Monday, April 11, 2016

6 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ህጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት ተዳርገዋል



ሚያዚያ ፫( ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢትዮጵያ ረሃብ አለማቀፍ ትኩረት እያገኘ ነው፡፡ ቢቢሲና አልጀዚራን የመሳሰሉ ታላላቅ የመገናኛ ብዙሃን በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን የተመለከተ ዘገባ አቅርበዋል፡፡ አለማቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች፣ መንግስትን ላለማስከፋት ፈራ ተባ እያሉም ቢሆን ሁኔታው አስፈሪ መሆኑን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ አሁን ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን ሲመለከቱ፣ ስጋታቸውን በአደባባይ መግለጽ ጀምረዋል፡፡ 6 ሚሊዮን ህጻናት ለከፋ ረሃብ መዳረጋቸውን የአለማቀፉ የህጻነት አድን ድርጅት አስታውቆአል፡፡ በአጠቃላይ ድርቅ ያጠቃው አካባቢ 30 ሚሊዮን የሚገመት ህዝብ መያዙን አልጀዚራ በሰራው ሪፖርት አመልክቶአል፡፡ የዚህን ዜና ሀተታ ከዜናው በሁዋላ እናቀርባለን፡፡

No comments:

Post a Comment