ከሸግዬ ነብሮ (ኢጆሌ ባሌ)
“ሀገር አጥፊው አረም በሀገሬ ሲስፋፋ፣
ሁሉም ተዳከመ የሚያርመው ጠፋ፣
የጊዜ ጉዳይ ነው እኔ አለቆርጥም ተስፋ፣
ሀገሬ ነው የሚል ኢትዮጵያዊ ሁሉ፣
ጥቃቱ ይሰማው ሲቆረስ አካሉ።”
ከሊቀ ማዕመራን አበባው ይግዛው “ወይ ሀገሬ” ከሚለው ግጥም የተወሰደ።
የአውሮፓ ቅኝ ገዥዎች አፍሪካን እንደ ቅርጫ ሥጋ ለመቀራመት በተነሱበት ወቅት በተለያዩ ሀገሮች እገራቸውን ያስገቡት በሀይማኖት አስተማሪነት ሰም የቄስ ካባ አልብሰው የመረጃ (ሰላይ) ሰዎቻቸውን በመላክ ነው።
ማርቲን ሉተር የተባለው የተባለው የጀርመን የሀይማኖት ሊቅ እ.ኢ.አ. በ1517 የፕሮቴስታንት ሃይማኖት መሻሻል አለበት በሚል ያቀረበው ፅንሰ ሃሳብ ተቀባይነት አግኝቶ ዛሬ ሉተራን የሚባል የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ዋናው ቅርንጫፍ እንዲፈጠር አድርጓል። እዚህ ላይ የሉተራን ቤተ ክርስቲያን፣ የጀርመንና የኦሮሞ የሉተራን ቤተክርስቲያን ተከታዮችን ቁርኝት ማስተዋሉ በኋላ ለምንመጣበት ዋናው ጉዳያችን ይጠቅማል።
ጀርመን ምሥራቅ አፍሪካን የራሷ ለማድረግ ዓይኗን በጣለችበት ወቅት ሃይማኖት የለሽ (ፓጋን) ወይም ባህላዊ ዕምነት ይከተሉ የነበሩትን የደቡብ ኢትዮጵያ ወገኖቻችንን የሉተራን ሃይማኖት ተከታይ ለማድረግና ከሕዝቡ ጋር በሃይማኖት ሽፋን ወዳጅነት ፈጥሮ አስፈላጊውን ቅድመ ቅኝ ግዛት ዝግጅት ለማጠናከር የቄስ ካባ አልብሳ የላከቺው ዮሐን ሉድዊግ ክራፍ የተባለ የመረጃ መኮንኗን ንው።
ዮሐን ብሩህ አዕምሮ፣ ተመራማሪ፣ የሃይማኖትና የሥነ – ቋንቋ ከፍተኛ ችሎታ ያለው ግለስብ ሲሆን፣ እ.አ.አ. ከ1837 እስከ 1842 ኢትዮጵያ ውስጥ በቆየበት ወቅት አማርኛ፣ ኦሮሞኛና ግዕዝ አጥንቶ የመጀመሪያውን የዮሐንስና የማቴዎስ ወንጌል በኦሮሞኛ ተርጉሞ ለንባብ አብቅቷል። ሆኖም ጥንታዊ የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሃይማኖት በብዙ መላዕክቶች በማመን ላይ ያተኩራል እያለ ይተች ስለነበረና የሉተራን ሃይማኖትንም ለማስፋፋት ያለመው ግብ እንደተጠበቀው ስላልተሳካለት ወይም ለሌላ ተልዕኮ ፊቱን ወደ ኬንያና ታንዛኒያ አዙሯል። ቢሆንም ዮሐን የኦሮሞ ተወላጆችን ሞምባሳ ላይ እየተገናኘ የሃይማኖት ስብከቱንና የተደበቀ የስለላ ተግባሩን ከማከናዎን አልተቆጠበም። በሀገሩ በጀርመንና በእንግሊዝ ሀገር ቆይታ ካደረገ በኋላም እ.አ.አ. ብ1867/68 አፄ ቴዎድሮስን ሊዎጋ ከመጣው በጄኔራል ሮበርት ናፒዬር ከሚመራው የታላቋ ብሪታኒያ ጦር ጋር አብሮ በመዝመት አፄ ቴዎድሮስ መስዋዕት ከሆኑባት መቅደላ ድረስ ተጉዟል።
ኬንያ/ናይሮቢ የሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ ሕንፃ በእርሱ ስም Ludwig Krapf House ተብሎ ይጠራል። አዎ! ለእኛ መርዝ ተከለ፤ ለእርሱ ግን በመታሰቢያንት ሕንፃ ተገነባለት።
ዮሐን ክራፍ ለሀገሩ መንግሥት ባደረገው የመረጃ ጥናቶች ውስጥ የሚከተሉት በአንኳርነት የሚጠቀሱ ናቸው፦
- የምሥራቅ አፍሪካንና የመካከለኛው ምሥራቅን ከዚያ በመነሳት መቆጣጠር ይቻላል፤
- የእስልምና ሃይማኖት፣ በአረብ ሀገሮችና በአፍሪካ የሚያደርገውን መስፋፋት መግታት ይቻላል፤
- የምሥራቅ አፍሪካ ነዋሪዎችን በክርስትና ሃይማኖት በማጥመቅ የጀርመን ወዳጅ አድርጎ የጀርመንን የበላይነት ማስፈን ይቻላል፤
- ከላይ የተዘረዘሩትን ሁኔታዎች ለማሳካት በየቦታው ተራርቆ የሠፈረውን የኦሮሞ ብሔረሰብ በካርታ ከልሎ ከኢትዮጵያ ነጥሎ ማውጣት የሚል ግምገማ ነው ያቀረብው።
ግንጠላውንም ለማካሄድ ብሔረሰቡን ከታሪክ ለማራራቅና ከሌሎቹ በሔረሰቦች ጋር ቅራኔ እንዲፈጥር ለማድረግ ጋላ የሚለው ቃል በሐበሾች ለአረቦች የተሰጠና ትርጉሙም ስደተኛ ማለት ነው ሲል ሰብኳል። የጊዜው አክራሪ የኦሮሞ ፖለቲከኞች ጋላ የሚለው ስያሜ የኦሮሞን ሕዝብ ለማንቋሸሽ በአማሮች የተሰጠ ነው ቢሉም፣ ቃሉ ስደብ እንዳልሆነ ከዚህ መረዳት ይቻላል። የኦሮሞን ታሪክ ያጠኑ ተመራማሪዎች ጋላ ማለት በሱማልኛ እስላም ወይም ክርስቲያን ያልሆነ ማለት ነው። አሁንም ከዚሁ የሱማልኛ ቋንቋ ሳንዎጣ በሱማልኛ “ጋል” ማለት ግመል ማለት ሲሆን፣ ጋላ የሚለው ሰምም ከዚሁ ጋል ከሚለው ስም የወጣና “ባለግመሎቹ” እንደማለት ነው የሚሉም አሉ። ከኦሮሞኛ ቋንቋ “ገላ” ከሚለው ግሥ የወጣና ትርጉሙም ቤታችን ሄድን ወይም ገባን ማለት ነው የሚሉም ሲኖሩ፣ በየትም ቦታ በስድብነት አልተመዘገበም።
