የጎንደር ሕብረት
gonderhibrert72@gmil.com /website: www.gonderhibret.org
1
04/06/2016
የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በጎንደር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፈተ!
ይድረስ ለጎንደር ህዝብ ቁጥር # 8
ወያኔ ገና ካፈጣጠሩ ጀምሮ አማራን ለማጥፋት ዓላማው አድርጎ የተነሳ መሆኑ ቢታወቅም፤ በተለይ በጎንደር/አማራ
ህዝብ ላይ ለሃያ አምስት ዓመታት ያህል የወልቃይት ጠገዴ፤ ካፍቲያ፤ ሁመራና ጠለምት ህዝብ በገሃድ ባካሄደዉ
የዘር ማጥፋት ዘመቻ ለማመን የሚከብድ አሰቃቂ ድርጊት ፈጽሟል።
ጀግናዉ የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ፤ የወያኔ
አረመኒያዊ ጭፍጨፋ ሳይበግረው፤ ትግስትና ጥበብ በተላበሰ መልኩ ለብዙ ዓመታት “ጎንደሬ፤ አማራ ነን፤ ለወያኔ
አንገዛም” በማለት በቆራጥነት ለማንነቱ በመታገል መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል። በርግጥም፤ ሁላችን እያየን
ያለነው ሃቅ፤ የወያኔ ግፍ እና በደል፤ እንዲሁም እሥራት እና ግድያ በጠነከረ ቁጥር፤ በኮሚቴ የሚመራው፤ ሰላማዊ
የማንነት ትግላቸው፤ ፍትህና ነጻነት ለምንሻ ሁሉ የሚመለከተን ሁኗል። በመሆኑም በሁላችንም ልብ ውስጥ ሰርፆ፤
ትግሉን ከአንድ አካባቢ ወደ መላው የአማራ ማንነት አቀጣጥሎታል። የማንነት ጥያቄን መፍትሄ ለማግኘት
በቁርጠኝነት ተነሳስተዉ “መንግስት አለ” በሚል እምነት አቤቱታ እንዲያቀርቡ ተወክለው የተላኩ የኮሚቴ አባላት
ጉዳት ድርሶባቸዋል። በወያኔ ታጣቂወች ታፍነዉ ተወስደዋል። በሰሞኑ ታስረዉ ተወስደው መዳረሻቸው ካልታወቁት
የኮሚቴ አባላት ውስጥ ሊላይ ብርሃኔ አንድ ማስረጃ ነው። እንዲሁም ሌሎችም የአካባቢው ኗሪዎች፤ በግድ ትግሬ
አንሆንም ብለዉ በአማራ ምንነት የፈረሙ በመቶወች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን በወያኔ አፋኝ እስኳድ ቡደን እየታደኑ
በሱዳን መኪና ተወስደዉ የደረሱበት አይታወቅም። በዚህ አስከፊ እርምጃ የተበሳጨዉ የዳንሻ ህዝብ በቁጣ ተሰልፎ
“ታፍነው የተወሰዱ የኮሚቴ አባላት ይመለሱ” በማለቱ ከትግራይ በመጣ ልዮ ወራሪ ሰራዊት፤ ትግሬ አልሆንም
ያለውን ኗሪ ሁሉ በጀምላ አስሮ እያንገላታ ወደ ሽሬና መቀሌ 06 እስር ቤቶች እያጎራቸዉ ነዉ። ይህን ሰይጣናዊ
የጥፋት ዘመቻውን ለመገደብ፤ ብሎም ማንነታችን ለማስከበር ሁላችንም፤ በአንድ ላይ እንድንቆም የግድ የሆነበት
ወቅት ላይ ደርሰናል።
ለብሔራዊ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን)፦
የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር የአማራን ህዝብ ተከዜን ተሻግሮ አስገድዶ መግዛቱን ከናንተ የበለጠ የሚያዉቅ የለም።
ታጋሹና ሰፊዉ የጎንደር/አማራ ህዝብ በወያኔ የደረሰበትን ዉርደትና እልቂት የሥርዓቱ አጋር ሁናችሁ በአቅመ
ደካማነት እንወክለዋልን የምትሉት ህዝብ፤ በትሃት አፋኝ ገዳዮችና በአማራዉ አስተዳደር ውሥጥ የተሸገሸጉ ሰላዮችና
ካድሬወች፤ በአማራ ህዝብ ላይ በጭካኔ በፈፀሙት ግፍ፤ ቢያንስ 5 ሚሊዮን ህይወት ጠፍቷል። ከእንግዲህ ግን
