Monday, April 4, 2016

ኢሳት ወደ አየር ተመለሰ – ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን እና ሬዲዮ የተሰጠ መግለጫ

ESAT television new satelliteኢሳት ባለፉት ስድስት ዓመታት (ከሚያዚያ 2003 እ/ኤ/አ April 2010) ጀምሮ በኢትዮጵያና ከኢትዮጵያ ውጭ የኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የመረጃ ምንጭ ሆኖ እያገለገል ይገኛል።ኢሳት በኢትዮጵያ ምድር እንዳይታይ ከሳተላይት ለማውረድ ስድስት ዓመታት ሙሉ በተደረገው የመንግስት ርብርብ 20 ያህል ሳተላይት ለመቀየር እና ተጨማሪ ወጪ ለማውጣት ተገደናል።ለሳተላይት አቅራቢ ኩባንያዎች የተማጽኖ ደብዳቤ በመጻፍ እና መደለያ በማቅረብ እንዲሁም ዋሺንግተን ፖስትን የመሳሰሉ ታዋቂ የምዕራብ ሚዲያዎች ጭምር እንደዘገቡት ኢሳት ላይ የሳይበር ጥቃት ቢሞከርም ሁሉንም ተቋቁመን ለ 6ኛው ዓመት ደርሰናል፥ ግባችን ዓመታት መቁጠር ሳይሆን ነጻነት በመሆኑ የኢትዮጵያውያን የዋይታ ድምጾች በደስታና ድል ሲመነዘሩ ለማየትና ለመስማት ተስፋም ሰንቀናል።
ESAT television new satellite
ኢሳትን እንደገና ወደ አየር ለመመለስ የተደረገው ጥረት ከዛሬ ዕሁድ መጋቢት 25/2008 ( እ/ኤ/አ April 3/2016) ጀምሮ ፍጻሜ በማግኘቱ የሙከራ ስርጭቱ ቀጥሏል ኢሳትን ለማፈን የሚንቀሳቀሰው ሃይል አሁንም በአፈና ሙከራው እንደሚገፋ ቢጠበቅም፥ እነርሱ ለማፈን ካላቸው እልህ በላይ እኛም ለነጻነት ቆርጠን የምንሰራ በመሆናችን ፈተናው ቢቀጥልም በማናቸውም ሁኔታ ኢሳት ወደኋላ እንደማይመለስ ማረጋገጥ እንሻለን።ይህንን ሁሉ ፈተና እየተጋፈጥን እንድንቀጥል ጉልበት የሆነን በውጭ ያሉ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እና በሃገር ቤት ያለው ወገናችን የነጻነት እና የፍትህ ርሃብ በመሆኑ አሁንም ድጋፋችሁ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ እያቀረብን አዲሱ ሳተላይት የሚከተለው መሆኑን እንገልጻለን።http://ecadforum.com/Amharic/archives/16332/
Satellite: Tel Star T12
Transponder TXP K33
15 Degrees West
Downlink Frequency: 12550
Symbol Rate: 4.411
QPSK,DVB-S 3/4

ይህ አዲስ ሳተላይት በናይል ሳት አቅጣጫ በመሆኑ የአረብ ሳት ተጠቃሚዎች የሳተላይት መቀበያ ሳህኑን (ዲሹን) ማንቀሳቀስ አይጠበቅባችሁም።ሆኖም በጥራት ማየት ካልቻላችሁ ሳህኑ ላይ ተጨማሪ LNB መግጠም ይኖርባችኋል።
የኢሳት አስተዳደ

No comments:

Post a Comment