ዮሐን ባቀረብው ሃሳብ መሠረት የብሔሩ መጠሪያ ኦርማኒያ እንዲሆን በ1860 ዓ.ም. የተወሰነ ሲሆን፣ ኦሮሞ እና ኦሮሚያ የሚሉት ስሞች የመጡት ከዚሁ ነው። ትርጉሙንም ኦርማ ወይም ኦሮማ ማለት ጎበዝ ማለት ነው ሲል ተንትኗል። በምሥራቅ ኬንያ በታችኛው ጣና ወንዝ የሚኖሩ ዘላኖች ኦርማ ይባላሉ። የኦሮሞ ነገድ ወደ ኢትዮጵያ ፈልሶ ከመግባቱ በፊት መነሻው ከዚህ ሊሆን ይችላል የሚሉም አሉ።
ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረው ኦሮሞ፣ ኦሮሚያ፣ የኦሮሚያ ካርታና ኦሮሚያ ራሷን የቻለች ሀገር መሆን አለባት የሚሉት ጠንሳሽ በጀርመን መንግሥት ተልኮ አካባቢውን በቅኝ ግዛት እንዴት መያዝ እንደሚቻል ያጠናው የጀርመኑ ሰላይ ዮሐን ሉድዊግ ክራፍ ነው።
ጀርመኖች የብሔረሰብ መጠሪያ ስም ሰጡ፤ የኦሮሚያ ግዛት ብለው ካርታ ሠሩ፤ በመጨረሻም ኦሮሚያ መገንጠል አለባት አሉ። የጀርመን ሉተራን ቤተክርስቲያን ብዙ ልጆችን (የአሁኑ አዛውንቶችን) በሀገር ውስጥም ሆነ ሀገራቸው ወስደው በማስተማርና በግንጠላ መርዝ በመበከል ኦሮሚያ በኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት ሥር ነች የሚል አስተሳሰብ በአንዳንድ የኦሮሚያ ተወላጆች ጭንቅላት ውስጥ አስርፀዋል። ለዚህ አስተሳሰብ የተንበረከኩ ጥቂት የኦሮሞ ልጆች ከአክራሪ የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ጋር በመሆን ከ50 ዓመታት ላላነሰ ጊዜ ተንቀሳቅሰው እነርሱ በአሜሪካና በአውሮፓ በድሎት እየኖሩ ብዙ የኢትዮጵያ ልጆችን እርስ በእርስ አባልተው ከፍተኛ የሕይዎት መስዋዕትነትና የንብረት ውድመት እንዲደርስ አድርገዋል። ለዚህ እኩይ ተግባራቸውም እንደ ሀሰል ብላት ያሉና የጀርመን የሐሰት ቄሶች በሃይማኖት ስም የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የሎጂስቲክ ድጋፍ ያደርጉላቸዋል።
ኢትዮጵያ ከምትታወቅባቸው አንዱ በቅኝ አለመገዛቷና የራሷ የሆኑ ቋንቋዎችን መጻፍ የሚያስችል ባለፊደል ሀገር መሆኗ ነው። ማንኛውም የሀገሪቱ ብሔረሰብ ቋንቋ በሀገሪቱ በነፃነት ይነገራል፤ በግዕዝ ፊደልም ሊጻፍ ይችላል። በራስ ከመኩራት ይልቅ በባርነት ወይም በቅኝ ግዛት ከተያዙ ሀገሮች ደረጃ ዝቅ ማለትን የመረጡ ለኦሮሞ ሕዝብ ቆመንለታል ያሉ ፈረንጅ አምላኪዎች የኢትዮጵያ ጠላት ከሆነው ወያኔ ጋር በመሆን ክ1991 ጀምሮ ኦሮሞኛ የሚጻፍው በላቲን ፊደል ሆኗል።
ቋንቋ እንደ ዛፍ የተተከለ፣ ካልቆረጡት የማይነቃነቅ ደረቅ አይደለም። ያድጋል፣ ይዳብራል፣ የሰው ልጅ መጠቀሚያ እስከሆነ ድረስ ፈሩን ሳይለቅ ይሻሻላል። ያሉት የግዕዝ ፊደላት ኦሮሞኛን ሙሉ በሙሉ ለመጻፍም ሆነ ለማናበብ አይበቁም እንኳን ቢባል፣ በግዕዝ ፊደላት ላይ ፊደሎችንና አናባቢዎችን ጨምሮ መጠቅም ሲቻል፣ የላቲን ፊደል ነው ለአፋን ኦሮሞ የሚመቸው በሚል ኢትዮጵያዊነትን ለማፍረስ ሰንካላ ምክንያት በማቅረብ በፈረንጆች ቅኝ ሳይገዙ በግድ ጌቶቻችን ናችሁ በማለት እጅ መስጠት ታምኖበታል። በግዕዝ “ጨ” እና “ሸ”ን የመሳሰሉ ፊደላት አልነበሩም። የአማርኛ ቋንቋን ሙሉዕ ለማድረግ ሲባል ግን ተፈጥረው እንጠቀምባቸዋለን።
በቅርቡ ቪዥን ኢትዮጵያ በተባለው ስብሰባ ላይ ስለ ቁቤ ተነስቶ ፕ/ር እዝቅኤል ጋቢሣ ኦሮሚኛን በላቲን ፊደል መጠቀም የተጀመረው ከ1840ዎቹ ጀምሮ ነው ብለዋል። ይህ መረጃ የሚያመለክተው የኦሮሞ ሊሂቃን እንደሚሉት በእነርሱ ጥናት ተደርጎበትና የኦሮሞ ሕዝብ ተዎያይቶ አምኖበት የተቀበለው ሣይሆን ቁቤ ኦሮሞ፣ ኦሮሚያ የሚለውን ባወጣው በጀርመናዊው ዮሐን ክራፍ የተሰጠ መሆኑን ነው። ከትልቅነት ትንሺነትን መምረጥ ይሉታል ይህ ነው።
ወያኔ የአማራን መሬት ከጎንደርና ወሎ ወስዶ ሕዝቡን በግዴታ ትግሬ ነህ ብሎታል። የሕዝብ ቆጠራ ብሎ በሠራው ማጭበርበር የአማራውን ቁጥር ቀንሶ ለማቅረብ ያደረገው ሙከራ ስለተነቃበት የሕዝብ ቆጠራው ተቀባይነት አጥቷል። በመሆኑም በወያኔ ዘመን በኢትዮጵያ ትክክለኛ ይሕዝብ ቆጠራ ስላልተካሄደ የኢትዮጵያ በሔረሰቦች፣ ባጠቃላይም የኢትዮጵያ ሕዝብ ይህን ያህል ነው ብሎ መናገር አይቻልም። አንድን ቋንቋ መናገር የዚያን ብሔረሰብ አባላትነትን አያቀዳጅም። (ዝርዝሩን በኋላ እንመጣበታለን።)