በእዉነት የአማራን ህዝብ ከወከላችሁ፤ “ጎንደሬ/አማራ ነን” በማለታቸዉ ብቻ፤ እየታፈኑ የሚገደሉ የወልቃይት
ጠገዴ ወገኖቻችን ሰቆቃ እንዲያከትም እና በሰላም እንዲኖሩ ከወገኖቻችሁ ጋራ በመቆም፤ ህዝባችሁንም እራሳቸሁም
ከዉርደት እንድታድኑ ጥሪያችን እናቀርባለን። ወያኔ ከእንግዲህ በአማራዉም ሆነ በመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ የተተፋ፤
ስርዓቱም በፍጹም የማይጠገን የነቃ ብርሌ በመሆኑ፤ በአቸኳይ መቀየር ያለበት ዘረኛ አምባ ገነን ቡድን ነዉ።
ህዝብ የወከላቸዉ የወልቃይት ጠገዴ ተወካዮች፤ የአማራ ምንነትን ለማስከበር ለፌደሬሽን ምክርቤት አቤቱታ
በማቅረባቸዉ በወያኔ ደህንነት ታፍነዉ ሲወሰዱ፤ እናንተም፤ እንደ አማራ ክልል ተወካይ ለምን? ብላችሁ መጠየቅ
የጎንደር ሕብረት
gonderhibrert72@gmil.com /website: www.gonderhibret.org
2
ነበረባችሁ። ይባስም ብሎ ሰሞኑን ህዝብን ለማወያየት በጠራችሁት ህዝባዊ ስብሰባ፤ የወልቃይት ጉዳይ ፈጽሞ
እንዳይነሳ ወያኔን ወክለው በአማራው ድርጅት ስም የሚመሯችሁ፤ አለቆቻችሁ በማስጠንቀቂያ ሲያፍኗችሁ፤ አሜን
ብላችሁ መቀበላችሁ፤ ለአሁኑ እጅግ አሳፋሪ፤ ለወደፊቱ ደግሞ፤ በታሪክ አስጠያቂ ከባድ ወንጀል ነው።
የወልቃይት ህዝብም ሆነ፤ የኮሚቴ ተወካዮች፤ የአማራ ምነነት መብት እንዲከበርላቸዉ ስለጠየቁ እንደ አራዊት
በወያኔ ሲታደኑ፤ የአማራ ተወካይ ነኝ ከሚለው አካል የጸጥታም ሆነ የህግ ከለላ ማግኘት ነበረባቸዉ። ይህ ግፍ
ሲፈጸም በቸልታ ምንንም አይነት የህዝባዊ አቋም መግለጫ ሳይወሰድ ጀሮ ዳባ ልበስ ማለት፤ ወከልኩት ለሚለዉ
ሰፊዉ የአማራ ህዝብ ከባድ ወንጀል ነዉ። ያለ ህዝብ ድጋፍ ስልጣን ይዞ ተኮፍኖ ቁጭ ማለት ከባህር የወጣ አሳ
እንደማለት ነዉና፤ ለሆዳቸው ከወያኔ ጋር ተማምለው በመሪነት ከተደረደሩት መሪዎች ብዙ ባንጠብቅም፤ ቢያንስ
የብ.አ.ዴ.ን ተራ አባላት ፍጹም ሳታመናቱ፤ አሁኑኑ፤ ለራሳችሁ ማንነት፤ በንጹህ ህሊና ለታሪክ ትበቁ ዘንድ፤
ከወገኖቻችሁ ጋር እንድትቆሙ፤ በአንክሮት እንጠይቃለን። የጎንደርንም ሆነ የአማራዉን ህዝብ ለመከፋፈል፤
ለማዋረድ የሚጠቀምባቸዉ የትግራይ መስፋፋትን መርሃ ግብር እንዲያስፈጽሙ፤ በካድሬነት መልምሎ በ ብ. አ. ዴ.
ን ውስጥ ሰግሥጎ ባስቀመጣቸዉ ታማኝ የወያኔ ጀሮ ጠቢዎች መታዘዝ ማክተም አለበት።
ሰሞኑን የወያኔ ቱባ፤ ቱባ ባለሥልጣናት እና ካድሬዎቻቸው በመቀሌ ሚስጢራዊ ስብሰባ አድርገው፤ “ጎንደርን
አጥቅተን፤ ወልቃይትን እንደያዝን ለመኖር ካሥፈለገ፤ የቅማንት እና የአማራን ህዝብ በ6 ወራት ዉስጥ በማያቆም
የርስ፤ በርስ ጦርነት ውስጥ መዘፈቅ አለብን” በሚል መሰሪ ተንኮል ተሥማምተው፤ ተማምለው ተለያይተዋል።
ለዚህም ጉዳይ የአማራው ድርጅት ተወካዮቻቸውን እነ አቶ ደመቀ መኮነንን የፊት አብሪ እንዲሆኑ መድበዋል።
እናስ! አናንተም የብ.አ.ዴ.ን አባላት ወገኖቻችሁ ሲጨፈጨፉ ማየት እንዴት ህሊናችሁ ይፈቅዳል? እስከመቸ
ድረስ፤ የአማራ ማንነት መዳብ፤ የትግሬ ማንነት ወርቅ ሆኖ በላያችን ላይ በግፍ ዘምኖ ይኖራል? መልሱን ከናንተ
እንሻለን። እኛ ግን፤ የትግራይ ግፈኛ ቡድን ጭቆናና የበላይነት አሁኑኑ በጋራ ትግላችን መወገድ አለበት እንላለን።
ይድረስ ለትግራይ ህዝብ!
