Wednesday, April 13, 2016

ሰበር ዜና (የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


በመቶዎች የሚቆጠሩ የ24ኛ ክፍለ ጦር አባላት ከነትጥቃቸው ጠፉ፡፡
የ24ኛ ክፍለ ጦር አባላት የሆኑ በመቶዎች የሚቆጠሩ ወታደሮች ለጊዜው ስሙና ማዕረጉ ተለይቶ ባልታወቀ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥ የሆነ የጦር መኮንን እየተመሩ ትናንት /ሚያዚያ 4 2008 ዓ.ም/ ከነሙሉ ትጥቃቸው ከድተዋል፡፡
አነዚህ ተደራጅተው ከነጦር መሳሪያቸው የጠፉት ወታደሮች የት እንደደረሱ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ወደ ሱዳንና ኤርትራ ይሻገራሉ ተብሎ ስለተገመተ የሱዳንና ኤርትራ ጠረፎች በጠቅላላ ከፍተኛ ቁጥር ባለው የመከላከያ ሰራዊት ታጥረው እንዲወጠሩ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም መንገዶች ሁሉ ተዘጋግተዋል፡፡

No comments:

Post a Comment