ኦሮሚያ ውስጥ ሳይወዱ በግድ ኦሮሞ ናችሁ ተብለው የተፈረጁ ኦሮምኛ የሚናገሩ የሌላ ብሔረሰብ አባላት እንደሚገኙ ሊሠመርበት ይገባል። ስለሆነም ኢትዮጵያ ውስጥ የኦሮሞ ብሔረሰብ ቁጥር ይህን ያህል ነው፣ ከሁሉም ብሔረሰብ ይበልጣል ብሎ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። የአፋን ኦሮሞ ተናጋሪዎች ቁጥር ግን ከፍተኛ ስለሆነ አፋን ኦሮሞ ሁለተኛ በሔራዊ ቋንቋ እንዲሆንና ከሁለተኛ ደረጃ ጀምሮ ካሪኩለም ውስጥ ገብቶ እንደ አማራጭ ትምህርት እንዲሰጥበት መጠየቅና መታገል የኦሮሞ ሊሂቃን ተግባር መሆን ሲገባው፣ ዮሐን ክራፍ ያዘጋጀውን የኦሮሚያ ካርታ ይዘው አትላንታና ሚኒሶታ በመሯሯጥ ጊዜያቸውን ሲያባክኑ ይታያሉ።
ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛትነት ያልተያዘች ለረጅም ዘመን ነፃነቷንና ሉዐላዊነቷን ባሏት በርካታ ብሔረሰቦችና ማኅበረሰቦች አስጠብቃ የኖረችና የምትኖር ሀገር ናት። “History is more than the path left by the past, it influences the present and can shape the future” Malcolm X.
የኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ታሪክ ለማጥላላት የሚሞክሩ ከሃዲዎች እንድሚሉት ከሰሜን በመጡ መኳንንት የተመሠረተች ሳትሆን ሕዝቦቿ ልዩነት እንኳን ቢኖራቸውም አንድነታቸውን የሚፈታተን ሁኔታ ሲፈጠር አንድ ላይ በመቆም ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር በደማቸው ዋጅተው፣ አጥንታቸውን ከስክሰው አቆይተዋታል። በየትኛውም ሀገር በፊውዳል ሥርዓት የመሳፍንት ፍትጊያ እንደነበረ ሁሉ፣ በኢትዮጵያም የተከሰተ ሁኔታ ነው። ይህን ግን እንደ ኢትዮጵያ የታሪክ መሠረት አድርጎ የጥንታዊት ኢትዮጵያን የረጅም ዘመን ሕልውና ለመናድ የሚጠቀሙብት የእናት ጡት ነካሾች ብቻ ናቸው። የዛሬይቱ ኢትዮጵያ ብዙ ወጣውረዶችን ያዬች፣ በተለያዩ ጦርነቶች ልጆቿ የተሰውባት፣ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ አንዳንድ ጎሣዎቿ የጠፉባት ሀገር ናት።
በ1517 አህመድ ኢብን ኢብራሂም (በተለምዶ ግራኝ መሐመድ) የወረራ ጦርነት የጀመረው በምዕራብ ሐረርጌ ሲሆን፣ ዘንተራ ሰሜን ጎንደር ጣና ሃይቅ አካባቢ በአፄ ገላውዲዎስ ጦር እስከተገደለበት 1535 ዓ.ም. ድረስ ለ19 ዓመታት ከፍተኛ ጥፋት ፈጽሟል።
ግራኝ አህመድን በመከተል ከ1530 ዓ.ም. ጀምሮ በቦረና በኩል ነው የመጡት የሚባሉ የኦሮሞ ወራሪዎች (የኦሮሞ ልሂቃን ፍልሰት ይሉታል) እግረመንገዳችወን ያገኟቸውን የሌላ ብሔረሰብ አባላትን በመደፍጠጥ እስከ ትግራይ ዘልቀዋል። በዚህ ሂደት የጋፋት ነገድ ሙሉ በሙሉ ጠፍቷል፤ ወይም በኦሮሞው የሞጋሣ ሥርዐት ሳይወዱ ተገድደው ኦሮሞ ሆኗል። የሚያ ነገድ ተወላጆችም ተመናምነው በዝዋይ ሐይቅ ደሴት ላይ እንዲወሰኑ እንደተደረጉ ቢነገርም መኖራቸው የተረጋገጠ አይደለም። ሃዲያዎችና ከምባታዎች ከግዛታቸው ከባሌና ከአርሲ ተፈናቅለው በደቡብ ምዕራብ ሸዋ በስደተኝነት አነስተኛ ቦታ ይዘው እንዲኖሩ ተደርገዋል። አርጎባዎች፣ ቀቤናዎች፣ ወርጅዎች፣ አላባዎች፣ ሲዳማዎች፣ የኦሮሞ ወረራ ሰለባ ሆነው ሳይወዱ በግድ ኦሮሞ እንዲሆኑ ወይም እንዲሰደዱ ሆነዋል። የዳውሮና የገሙ ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቅለው ግዛታቸው በኦሮሞዎች ተወስዶባቸዋል።
በዘመናችን ኦሮሚያ ተብሎ የተከለለው ቦታ የተለያዩ የብሔር ብሔረሰቦች ጥንቅር ውጤት ነው። የኦሮሞ ወራሪዎች የሌሎች ብሔረሰቦችን ግዛት ሲይዙ ነዋሪዎችን ኦሮሞ ከማድረግ ጀምሮ የቦታዎችን መጠሪያ ስም ቀይረዋል። ፈጠጋር = አርሲ፣ ግራሪያ = ሰላሌ.፣ ገንዝ = ጅባትና ሜጫ፣ ኢሊባቡር = እናሪያ፣ ሌቃ (ምሥራቅ ወለጋ) = ዳሞት፣ ቢዛሞ = ቄለም (ምዕራብ ወለጋ) ወ.ዘ.ተ.
