Sunday, April 10, 2016

“የኢትዮጵያ ሳክስፎን ንጉሥ” የሚል የክብር ስም የተጎናጸፉት አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ የቀብር ስነ ስርአት ተፈፀመ

አረፍዓኔ ፋንታሁን
የ-አርቲስት-ጌታቸው-መኩሪያ-የቀብር-ሥነሥርዓት1
‹የኢትዮጵያ ሳክስፎን ንጉሥ›› የሚል የክብር መጠሪን የተጎናጸፉት አርቲስት ጌታቸው መኩሪያ በተወለዱ በ81 ኣመታቸው መጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። የቀብራቸው ሥነሥርዓትም ወዳጅ፣ ዘመድ እና የጥበብ አድናቂዎቹ በተገኙበት መጋቢት 27 ቀን 2008 ዓ.ም በጼጥሮስ ወጻውሎስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል። እኛም በቀብራቸው ላይ ተገኝተን ያነጋገርናቸው የሙያ አጋሮቻቸው ይህንን ነግረውናል።

ለኔ ጌታቸው በሀይል የማከብረው ታላቅ ባለሙያ ነው። አብሬ የመስራት ዕድሎች ነበሩኝ።የማስታውሰው ከአሜሪካ ትምህርቴን ጨርሼ እንደመጣሁ በቀረርቶ አጨዋወቱ በጣም ስለማደንቀው ፡አንድ አዲስ ቅንብር ሰርቼ፣ እንደማስታውሰው በራስ ሆቴል መሥራታችን ትዝ ይለኛል። ከዛም እንግዲህ ያለፈው ላንደን ላይ፣ ከትልቅ ኦርኬስትራ ጋር አብረን የመሥራት ዕድል አግኝተናል። ከዛ ለመጨረሻ ጊዜ የማስታውሰው ፈረንሳይ ሀገር የኔ ባንድ እና ጌታቸው ከአይኤክስ ጋር አብረው የነበሩበት ኮንሰርት ነበር። ዛሬ ከባድ ሀዘን ነዉ የተሰማኝ።ትልቅ ሰው ነበር።ትልቅ ነገር ሰርቶ አልፋል።
ሙላቱ አስታጥቄ፤ የኢትዮ ጃዝ ፈጣሪ
ሙላቱ-አስታጥቄ፤-የኢትዮ-ጃዝ-ፈጣሪ
መቼም ሞት ለሁላችንም የማይቀር ጽዋ ቢሆንም የአቶ ጌታቸዉ ማለፍ በእጅጉ ያሳዝናል።ትልቅ ባለሙያተኛ ነበር።በተለይ ለዚህ ወጣቱ ትዉልድ ብዙ ነገር ማስተላለፍ የሚገባው ሰው ነበር። ኢትዮዺያዊ ቅኝቶቾን በዘመናዊ መሳሪያ እንደፈለገ የሚያደርገው እሱ ነው ብል አልተሳሳትኩም። በእርግጥ ብዙ ወጣቶችን አፍርቷል። እኔ ራሴ ከሱ ብዙ ተምሬያለሁ።አብሬ በመስራቴም ደስ ይለኛል። ብዙ ትዝታም አለን።ከኔ ጋር በ 1974ዓ.ም በቀይ ኮከብ ዘመቻ ኤርትራ ሄደን ነበር። እንደዚሁም ሰሜን ኮሪያ አብረን ሄደናል። ብዙ ነገር አጫዉተዉኛል። ትልቅ ትምህርት አግቻለሁ።በሞቱ በጣም ነው ያዘንኩት።
ኮማንደር ሊቀመኳስ አየለ፤ የፌደራል ፓሊስ ኦርኬስትራ እና ትያትር ክፍል ሃላፊ
ኮማንደር-ሊቀመኳስ-አየለ፤-የፌደራል-ፓሊስ-ኦርኬስትራ-እና-ትያትር-ክፍል-ሃላፊ
እንግዲሕ የሙዚቃዉን ነገር ስናስብ ጋሽ ጌታቸዉን ማጣት ቀላል ነገር አይደለም።ጋሽ ጌታቸዉ ሠርቶ የማይጠግብ፣ ደግሞ የትም ቦታ ቢሆን ትልቅ ስራ የሚሠራ ነዉ። የሙዚቃን ትምህርት መማር ብቻ ሳይሆን ሊሠጥህ ይገባል።ጋሽ ጌታቸዉ የተሰጠዉ ሰዉ ነዉ።ለዚህ የተፈጠረ ሰው ነው ማለት ትችላለህ።የሰዉ ልብ ዉስጥ የሚቆይ ስራ የሚሠራ ሰዉ ነው። የተዋወቅንዉ በ1954 ብሔራዊ ትያትር ስሰራ ነዉ። በአንድ እክል ምክንያት ለተወሰነ ጊዜ ከብሔራዊ ትያትር ርቆ ነበር። ከዚያ በሁላ ተመልሶ አብረን ሠርተናል። ቀደም ብሎ ከነመራአዊ ስጦት፣ወዳዼነሕ ፍልፍሉ ጋር ብሔራዊ ትያትርን ከመሠረቱት አንዱ ነው ።እነ ነርሲስ ናልባልዲያን ካበቛቸው ማለት ነው። እግዚያብሔር ነፍሱን ይማረው።በሰው አቤቱታ የሚመለስ ቢሆን ጌታቸዉ በትልቅ ስራው ሊቆይ የሚገባው ነበር።ለመጨረሻ ጊዜ የተያየነው የዛሬ አመት የብሔራዊ ትያትር 60ኛው አመት ሲከበር ነበር።ቁጭ ብሎ ያን ስራዉን ፡ ፈፅሞ ከርሱ ያልተለየ መሆኑን ፡ባለ ጉልበት ሠርቶ ያሣየበት ነበር። ሕዝቡ መድረክ ላይ እየወጣ እግሩ ላይ ፍቅሩን ሲገልጽለት ነበር።ልክ እንደ ስንበት ነበር ማለት ትችላለህ። ከዚያ ወዲህ የሠራ አይመስለኝም።
ግርማ ነጋሽ፤ ድምጳዊ
ግርማ-ነጋሽ፤-ድምጳዊ
በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው።ሞት ለማንም የማይቀር ቢሆንም። ጋሽ ጌታቸው በአካል ቢለየንም መቼም ሥራው ህያው ነውና አልሞተም ነው የምለው እኔ።የተዋወቅነው ብሔራዊ ትያትር እያለ ነው። እኔ ራስ ባንድ ተቀጥሬ እያለሁ ጕረቤት ስለነበርን ተቀራረብን።ይሄ እንግዲህ በ1955 ላይ ነው።ትውውቃችን ፖሊስ እያለም ቀጠለ። ሠርቶ የማይደክም ሰው መሆኑን አስታውሳለሁ። ጥሩ ሰው ነው ደግሞ።
ባህታ ገብረ ሕይወት ፤ ድምጳዊ


No comments:

Post a Comment