የጎንደር ሕብረት ከተመሰረት ጊዜ ጀምሮ፤ በምናወጣቸው መግለጫዎቻችን ሁሉ፤ በደም በሥጋችን ተዋህዶ ወገናችን
ለሆነው የትግራይ ሕዝብ በተደጋጋሚ የወንድማማችነት ታሪካችን እንዳይበረዝ፤ ጥሪ ማድረጋችን ይታወሳል። ይሁን
እና፤ ዛሬም እንደ ትናንቱ፤ የጎሳ ፖለቲካን አላማው አድርጎ ከአብራክህ የወጣው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ብሎ ራሱን
የሚጠራው ቡድን በመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከባድ ጉዳት እያደረሰ፤ አንጡራ ሃብቷን እየዘረፈ የእርስ በእርስ
ግጭትን እያቀጣጠለ፤ እስከ መጨረሻው አጥፍቶ ለመጥፋት በመግፋት ላይ ይገኛል። በአለፉት 25 ዓመታት
የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ “ በዘመናት ታሪኬ በጎንደር ክ/ሀገር አስተዳደር ስጠራ የኖሩኩ አማራ ነኝ” በማለቱ
ምክንያት፤ የዘር ማጥፋት ድርጊት ተፈጽሞበታል። ታጥቀዉ የሚገሉትም ሆነ ሃብቱን የሚዘርፉት ዋና
መንደርደሪያቸዉ፤ ይኽው የተፈጠሩበ የትግራይ ክፍለ ሃገር ነዉ። በትምህርት ተቋም ያሉም ሆኑ፤ በመላ አገሪቱ
የሚኖሩ ትውልደ ትግራይ የሆኑ የጥቅም ተካፋዮች፤ በጎንደር ህዝብ ላይ ወያኔ የያዘዉን የመስፋፋት ፖሊሲ
በሚስጥርም ሆነ በገሃድ እየደገፉ መሆናቸውን በትዝብት እየተመለከትን ነዉ። ይህ የወደፊቱን የሁለቱን ክፍለ
ሀገሮች አብሮ በሰላም የመኖር ህልዉና ያላገናዘበ የጥፋት ዓላማ በመሆኑ፤ አሁኑኑ ለጋራ ሰላማችን እና ለአለፈውም
የጎንደር ሕብረት
gonderhibrert72@gmil.com /website: www.gonderhibret.org
3
ሆነ ለመጭው አብሮነታችን ሲባል፤ እውነትን እና ታሪክን መሰረት አድርገን፤ በጎንደር ክ/ሀገር የወልቃይት ኗሪ
የሆኑትን ወገኖቻንን ግፍ እና በደል አብረን በቃ! ሰላማዊ መፍትሔ ይሰጥ! ልንል ይገባል።
የትግራይ እና የጎንደር ህዝብ አብሮ የመኖር ችግር ከቶዉን አልነበረዉም። ወያኔ የያዘዉ ፖሊሲ ግን፤ በጎንደር ክፍለ
ሃገር ለብዙ ዓመታት የኖረዉን የትግራይ ህዝብ ለማጋጨት፤ ከተከዜ ማዶ ተሻግሮ፤ የጎንደርን መሬት፤ ታሪካዊ
የትግራይ መሬት ነዉ ብሎ በጉልበት መንጠቅ ህዝብን ከህዝ በማዳማት ከስልጣን ለመቆየት ብሎም የአማራን
ህዝብ ከምድረ ገጽ ለማጥፋት መርሃ ግብር ነድፎ የከፈተዉ ዘመቻ መወገዝ አለበት። ለዚህ መሰሪ ተግባር
ይጠቅማል በሚል፤ የአማራና የቅማንትን ማህበረሰብ ከፋፍሎ፤ ዘላዓለማዊ ሰላማቸው ደፍርሶ፤ በጠላትነት
እንዲተያዩ፤ በተፈጠረው ጊዚያዊ የማንነት ጥያቄ ችግር ላይ ቤንዚን እያርከፈከፉ፤ እሳት ለማንደድ የሚደረገው
የወያኔ ተንኮል አሁኑኑ መቆም አለበት። ሰፊዉ የትግራይ ህዝብ፤ የወያኔን፤ አንዱን ዘር ከሌላዉ ዘር ጋር የማዋጋት
ዘመቻን፤ ከራሱ ደህንነት አኳያ መቃወም አለበት። ይህ ካልሆነ ግን፤ በሁሉም የአገሪቱ በሰላም፤ እየኖሩ ያሉት፤
የትግራይ ተወላጅ ወገኖቻችንን የመጨረሻ እጣ ፈንታ እጅግ የከፋ እንደሚያደርገው፤ ከወዲሁ አሳሥቦናል። በምንም
ስሌት፤ ትልቁን ዓሳ፤ ትንሹ ዓሳ ሊውጥ፤ ፈጽሞ አይቻለውም እና!!