የቅኝ ገዥ ሀገራት ባህሪን ስናይ አንዱን ሉዐላዊ ሀገር ከሌላ ቦታ መጥቶ በጉልበት ነጥቆ ማስተዳደርንና የተፈጥሮ ሀብትን መዝረፍን ያመለክታል። ቅኝ ገዥዎች ለመግዛት እንዲያመቻቸው የራሳቸውን ቋንቋ፣ ሀይማኖት፣ ባህልና አኗኗር በሚገዙዋቸው ሀገሮች ላይ በግድም ሆነ በውድ ተጭነው ያሰፍናሉ። ኦሮሚያ ተብሎ በሚጠራው ክልል የነበሩ ብሔረሰቦች ነገዳቸው ጠፍቶ ባህላቸው ተረስቶ ማንነታቸው ተቀይሮ እንዲኖሩ ተደርገዋል። የገዳ ሥርዓትን በግድ እንዲቀበሉ ተደርገዋል። በመሀሉም ባህሌን፣ ወጌን፣ በማለታቸው የደረሰባቸው ጉዳት ይህ ነው ኣይባልም። ከዚህ የበለጠ ከቅኝ ገዥነትና ተገዥነት በምሳሌነት የሚጠቀስ አይኖርም። ከላይ በዝርዝር ለማሳየት እንደተሞከረውም በዓለም ላይ እራሷን የቻለች ኦሮሚያ የተባለች ሀገር አትታወቅም። ኦሮሚያም ኦሮሞዎች በታሪክ አጋጣሚ የሚኖሩባት ሀገር ናት እንጅ የኦሮሞዎች ብቻ አይደለችም።
የ16ኛውንና የ17ኛውን ክፍለ ዘመን የኢትዮጵያን ታሪክ ስንመለከት የኦሮሞን ብሔረሰብ መስፋፋት እናጤናለን። በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞ ብሔረሰብ የሚገኝበት መሬት ወይም ኦሮሚያ ተብሎ የሚጠራው የኩሽ ቤተሰብ ብቻ ሳይሆን፣ የሴማውያንም እንደነበረ ነው በታሪክ የሚታወቀው። የዎራሪዎቹ ዘመናት የሚታወቁት በተነሱት የኦሮሞ የጦር አለቆች ወይም መኳንንቶች መጠሪያ ነው።፡ የዘመን አቆጣጠሮቹ እንድ አውሮፓውያን አቆጣጠር ናቸው። መልባ 1522 – 1530፣ ሙደና 1530 – 1538፣ ኪሎሌ 1538 – 1546፣ ቢፎሌ 1546 – 1554፣ መሰሌ 1554 – 1562።
የኦሮሞ መስፋፋት እስከ ራያ አዘቦ ድረስ የዘለቀበት ሁኔታ ነበረ። የየጁ ኦሮሞ ባላባቶች የአማራውን፣ የትግሬውንና የአገውን ግዛት ተቆጣጥረዋል። ከአፄ ቴዎድሮስ በፊት የየጁ ኦሮሞ ዳይናስቲ አባ ሴሩ ጉዋንጉል፣ ቀዳማዊ ራስ አሊ፣ ራስ አሊጋዝ፣ ራስ ጉግሣ መርሶ፣ ራስ ይማም፣ ራስ ማርየ፣ ራስ ዶሪ፣ ዳግማዊ ራስ አሊ፣ የሰሜን ኢትዮጵያ ገዥዎች ነበሩ። በአንድ ወቅት የጎንደር ቤተመንግሥት ቋንቋ ኦሮሞኛ ነበር። የአፄ ቴዎድሮስ ባለቤት ተዋች አሊ፣ የአፄ ምኒልክ ባለቤት እቴጌ ጣይቱ ብጡል፣ የራስ መንገሻ ባለቤት ከፋይ ወሌ፣ የንግሥት ዘውዲቱ ባለቤት ባለቤት ራስ ጉግሣ ወሌ፣ የትግራይና የባህረነጋሽ ገዥ የነበሩት ራስ ውቤ የየጁው የራስ ጉግሣ መርሶ ዘር ናቸው።
በምኒልክ ዘመነ መንግሥት የሰው ልጅ የደረሰበት የዕድገት ደረጃ ፊውዳሊዝም ነው። በየትኛውም ሀገር የተስፋፊነት ጦርነቶች ተካሂደዋል። የሚኒልክ አካሄድ የሚለይበት ግን የኢትዮጵያን ግዛት አንድ ላይ አጠቃሎ አሀዳዊ መንግሥት መሥርቶ በዘመናዊ ሥርዐት ማስተዳደር ነበር።፡ በጊዜው ዲሞክራሲ ምርጫ የሚባል የሚታሰብ አልነበረም። ባለጡንቻ እየተዋጋ፣ እያስገበረ፣ የጎሣ መሪዎችን እየጣለ የራሱን አስተዳደር ይመሠርታል። በምኒልከም የተደረገው ኦሮሞዎች በጡንቻ እየደፈጠጡ የመጡትን ሕዝብ ማስመለስና አንድ አድርጎ ማስተዳደር ነው። በመሀሉ መገዳደል፣ መማረክ፣ መታሠር የሚጠበቅ ነው። በወያኔ የተጨመረው የጡት ቆረጣ የቆርጦ ቀጥል ታሪክ ነው። ጡት ቆረጣና የወንድን ብልት መስለብ የሃይማኖት የለሽ (የባህላዊ ዕምነት ተከታዮች) ባህል ነው። የወንድ ብልት ተቆርጦ ልጃገረድ ለማግባት እንደግዳይ የሚቀርብበት ቦታ የት እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀው ነው። ሚኒሊክ ሀገር በመክዳት ለጣሊያን አድረው የኢትዮጵያ አርበኞችን የወጉ ትግሬዎችን ግራ እግርና ቀኝ እጅ (የተንበረከከበትን ግራ እግርና ምላጭ የሳበበትን ቀኝ እጅ) እንዲቆረጥ ማድረጋቸው በፎቶ የተደገፈ ማስረጃ የሚቀርብበት ንው። የወያኔ መንግሥት የአያቶቹን አሳፋሪ ተግባር ስለሚያውቅ ለተቆረጠው እጅና እግር ሀውልት ልትከል ሳይል የአማራና የኦሮሞን ብሔረሰቦች ለማለያየት በተቆረጠ እጅ ላይ ጡት አስቀምጦ በአርሲ ዞን ሂጦሳ ወረዳ በኦሮሞና በአማራ ሕዝብ ላይ ሰቆቃ በፈፀሙ የኦፒዴኦ መሪዎች በነጁነዲን ሳዶ አማካኝነት የአኖሌን ሀውልት ተከለ። የዋሆችም ተደሰቱ፤ ጣታቸውንም በሌላ ብሔረሰብ ላይ ላይ ቀሰሩ። ወያኔም እንደባለውለታ ተቆጥሮ የኦሮሚያን መሬት ለአረቦችና ሕንዶች ሲቸበችብ ዝም ተባለ።
