Tuesday, April 19, 2016

Abebe Gellaw የፌስቡክ አሉታዊ ትግል


ጭንቅላት ያላቸው ሰዎች አስበው ተጨንቀው እንደ ፌስቡክ ያለ የሃሳብ መለዋወጫ፣ የተራራቀን ማቀራረቢያ፣ የነገርና የምስል መቀባበያ ፈጥረው እኛንም ተጠቀሚ አደረጉን። አንዳንዶች ታዲያ ይቺን ምኑንም ምናምኑንም የመለጠፍ ትንሽ ስልጣን በመጠቀም ሌሎችን ሲወርፉ፣ ስድብ ሲያዥጎደጉዱ፣ ሲከፋፍሉና መርዘኛ ቃላትን ሲያዘንቡ፣ አገራቸውንና ህዝባቸውን ሲሰድቡ፣ የራሳቸውን አወድሰው የሰውን ሲያራክሱ፣ በጅምላ ሲፈርጁና ሲወንጀሉ ወርቃማ ጊዚያቸውን ሲያጠፉ ያታያሉ፤ ይህንን ከንቱ ንቅናቄ "ትግል" ይሉታል። 
ትርጉሙ ከገባን ትግል ዘመድ አዝማዱ፣ አላፊ አግዳሚው ላይ የስድብ ናዳ ማውረድ አይደለም፣ መለያየት አይደለም፣ መናቆርና ማናቆር አይደለም፣ መሳደብና ማሰዳደብ አይደለም፣ አዋቂ መስሎ ባዶነትን መግለጥ አይደለም። ትግል በዋነኛነት የሚፈተነው በተግባር ነው። ላመኑበት በጎ አላማ መፋለም ማለት ነው። በሚቻል አቅም ሁሉ መስዋትነት መክፈል ማለት ነው። ትግል ዛሬ ላይ ቆሞ ነገን አልሞ አስቸጋሪ ጉዞን መጓዝ ማለት ነው። እኛ ከህዝብ ጠላቶች ተሽለን ካልተገኘን አሉታዊ የፌስቡክ ትግላችን ከንቱ ብቻ ሳይሆን ጎጂ መሆኑን መገንዘብ በትንሹም ቢሆን ያስፈልጋል። 
Negativity is the enemy of creativity, as they say.

No comments:

Post a Comment