Wednesday, April 20, 2016

ጥልቅ የሐዘን መግለጫ


ባለፉት 25 ዓመታት የጎጠኛው እና የዘረኛው የወያኔ ቡድን በሁሉም የሐገራችን ግዛቶች ውስጥ በታሪክ ታይቶ የማይታወቅ የሐገርን እና የሕዝብን ሐብት የመዝረፍ አላማ ሕዝብን የመለያየት የማሰቃየት የማፈን የመግደልና እንዲሁም የጅምላ ጭፍጨፋዎችን በንጹሐን ዜጎች ላይ ያለምንም እርሕራሄ እየፈጽጸመ ያለ አረመኔ ቡድን መሆኑን በተለያየ ጊዜያቶች በህዝባችን በይፋ ያስመሰከረ መሆኑ ግልጽ ነው:: 
ኆኖም ግን ይህ አልበቃ ብሎት በ08/04/2016 ዓዝ/ም በጋንቤላ አካባቢ የሚኖሩ የኑዌር ብሔረሰብ ኢትዮጵያዊ ወገኖቻችንን ሴቶችና ሕጻናትን ጨምሮ ከ 140 በላይ የሆኑ ዜጎች ላይ እጅግ በጣም አሰቃቀ የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋ እና ከመቶ በላይ ደግሞ ከጎረበት አገር ተሻግረው በመጡ የደቡብ ሱዳን ወታደሮች ታፍነው የተወሰዱ መሆኑን እየተገለጸ ቢሆንም በኢትዮጵያ መንግስት በራሱ የተቀነባበረ መሆኑ የሚያሳይ እና የሚጠቁሙ በርካታ ነጥቦችን መግንዘብ ይቻላል :: 
መሆኑን ለሐገራችን እና ለህዝባችን ደንታ የለለው መንግስት ተብዬ በወቅቱ ተገቢውን የመከላከል እርምጃ በፍጥነት አለመውሰዱ መወቀስ ብቻ ሳይሆን ከጥቃቱ ጎን ለጎን የመንግስታችን ጥብቅ ሚስጥራዊ ስራ እንደሆነ በግልጽ የሚያሳይ ዘርን ያማጥፋት ተግባር መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ግልጽ ሴራ ነው:: ስለዚህ እኛ በደቡብ አፍሪካ የምንገኝ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር በወገኖቻችን ላይ በተፈጸመው አረመኔያዊ የጭፍጨፋ ተግባር በእጅጉ ያሳዘነንና ጥልቅ ሐዘን ውስጥ የገባን መሆኑን እየገለጽን በጋንቤላ ኑዌር ብሔረሰብ እና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናቱን ይስጥልን በማለት የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ማህበር በደቡብ አፍሪካ የጥልቕ ሐዘን መግለጫውን ያስተላልፋል::

የወገኖቻችን ደም በከንቱ ፈሶ አይቀርም 
የኢትዮጵያ ትንሳኤ ቅርብ ነው ::
ድል ለሰፊው ሕዝብ ::

No comments:

Post a Comment