ምኒልክ ወደ ደቡብ በዘመቱበት ወቅት የአንድ ብሔር ወታደሮችን ብቻ ይዘው አልዘመቱም። ከጦር አዛዥ እስከ ተራ ተዋጊነት የሁሉም ብሔረሰቦች ተሳታፊነት አለበት። የጅማው አባ ጅፋር 30 ሺህ ጦር ይዘው እንደዘመቱ፣ ራስ ጎበና ዳጨና ባልቻ … ወ.ዘ.ተ. የጦር አዝማቾች እንደሆኑ ነው የሚታወቀው። የነፍጠኛ አስተዳደር አሰፈኑ ለሚባለው ነፍጥ መሣሪያ፣ ነፍጠኛ መሣሪያ ለታጠቀ የሚሰጥ ስያሜ ነው። ነፍጠኛ የሚለው ቃል ጎሣን ወይም ብሔርን አያመለክትም፤ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ የትግሬ፣ የጋሞ፣ የወላይታ፣ የአፋር ወዘተ ነፍጠኛ አለ። በ1938 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ዘመናዊ የመከላካያ ኃይል እስከሚመሠረትበት ጊዜ ድረስ መሣሪያ ታጥቆ ዳር ድንበር የሚጠብቀው ሁሉ ነፍጠኛ ነበር የሚባለው።
የተለያየ ስም የተሰጠው የአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት የፈጠረው አስገባሪ፣ ጢሰኝንት ወዘተ. ባጠቃላይ ፊውዳሊዝም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጊዜያዊ ወታደራዊ አስተዳደር ደርግ የካቲት 25 ቀን 1967 ዓ.ም. የወጣው የመሬት ላራሹ አዋጅ ለመጨረሻ ጊዜ ያንኮታኮተው መሆኑ እየታወቀ ከሌላ ባላጋራ ወይም ወያኔ ጋር ከመፋለም ይልቅ ስለፊውዳሊዝም ማላዘኑ ጥቅሙ ምን እንደሆነ አይታወቅም።
Inferiority complex ወይም የበታችነት ስሜት መጠናዎት በራስ ካለመተማመን የሚመጣ የአዕምሮ መታዎክ ነው። ሕመሙ ልጅ አዋቂ፣ ወንድ፣ ሴት፣ የተማረ፣ ያልተማረ ሳይለይ በየትኛውም ሰው ላይ ይከሰታል። የህክምና ባለሙያ ሳያማክሩ በራስ ለመወጣት የሚደረግ ትንቅንቅ ለሌሎች የጥላቻና የአውሬነትን (aggressive) ባሕሪን የማሳየት ሁኔታ ይፈጥራል።
በውጭ የሚኖሩ የተማሩም ሆኑ ያልተማሩ አንዳንድ የኦሮሞ የፖለቲካ አክቲቪስቶች ባሕሪ በዚህ ይገለጣል። (“I am Oromo first” የሚለው የጃዋር መሐመድ አዲስ መፈክር ከዚሁ የመነጨ ነው። አንገቷ ላይ የዋርካ ምስል ተነቅሳና የሱን መፈክር ከሥሩ አስጽፋ አንድነትን የሚደግፉ ኢትዮጵያወያንን ስትዘልፍ የምትውለውን ጀርምን የምትገኘው አደገኛ ቦዘኔ ሁኔታ የህመሙን ከፍተኛ ደረጃነት ያሳያል።)
በቅርቡ ለንደን ላይ በተደረገው የኦሮሞ የሕግ ባለሙያዎች ስብሰባ ላይ በጥቂት ግለሰቦች የተንፀባረቀውም ይህ ባሕሪ ነው። አማራውን ከሌላው ብሔረሰብ ከሚገባው በላይ አግዝፍው በማየት የራሳችውን ብሔረሰብ በማሳነስ ርቀው በመሄድ ከፊታችን ልጆቻችንን በመፍጀት ላይ ያለውን የጭራቆች መንግሥት (ወያኔን) በጋራ ተባብሮ ከመጣል ይልቅ “የእኛ ዓላማ ኢትዮጵያን አፈራርሶ ኦሮሚያን መገንጠል ነው” ይላሉ። ኢትዮጵያን በማግሥቱ ሄደው እንደ ቦረና ሣር ቤት እንደሚያፈራርሷት ሁሉ። ኢትዮጵያ ማለት አማራ፤ አማራ ማለት ኢትዮጵያ እንደሆነች በአዕምሮአቸው የሠረፀው የትንሽነት ሕመም ስለሚነግራቸው ኢትዮጵያ ከ80 በላይ ብሔረሰቦች ሀገር መሆኗን ይረሱታል። በእነሱ አስተሳሰብ ሰሜኑ የትግሬና የአማራ፣ ደቡቡ የኦሮሞ ነው። ሌላው ብሔረሰብ አይነሳም። ኢትዮጵያ ባቀፈቻቸው ብሔረሰቦች አጥንትና ደም የተገነባች በማንም ህመምተኛ ጩኸት የማትነቃነቅ መሆኗን ሊረዱ የሚችሉት የህክምና ባለሙያ ዘንድ ሄደው በመታከም በራሣቸው መተማመን ሲችሉ ብቻ ንው። እነኚህ የዞረባችው ሀገር አጥፊዎች የወያኔው የኦሆዲድ አባላት “de-Amharicization” የሚል አዲስ ቃል ፈጥረው ኦሮሚያን ከአማራው ጋር ከሚያገናኙ ባህላዊ ትሥሥሮች እናለያያለን በማለት ውጥን መያዛችውን ለማዎቅ ተችሏል። በእነርሱ አባባል የአማራ ዶሮ ወጥ መብላትና የዶርዜ ጥበብ መልበስ በኦሮሞው ላይ አማራው ያሳደረው የባህል ተፅዕኖ ነው። እነርሱ በእንግሊዝ ሱፍና በአሜሪካ ጂንስ ተከሽነው ሲወጡ ግን የፈረንጆቹ የአለባበስ ባህል ተገዢ ነን አይሉም። ይህ ሁሉ ዝግጅት ኦሮሚያን ገንጥሎ ሥልጣን ላይ ለመቀመጥና አዲስ አበባን ከያዙ በኋላ የወያኔ ጄኔራሎች ዘርፈው የገነቡትን ሕንፃ እንወርሳለን በሚል ቅዠት ውስጥ ስለሚዋኙ ነው።
እጄ ጠባብ፣ ኩታና የጥበብ ቀሚስ የአማራው ብቻ ሳይሆኑ፣ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ተመራጭ የዓመት በዓል የክት ልብሶች ናቸው። ሥራው የዶርዜ ሲሆን፣ ዘሩን የማይናገር መዋቢያና መታዎቂያችን ሆኖ ሳለ ኢትዮጵያዊነትን ለማጥፋት የተነሳው ወያኔ በኦሎምፒክ ሜዳ የየሀገሩ ስፖርተኞች የሀገራችውን የባህል ልብስ ለብሰው ሲያልፉ የእኛዎቹ ግን በስፖርት ቱታ እንዲሰለፉ አድርጓል። የሚሰጠውም ምክንያት የኢትዮጵያ የባህል ልብስ የአማራ የባህል ልብስ ነው የሚል ነው።
የኦሕዴድ አባላት፣ የአሁኖቹ የወያኔ ተቃዋሚ የኦሮሞ ሊሂቃን ነን ባዮች አቋም ጌቶቻቸው በአዕምሮዎቻቸው ላይ የሠሩት የአዕምሮ አጠባ (Brain wash) ውጤት ነው።
ባለፈው ጊዜ በዩናይትድ ኪንግደም ለንደን ከተማ የኦሮሞ የሕግ ባለሙያዎች ማህበር የጠራው የሁለት ቀን ጉባኤ ተካሂዷል። በስብሰባው ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ወየሳና በጸሐፊው በአቶ ሁንዴ ዱጋሣ አባባል የስብሰባው ዓላማ በኦሮሞ ድርጅቶች መካከል ያለውን ሀሳብ ለማቀራረብ ከዚያም ወደፊት ከሌሎች የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ጋር ተቀራርቦ አንድ ላይ ለመሥራት ነው። ቀጣዩም ስብሰባ በአትላንታ እንደሚካሄድ አስታውቀው ነበር። የአትላንታው ስብሰባም ተካሂዶ ነበር።ሆኖም ግን ሾልክው የሚወጡ መረጃዎች የሚያመለክቱት ቀደም ሲል የተባልውን አይደለም። የስብሰባው ዓላማ የተቀደሰ ቢሆንም ሁለት የድርጅት መሪዎች ነን በሚሉና በጃዋር መሀመድ የተሰጡ አስተያየቶች አሉታን ፈጥረዋል። በተለይ የተሰጡት አፍራሽ አስተያየቶች በታዳሚው የሞቀ ጭብጨባ መታጀብ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዘንድ ጥያቄዎችን ጭሯል። የአንዳንዶቹንም የሕይወት ታሪክ ወደኋላ መለስ ብሎ ለማየት አስገድዷል።
“ያሳደግነው ጥጃ የምንጭ ውሃ ግተን፣ ከጨሌው አግጠን፣
ያሳደግነው ጥጃ ወትተ አጠጥተን፣ ለምለም ሣር አግጠን፣
ፈርገጥ ፈርገጥ አለ እኛኑ ሊረግጠን።” ፈተነኝ ከሚለው ዜማ የተውሰደ።
የመድርክ አዝጋጁ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት ተከታይ ነኝ ባዩ የመቶ አለቃ ተሻለ አበራ በደርግ ዘመነ መንግሥት ከፖሊስ ኮሌጅ በመኮንነት ተመርቆ ወደ ቀድሞዋ ሶቪየት ሕብረት ለትምህርት ተልኳል። በጊዜው በሥራ ላይ የነበሩ ወደሶቪየት ሕብረት ለትምህርት የሚላኩ የኢሠፓ አባላትና ካድሬዎች ናቸው። ወያኔ ሥልጣን እንደያዘም በተለያዩ የሥራ መደቦች ሲያገለግል ክቆየ በኋላ እስከ ኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንትነት ደርሷል። አሁንም የኦሕዴድ አባል ሳይኮን እዚህ ደረጃ ላይ እንደማይደርስ ፀሐይ የሞቀው ሐቅ ነው። መቶ አለቃ ተሻለ በወያኔ ለትምሀርት ወደ እንግሊዝ ሀገር ሂድ ሲባል ሚስትና ልጁን አስቀድሞ ወደ ዑጋንዳ በመላክ ለተሻለ ኑሮ በዚያው ቀርቷል። ባለወለታ ወይም ትግሬ ላልሆነ የዚህ ዓይነት ዕድል የማይታሰብ ነው። እንግሊዝ ሀገር እንደሄደም ዘመድም ሆነ ወዳጅ ስላልነበረው የቀረበው ወያኔን በመቃወም የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት (Downing Street) ደጃፍ ላይ የነበሩ ኢትዮጰያውያንን ነው። እነርሱም ወገናችን ነው በሚል ችግሩን ተረድተው አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ አድርገው የመኖሪያ ፈቃድ እስከሚያገኝና ጉዳዩ ፈር እስከሚይዝለት ድረስ ሲንከባከቡት ቆይተዋል። ዓመልና ጅራት ከወደኋላ እንደሚባለው ሁሉ የመቶ አለቃ ተሻለ ሀገር ከለመደና የስደተኝነት ጉዳዩ ካለቀለት በኋላ የዘር ክሩን መዝዞ ወደ ኦሮሞ ተቃዋሚዎች በመሄድ ውለታ ካደረጉለት ኢትዮጵያውያን ተደብቆ ይኖራል። ተሻለ ኢትዮጵያ ፈራርሳ የኦሮሚያ መንግሥት ይመሠረታል ብሎ የሚያስብ ፀረ የሀገራችን አንድነትና የኢትዮጵያዊነት ጥላቻ እንዳለው በተለያዩ ሁኔታዎች አቋሙን በማንፀባረቅ ላይ ይገኛል። ውሎው ኦሮሚያንና ኦጋዴንን እንገነጥላለን ከሚሉ የኦሮሞ ተወላጆችና የሱማሌ ዜጎች ጋር ሲሆን፤ ይህንንም ለማሳካት የሰብዓዊ መብት ታጋይ ድርጅቶችንና የእንግሊዝ ባለሥልጣናትን በመቅረብ መርዙን ሲረጭ ይውላል።
ዓላማችን ኢትዮጵያን አፈራርሰን ኦሮሚያን መገንጠል ነው ያለው የወያኔ ጄኔራል ሆኖ ሲያገለግል ቆይቶ ወደ ኤርትራ በመግባት ከሌቻ ወለቡማ የተባለ ድርጅት ያቋቋመውና አሁን በዑጋንዳ የሚገኘው የጄኔራል ከማል ገልቹ ተጠሪ ሊበን ዋቆ ነው። ድርጅቱ ከፋላ በመባል የሚታወቀው የሶማሌ አቦ ተቀፅላ እንደሆነ ይነገራል። ሊበን የሚታወቀው ጥቅም ባግኝበት የሚያድር በመሆኑ ንው። በደርግ ዘመነ መንግሥት በኢ.ሕ.አ.ፓ. አባልነት ተመልምሎ ብዙ ወጣቶችን በማጋለጥ ሕይዎታቸው እንዲያልፍ አድርጓል። በአንድ ወቅትም የኦነግ አባል ነኝ ብሎ በመጠጋት በኢሓፓ ላይ ያደረገውን እኩይ ተግባር ደግሞታል። በተለያዩ ጊዜያት የመንግሥትን ተቃዋሚዎች በማጋለጥና በማስመታት ላደረገው አስተዋፅዖ በሻምቡና በቦረና አውራጃ አስተዳዳሪነት ሊሾም በቅቷል። የደርግ መንግሥት ከወደቀም በኋላ በወያኔ እግር ሥር ሲልከሰከስ እንደነበረ የሚያውቁት ይናገራሉ።
ጉዲሣ ሙለታ (United Liberation Front) ኡልፎ መሪ የኦሮሞ ትግል ዓላማ እየፈረሰች ያለች ኢትዮጵያን መደገፍ ሳይሆን የጊዜውን አጋጣሚ ተጠቅሞ ኦሮሚያን ነፃ ማውጣት ነው ብሏል። ጉዲሣ ሙለታ ይህን ሲል ወያኔ በተባበረ ክንድ ሊወድቅ በተንገዳገደብት ወቅት ምርኩዝ እያቀበለ እንደሆነ አልተረዳውም። የፖለቲካ መሀይምነት ይሉታል ይህ ነው። ጉዲሣ ብዙም ተከታይ የሌለው፣ አትላንታ ላይ በተደረገው ስብሰባ አማራውንና የኢትዮጵያ አንድነት ደጋፊዎችን በፌስ ቡክ በመዝለፍ የምትታወቀውን የጀርመን ነዋሪ ቦዘኔ ከኋላ ኋላ እየተከተለ “አድናቂሽ ነኝ” እያለ ሲያሞካሻት መታየቱ ምን ያህል የወደቀ ሰው መሆኑን ያሳያል።
ሜንጫ በአረብኛው ሜንቻ ከተባለው የስለት መሣሪያ የተወሰደ ነው። አክራሪ እስላሞች የሌላውን ሃይማኖት ተከታዮች አንገት የሚቆርጡብት መሣሪያ ማለት ነው። በአሜሪካ ያደረገውን እውንተኛ ዓላማውን የሚገልፀውን አክራሪ የእስልምና ሃይማኖትን ለማስፈን የተጠቀመበትን ንግግር ለማዳመጥ የሚቅጠለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ። https://www.youtube.com/watch?v=RMLLmAMWdG8 የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችን ሰብስቦ ባደረገው ንግግር ጃዋር መሐመድ እኛ ዘንድ የሌላውን አንገት በሜንጫ ነው የምንቆርጠው ሲል ታዳሚው “አላህ ወ አክበር!” ብሎ አጨብጭቦለታል። ጃዋር ከሼሪያ ሕግ ተከታይ ጂሃዲስቶችና ከአይሲስ የሚለየው በምንድን ነው? ይህ ሰው ነው እንግዲህ በውጭ በሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆች የኦሮሞ ታጋይ ተብሎ የሚወሰደው።