የወያኔ አካሄድ ትግራይን ከጎንደር/አማራ ታሪካዊ መልካም ጉርብትናን በጥሶ ለራሱ ስልጣንና የሃብት መዝረፊያ
መሰላል አድርጎ የትግራይን ህዝብ በጦርነት የመማገድ አባዜ ነዉ። በተለይ ያሁኑ ጦርነት የጀመረዉ ከወር በፊት
የትግራይን ህዝብ በጠገዴና በሁመራ አሰልፎ በሽማግሌወች ላይ የሃይል እርምጃ እንዲወሰድ፤ “የትግራይ ህዝብ
ድምጽ ሰቷል” የሚለዉ የነ አቶ አባይ ወልዱ የአዋጅ ነጋሪትን መሰረት ያደረገ በመሆኑ፤ ይህን ጦርነት መላው
የትግራይ ሕዝብ በጥብቅ እንዲቃወም፤ ታፍነዉ የተወሰዱ የኮሚቴ አባላት በአስቸኳይ እንዲፈቱ፤ ጥያቄ
እንዲያቀርብ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።
የተከበሩ ልኡል እራስ መንገሻ ስይዮም መሰረት የሌለዉን የወያኔን የወልቃይት ይገባኛል አደገኛ አቋም
ለማስጠንቀቅ፤ የሁለቱን ህዝቦች የብዙ ሽሂ ዓመታት መልካም ታሪክ መሰረት አድርገዉ የበጌ ምድርና የትግራይ
ድንበር ተከዜ መሆኑን በአባትነታቸዉ ለትግራይ ሕዝብ እና ለአዲሱ ትዉልድ አስተምረዋል። ይህን አላስፈላጊ ጦርነት
ለማስወገድ እዉነት የሆነዉ ሃቅ ለመላዉ ኢትዮጵያ ህዝብ ለማሰማት ያስተላለፉት መልክት ታሪካዊ ነዉ። በኛ
እምነት፤ የጎንደር ህዝብ ከልዑል እራሥ መንገሻ ሥዩም የበለጠ፤ ትግራይን ወክሎ የሚናገር የለም ብሎ ያስባል
ብለን ሥለምናምን፤ ከፍተኛ የአክብሮት ምስጋናችን ልናስተላልፍ እንወዳለን። ሌሎችም እንዲሁ፤ ለአገራቸው
አንድነት፤ ለሕዝባቸው ሰላም የሚቆረቆሩ ሀቀኛ የትግራይ ልጆች፤ በወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ላይ ወያኔ እዬፈጸመ
ያለዉን ግፍ በማዉገዛቸዉ እና የሁለቱ ክፍለ ሃገራት ድንበር ተከዜ መሆኑን አስረግጠዉ በመናገራቸዉ፤ የወያኔን
የዉሸት የመሬት “ይገባኛል” ጥያቄ ዉድቅ ሁኖ እርቃናኑ እንደቀረ ማረጋገጫ ነዉ። የተከበሩ ገብረ መድህን አራያ
እና የተከበረዉ መምህር አብርሃ ደስታም በምሳሌነት ይጠቀሳሉ።
በሽማግሌ ሥም ለሚንቀሳቀሱ ወገኖች፦
በጎንደርም ሆነ በመላዉ ኢትዮጵያ ሽምግልና ትልቅ ታሪካዊ ቦት ያለዉ ነዉ። ለሁለቱም ወገን በነጻነት የእዉነቱን
የሚናገር፤ የተበደለን የሚያስክስ፤ ያጠፋን የሚገስጽ፤ በቅጣት የሚፈርድ እንደነበር አበዉ አባቶቻችን ስተምረዉናል።
የጎንደር ሕብረት
gonderhibrert72@gmil.com /website: www.gonderhibret.org
4
የሚወክላቸዉም፤ አምኖ የሚመርጣቸው በዳይ እና ተበዳይ አካል ነዉ። በወያኔ ዘመን እየተከሰተ ያለዉ ግን፤ እጅግ
የሚያሳፍር እየሆነ መጥቷል። ሽማግሌወች የሚሾሙት በወያኔ ነዉ። አብዛኛወችን የምንኩስና፤ የጵጵስና ቆብ አልብሶ
በሙስና የተዘፈቁ፤ ስብዕናቸዉን የሸጡ ፤ የሃይማኖት አባትነታቸዉን ጭራሽ የረሱ፤ በንዋይ የሰከሩትን በሽምግልና
