢ ቢመለስም በከፋ መልኩ ሽጉጥ ደብቀሃል ተብሎ የሃሶት ክስ ተመስርቶበት ለሶስት ወር ያህል እንደታሰረና በተመሳሳይ በእስር ቤቱ የሚገኙ ወጣት እሱረኞችም ኣብዛኞቹ ያለ ማስረጃ በጥርጣረ ብቻ የታሰሩ መሆናቸውን አስረድተዋል፣፣

No comments:

Post a Comment