ጃዋር OMN በሚል ያቋቋመው መገናኛ ብዙሓን ከአንዳንድ የአረብ ሀገሮች የገንዘብ ድጎማ እንደሚያገኝና በየሀገሩ የሚገኙ አንዳንድ ወጣቶችንና ቦዘኔዎች እየከፈለ እርሱ በዜና ማሰራጫው ሊል የማይችለውን እነሱ በሶሻል ሚዲያዎች እንዲሉለት እንደሚያደርግ ይነገራል። የአንዳንዶቹም እንቅስቃሴ ማስረጃ እየተሰበሰበና ለሕግ ለማቅረብ ዝግጅት እየተደረገብት ስለሆነ ወደዝርዝሩ አልገባም።
ከጥቂቶች በስተቀር የጃዋር መሐመድ ተከታዮች እስልምና ሀይማኖት ተከታዮችና ከፋላ በመባል የሚታወቁት የሶማሌ አቦ ወይም ኦሮሞኛ ተናጋሪ የምዕራብ ሶማሊያ ነፃ አውጪ ጀሌዎች እንደሆኑ ነው የሚነገረው። ከአልሽባብ ጋርም ግንኙነት አላቸው ይባላል።
አንዳንድ ከፋፋዮች ለማራገብ እንደሚሞክሩት ሳይሆን ሰፊው የኦሮሞ ሕዝብ አያት ቅድመ አያቶቹ የተዋደቁላት ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ፣ ደሞክራሲ ሰፍኖ፣ ሁሉም በእኩልነት የሚኖሩባት ሀገር ነው የሚፈልጉት። የኦሮሞ ሕዝብ በኢትዮጵያ ላይ የአንበሣ ድርሻ ያለው፣ ብሔረሰቡ የሰፈረበት ቦታ ለም ቢሆንም ጫንቃው ላይ የተቀመጡ ደም መጣቾች ለጊዜው የበይ ተመልካች ቢያደርጉትም ከሌሎች ወገኖቹ ጋር አብሮ ታግሎ መብቱን ማስከበር እንጅ አኩርፎ ልገንጠል የሚል ሕዝብ አይደለም።
አማራ በቂ የሰው ኃይል፣ የተፈጥሮ ሀብት፣ አባይን የመሰለ እንኳን ኢትዮጵያን ለሱዳንና ግብፅ ሕይዎት የሚዘራ የውሃ ሀብት ያለው ነው። ሀገር በቀልም ሆኑ የውጭ ሀገር ጠላቶች የሚረባረቡበትና የሚፈሩት የፀና የኢትዮጵያ ፍቅር ስላለው ብቻ ነው። አንድነትን የሚሰብከውና የሚፈልገው ብቻውን መቆም አቅቶት ሳይሆን ከሌላው ሕዝብ ጋር ተባብሮ ጠንካራ የጋራ ሀገር ለመመሥርት ሲል ብቻ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ተጭኖብኛል፤ ማንነቴን አይገልፀውም፤ ኢትዮጵያዊነት የሚባል መታወቂያነት ወይም identity የለም የሚለው ጃዋር ስለ ብሔረሰብ እንጅ ስለ ኢትዮጵያዊነት ተናግሮ አያውቅም። አማራ ኢትዮጵያዊነቱን ከረሳ ኦሮሞ የመገንጠል ህልሙ እውን ይሆናል በሚል እሳቤ ይመስላል ከአትላንታ ስብሰባ በኋላ የአማራውን መበደልና በአማራነት የመደራጀትን አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥቶ ሲናገር እየተሰማ ነው። የማንነት ጥያቄ ያነሳው አማራው ኢትዮጵያዊነትን ማቀንቀኑ እንደጎዳውና ይህንንም ትቶ እርሱና ጀሌዎቹ “I am Oromo First” እንደሚሉት አማራውም የእነርሱን መንገድ በመከተል ላይ እንደሆነ ለማሳመን ጥረት ሲያደርጉ ይስተዋላል። እነ ጃዋር ያልተረዱት አማርው ኢትዮጵያዊነቱን ብሎም በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ያለውን የፀና አቋሙን እንደያዘ የሚደርስበትን ጥቃት ለመከላከል በአጭር ጊዜ ውስጥ በመደራጀትና ተደራጅቶም በጠላቱ ላይ ጥቃት በመሠንዘር ላይ መሆኑን ነው።
ጊዜው የግሎባላይዜሽንና በአንድነት የመሰባሰብ ዘመን እንጅ የተበጣጠቁ ደሴቶችን የመፍጠሪያ ጊዜ አይደለም። እንደ ወያኔ በ21ኛው ክፍለ ዘመን በዘር ተደራጅቶ ስልጣን የመያዣም አይደለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በፖለቲካ ከነቃ ሰንብቷል አንዱ ዘር ሌላውን ረግጦ የሚገዛበት አይደለም። ይህን ዓይንት አስተሳሰብ የሚያራምድ ካለ አሁን በሥልጣን ላይ ካለው ወያኔ የማይሻል ነው። ጊዜው እራስን በዕውቀት አሳድጎ ለገበያ መውጣትን የሚጠይቅ ነው። ኢትዮጵያ የብሔረሰቦቿ ድምር ውጤት ስለሆነች ለአንዱ እናት ለሌላው የእንጀራ እናት የምትሆንበት ጊዜ ማብቂያው እሩቅ አይደለም፤ በአንድነት ተባብረን ከታገልን።
ከ120 ዓመት በፊት ተደረገ ለተባለው ዝባዝንኬ ጆሮአችንን ሰጥተንና የወያኔን የቤት ሥራ ተቀብለን የምናላዝን ካለን እስከ ህልