Friday, April 8, 2016

በአምቦ ወህኒ ቤት አንድ ወጣት በደረሰበት አሰቃቂ በድብደባ ተገደለ ኢሳት ( መጋቢት 29 ፥ 2008)


አምቦ ወህኒ ቤት ውስጥ የታሰረ አንድ ወጣት በድብደባ መገደሉን ወላጅ እናቱ ለኢሳት ገለጹ። ላለፉት 10 አመታት በወህኒ ቤት ውስጥ የቆየው ወጣት ጌጡ በቀለ ቶሎሳ፣ ህይወቱ ያለፈው ከአምቦ ወህኒ ቤት ቃጠሎ ጋር በተያያዘ እጅ አለበት በሚል በደረሰበት ድብደባ መሆኑም ተመልክቷል።
በፖለቲካ ሳቢያ ከ10 አመት በፊት ወህኒ ቤት መግባቱ የተገለጸው ወጣት ጌቱ በቀለ፣ እዚያው እያለ በመጣበት ተጨማሪ ክስ ወህኒ ቤት ውስጥ እንዲቆይ መደረጉን ከወላጅ እናቱ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል። የመጣበትም ተጨማሪ ክስ በአካባቢው ከተገደለ የኦህዴድ ካድሬ ጋር በተያያዘ ሲሆን፣ ገዳዩ አንተነህ በሚል ተወንጅሎ መቆየቱንም መረዳት ተችሏል። 
Ambo
ወላጅ እናቱ በቅርቡ ወህኒ ቤት ሄደው ሲጎበኙ ጤነኛ የነበረው ጌቱ በቀለ ቶሎሳ በሳምንት ጊዜ ውስጥ ህይወቱ ማለፉን አስረድተዋል። ሆስፒታል መግባቱን ገልጾ በላከላቸው መልዕክት ሊጎበኙት ሲሄዱ አስከሬኑ መላኩ እንደተነገራቸው አስረድተዋል።
አስከሬኑን ለማግኘት የደረሰባቸውን መጉላላትም ያስታወሱት የሟች ወጣት ጌቱ በቀለ ቶሎሳ እናት፣ አስከሬኑ ሲደርሳቸው ከፍተኛ ድብደባ ያደረሱበት መሆኑን ገልጸዋል።
ሟች ወጣት በአካሉ ላይ በደረሰበት ድብደባ ከፊል ሰውነቱ በፋሻ መጠቅለሉንም ለኢሳት አስረድተዋል።Ambo

No comments:

Post a Comment