አሰልፎ ገዝቱ እያለ ህዝብን እንዲያዘናጉ፤ ትጥቃቸውን በመፍታት በየእስር ቤቱ እንዲማቅቁ ማድረግ ነዉ። ህዝብ
እዉነተኛ ሽማግሌወችን ሲመርጥም፤ የራሱን ካድሬ ሽማግሌወች ለማስገባት ከላይ ከታች ይባዝናል። ይህ የብዙ
እዉነተኛ አባቶችን ስራ ጥቁር ቀለም እየቀባ፤ የሽማግሌ ነጻነት እና ክቡር ባህል አርክሷል። እናም! በጀግንነት
ነፃነታቸውን ለማስከበር፤ ወያኔን የሚሞግቱ ወገኖቻችን እጅ በሽምግልና ስም እየጠመዘዛችሁ፤ ለፍሪዳ
አታቅርቧቸው፤ በማለት እንማፀናለን።
በመሆኑም፤ ወገኖቻችን ሆይ! ህዝብ አምኖ የመረጣቸዉ እንጂ ወያኔ የመደባቸዉ ሽማግሌወች ለድርድር
እንዳይመጡብህ። ለሃይማኖትህ ክብር የሌለዉ፤ ግን ለዕምነት ቀናይ መሆንህን የሚያዉቀዉ ብልጥ ነኝ ባዩ ወያኔ፤
በሽምግልና ስም ትግልህን በረዶ እንዳይቸልስበት አደራ እንላለን። ወያኔ ባንድ በኩል እየደበደበ የሱ ሽማግሌወች
እጅህን አጣምረህ ቁጭ በል፤ ይቅርታ ጠይቅ የሚሉትን የሙስና ሃዋርያወች አትስማቸዉ። ከዚህ ቃላችን በበለጠ፤
ቀን ሲደራደርህ ውሎ፤ ማታ ሲያፍንህ እና ሲገድልህ፤ ሲያድር በተግባር እያየህ ነው። እናም፤ በወያኔ ልብ፤ ተንኮል
እንጅ ይቅርታ የለም። ታሪካዊ ባህሬዉም አይፈቅድለትም!! በመለማመጥ፤ ከወያኔ ነፃነት የምታገኝ መሥሎህ ከሆነ፤
ሞኝነት በመሆኑ፤ የጀመርከውን የነፃነት ትግል፤ ጎበዝ አለቃህን እየመረጥክ በመላ አገሪት በማቀጣጠል፤ ለአንዴ እና
ለመጨረሻ አፋኝ እና ግፈኛውን የወያኔ ሥርዓት አስወግድ።
ለመከላከያ ሰራዊት፡-
ከሁሉም በፊት አንዴ ቆም ብላችሁ ፀጥ ባለ ቦታ የራሳችሁን አመጣጥ እና ቤተሰብ አሥቡ። በርግጠኝነት
አብዛኛዎቻችሁ፤ የመጣችሁት በገጠሪቱ ኢትዮጵያችን፤ ከእጅ ወደ አፍ በሆነ አቅም በርሻ ሥራ ከሚተዳደሩ
ቤተሰቦች ነው። ከዚህ ውጭ የመጣችሁ ብትኖሩ ደግሞ፤ በጣም ዝቅተኛውን የጎሥቋላ ኑሮ ከሚጎነጩ የከተማ
ቤተሰቦች ነው። ይህ የአመጣጥ መሰረታችሁ በወታደራዊ ሙያ የበለጠ አዋህዶ አንድ አደረጋችሁ። በዚህ ሙያ
ስትቀጠሩ፤ “እናቴን፤ አባቴን ወይም ወንድሜን እና እህቴን ቀጥቅጨ፤ ወይም ጨፍጭፌ ለዚህ ሥራዓት
አሥገዛለሁ” ብላችሁ እንዳልሆነ ቢያንስ ስለ አብዛኛዎቻችሁ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል። የስማችሁ መጠሪያ
“የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት” ነበር። ሆኖም ዛሬ፤ ያለ ምንም ርህራሄ በመላ አገራችን፤ ጾታ፤ እድሜ ሳይገድባችሁ፤
የተወለዳችሁበትን ህብረተሰብ የአነሥተኛ ኑሮ ሰቆቃ፤ የነፃነት ጥማት ረሥታችሁ፤ ስለመብቱ፤ እና የመልካም
አሥተዳደር የጠየቀውን ወገናችሁን ሁሉ በየተላካችሁበት፤ የአለቆቻችሁን ትዛዝ ያለምንም ጥያቄ ለመፈጸም፤ በጭካኔ
ሌት ከቀን ስትጨፈጭፉ ማየታችን እጅግ፤ ልብን ሰባሪ፤ ከመሆኑም በላይ፤ በየቦታው የምታደርጉትን አረመኒያዊ
ተግባር ቪዲዮ እና ሥዕል ስንመለከት፤ እውነት እኒህ ሙያተኞች ከሰው ተፈጥረዋል ወይ? የሚል ጥያቄ
አጭሮብናል።
ሙያችሁም ይሁን መጠሪያችሁ፤ ከወራሪ አገራችን፤ ከግፍ አገዛዝ ደግሞ ወገኖቻችሁን ልትከላከሉ ሲገባ፤ የአንድ
ሥራዓት ሎሌ፤ በመሆን፤ የራሥችሁን ቤተሰብ በመጨፍጨፍ፤ ከፍ ካለ፤ የግፈኛ ሥራዓቱ፤ ዝቅ ሥትሉ ደግሞ፤
የወያኔ ድርጅት አገልጋዮች ሆናችኋል።
የጎንደር ሕብረት
gonderhibrert72@gmil.com /website: www.gonderhibret.org
5
ልብ በሉ! ቢያንሥ በወታደራዊው የአመራር ዘርፍ ያላችሁ፤ ትላንት በደርግ ሥራዓት ቢያንሥ ከናንተ በተሻለ
መልኩ አገሩን እጅግ ይወድ የነበረው፤ በሙያው ዓለም ያደነቀው መዓረግ የነበረው ወታደር፤ በግፍ ተገድሎ፤
ወይም የደረሰበት ሳይታወቅ የቤተሰብ የልብ ቁሥል ሆኖ ሲቀር፤ አብዛኛው ያለ ጥሮታ፤ ተበትኖ፤ የጎዳና ለማኝ
ሆኖ እንደነበር አሥታውሱ። በማንኛውም መልኩ፤ ሥራዓቱን አሳብጣችሁ፤ በትዕቢት፤ ነኪ እና ነቅናቂ የሌለው
አሥመሥላችሁ፤ ብታዩትም፤ በየትም ዓለም እንዳየነው፤ ግፈኞች፤ የግፍ ጽዋቸው ሞልቶ ሲፈስ፤ በህዝባዊ መዓበል፤
ታጥበው እንደሚደፉ ጥርጥር የለነም። እናንተም ይህን ህቅ አሁኑኑ ተቀብላችሁ፤ ከአውሪያዊ ባህሪ፤ ወደ
ሰውነታችሁ ተመለሱ። ስው እንዴት እንደ ዱር አውሬ በግፍ ይጨፈጨፋል ብላችሁ ራሳችሁን ጠይቁ።
ከወገኖቻችሁ፤ እርግማን፤ ከአለም አረመኒያዊ የታሪክ መጽሐ ተጠቃሽ ከመሆን ራሳችሁን ነፃ አውጡ። የምትበሉት
የሙያ ደመወዝ ሳይሆን፤ የወገኖቻችሁን ሥጋ ነው። የምትጠጡት፤ በጎናችሁ ያለው የኮዳ ውሃ ሳይሆን፤
የወገኖቻችሁ ደም ነው።
እነሆ ዛሬ፤ እጃችሁ ወደ ምግብ እና መጠጥ ሲመለስ፤ ህይወታቸው ያለፉ አሩጋውያን “ልጀ” አዋቂዎች እና ሕፃናት፤
“ወንድሜ” የምትበሉት ምግብ እና መጠጥ፤ ሥጋ እና ደሜ ነው!! እያሉ ይንጫጫሉ። ይህ፤ የህሊና ደወል፤
ወደተነሳችሁበት ወገንህ እና እውነተኛ ሙያችሁ ይመልሳችሁ። እየመሸ ያለው፤ ሳይጨልምባችሁ፤ እየተከላከላችሁት
ያለው የተንገዳገደው ሥራዓት ፍጻሜ ሳይደርስ፤ ዛሬውኑ ከወገኖቻችሁ ጋር ተሰለፉ። የህይወት እጣ ፈንታችሁን፤
የሙያ እድላችሁን፤ ከሥራዓቱ ጋር አፈር አታልሱት።
ለመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ፦
የትግራይ ነጻ አዉጭ ግንባር በተግባር እንደታየዉ፤ ወራሪ ቡድን በመሆኑ፤ ህዝቡን እየጨፈጨፈ፤ አንጡራ ሃብት
ከዉጭ ጠላቶች ጋር በመተባበር እየዘረፈ ያለ፤ አጥፍቶ፤ ጠፊ ቡድን በመሆኑ፤ ነገ ባንተ ሳይ ሳይደርስ ሁሉም
የኢትዮጵያ ህዝ ከጎንደር ወንድሙ/ እህቱ ጎን እንዲቆም መልክታችን እናስተላልፋለን። የሰሞኑ ወያኔ በጎንደር
ላይ የከፈተው ጦርነት፤ የተጠነሰሰው መቀሌ ላይ በተደረገው ሚስጥራዊ ስብሰባ ሲሆን፤ ቀመሩም፤ ጎንደርን
ደረጃ በደረጃ አጥቅተዉ፤ እንዴት በሌላ ክ/ሀገር የሚኖረውን አማራ እንደሚያጠፉ የወሰኑበት ሚስጢታዊ
ዶክሜንት በተጋለጠ ማግስት ነዉ።
አፈትልኮ የወጣው የሚስጢራዊ ዘገባዉ በአጭሩ እንደሚከተለዉ ነዉ።
1ኛ) ለትግራይ ህዝብና ድርጅቶች የትግራይን የበላይነት ማሳመን፤
2ኛ) ደካማና በጥፋት የተቀጡ ሰራተኞች ወደወልቃይት ጠገዴ ተሹመዉ እንዲሄዱ፤
3ኛ) የጤናም ሆነ የተለያዩ ባለሙያወች መለማመጃ፤ በዚሁ አካባቢ እንዲሆን፤
4ኛ) በዉጭ የሚደራጁትን የጎንደር ተወላጆች እንቃፋት መሆን፤ መከፋፈል፤
5ኛ) ከቤተሰብ እና ከማህረሰቡ ማግለል፤
የጎንደር ሕብረት
gonderhibrert72@gmil.com /website: www.gonderhibret.org
6
6ኛ) የወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች የንግድም ሆነ የትምርት እድል ከደጎንደር እንዲቋረጥ ማድረግ፤ ግንኙነቱ በጣም
እንዳሳሰባቸዉ፤
7ኛ) የሱዳን እና የትግራይን ግንኙነት ማጠናከር፤
8ኛ) ከጎንደር ታሪክ በላይ አኩስምን አጉልቶ ማሳየት፤
9ኛ) ከአጼ ቴወድሮስ ይልቅ የአጼ ዮሃንስን ሃያልነት ማስተዋወቅ፤
10ኛ) የሃይማኖት ሰባኪወች ትምህርት፤ ከአማረኛ ፍጹም ነጻ እንዲሆን ማድረግ፤ የጎንደርና የጎጃም ቋንቋን
ማጥፋት፤
11ኛ) በደጋዉ ጎንደር አካባቢ ከትግራይ አምጥቶ ማስፈር፤ እሴቶችን ማዳቀልና፤ የሚሉት ገሃድ የወጡት የወያኔ
ባለሥልጣናት ሴራዎች፤ የቅኝ ግዛት አላማን ለማሳካት የዘር ማጽዳት እቅዶች አካል ናቸው ።
ለምሳሌ እንደ ድጋፍ ልንጠቅሳቸው የሚገቡ እጅግ ብዙ የግፍ አይነቶች ቢኖሩም፤ የሰሞኑን አንድ ግፍ ብንጠቅስ፤
አንዲት በበሽታ ትሰቃይ የነበረች መጫት እህታችን፤ በህክምና ሙያ የሰለጠኑ የወያኔ ዶክተሮችን ጎንደር እንዲልኳት
ምርጫዋ መሆኑን ብትማጸንም፤ ሙያተኞቹ፤ ጥያቄዋን ከማጓተታቸውም በላይ ህክምና ሳታገኝ ሶስት ቀን ተከልክላ፤
መጨረሻ ነብሷ ሊወጣ መቃረቡን ሲያረጋግጡ ወደ ጎንደር መሄድ እንደምትችል ቢፈቅዱም፤ የደህንነት
ባለሥልጣኖች ደግሞ የበኩላቸውን፤ የዘረኝነት በቀል ለመወጣት፤ እህታችን እንኳዬሁሽ ጎንደር መሄድን በመምረጧ
የይለፍ ወረቀት ተከልክላ በሰላሣ (30) ዐመቷ ከዚህ አለም በሞት ተለይታናለች። ከዚህ የከፋ እጅግ አረመኒያዊ
የዘር ማጥፋት ጦርነት የለም፤ በየትም ዓለም አልተከሰተም።
ውድ የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ይህ በአንድ አካባቢ ያየነውን ክስተት፤ በዚህ ገጽ ላይ ለማስቀመጥ ሞከርን እንጅ፤
የዚህ ሥራዓት ግፍ እና በደል፤ እንዲሁም ጭፍጨፋ በሁሉም የአገራችን፤ ብሔረሰቦች ላይ መልኩን እየቀያየረ
ሲተገበር እያየን ያለነው ሃቅ ነው። በመሆኑም፤ ይህ አረመኔው የወያኔ ሥራዓት፤ አንድ በአንድ ለዘለዓለም
ከሚቀጠቅጠን፤ እና እኛም በተናጠል በየአካባቢያችን ለውጤት የማይበቃ ከንቱ መስዋዕትነት ከመክፈል ይልቅ
ሁላችንም በአንድነት ክንዳችን አጠናክረን መታገል እና የወያኔን እድሜ አሳጥረን፤ በምትኩ ሁላችንም በህግ ፊት
እኩል የምንተያይበትን ሥራዓት ማምጣት ይኖርብናል። በተለይም በጎንደር ሰፊዉን የማራ ህዝብ በደቡብ ሰፊውን
የኦሮሞ ሕዝብ ከዘር ማጥፋት አደጋ ለማዳን በአንድ ላይ የምንቆምበት ጊዜ የማይሰጠው አንገብጋቢ ወቅት ነዉ።
ይህ ዘርን መሰረት ያደረገ አደገኛ የወያኔ በጊዜ እና በቦታ ነጣጥሎ የማጥቃት ስልት፤ በየተራ ሁሉንም ጎሳዎች
ለመብላት፤ የታሰበ እና የተሰላ በመሆኑ፤ ሰፊዉ የኢትዮጵ ህዝብ ይህንን ዘርን መሰረት ያደረገ ጥቃት ለመመከት ወንድ
እሴት ሳይል፤ ዉርደት በቃን! ብሎ በአሸናፊነት ለመወጣት፤ ቆሞ ተራን ከመጠበቅ ይልቅ አሁኑኑ ሁሉም በአንድነት ለነፃነቱ
መነሳት አለበት።
በወያኔ ግፍ ግድያ፤ እስራት፤ ዘረፋ የተቆጨ እና ይህን መልክት የሰማ ሁሉ በያለበት ተመካክሮ በዉጭም፤ በዉስጥም ያካባቢ
መሪዉን መርጦ ኢትዮጵያን መታገድ ለነገ የማይባል ሃገራዊ ሃላፊነት ነዉ። እንዲሁም በአገር ቤት በጦር ሜዳ መሰለፍ
የጎንደር ሕብረት
gonderhibrert72@gmil.com /website: www.gonderhibret.org
7
የማይችል ሁሉ፤ ተማሪ አስተማሪዉ፤ ነጋዴዉ ገበሬዉ በአንድነት ቁሞ በገፍ እዬታፈሱ የታሰሩ ወገኖቻችን እንዲፈቱ እና ዘርን
መሰረት ያደረገ የወረራ ጦርነትን በማዉገዝ በነቂስ ወጥቶ ተቃውሞውን እንዲገልጽ ወገናዊ ጥሪያችን እናስተላልፋለን።
በመጨረሻም የፌደሬሽን ምክርቤት የወልቃይት ጠገዴን በትግራይ ክልል በጉልበት የተጫነበትን የማንነት ጥያቄ ጉዳይ መጋቢት
26/7/2008 በጻፈዉ የዉሳኔ ደብዳቤ በወያኔ ቀጭን ትዛዝ የወረደ መሆኖን ግልጽ ያደረገ ለአጣዳፊዉ መፍትሄ ያልሰጠ በህዝቡ ላይ
እየደረስ ያለዉን ጭፍጨፋ የማይገታ መሆኑን አረጋግጠናል። አፈና፤ ግድያ እያካሂዱበት ላሉት ወደነ አቶ አባይ ወልዱ ፍትህ አግኙ
ብሎ መምራት፤ በጎንደር ላይ የታወጀዉ ጦርነት ለመተግበር ፍቃድ የሰጠ ብጣሽ ወረቀት ነዉ የሚል እምነት አድሮብናል። ይህም
ከተስፋፊዉ ወያኔ የበላይነት ሌላ መንግስት ላለመኖሩ ትልቅ ማስረጃ ሲሆን፤ አገራችን ወደ እርስ በርስ ጦርነት የሚጋብዝ አደገኛ ውሳኔ
ነው። ህዝብ አቤቱታዉን የሚሰማ መንግስት ካጣ፤ አዲስ የህዝብ መንግስትን መፍጠር የግድ ይላል። ወያኔ ከጫንቃችን ላይ ሁኖ
ለዘመናት መጋለቡ በአስቸኳ ማክተም አለበት።
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
የጎንደር ሕብረት።
No comments:
Post a Comment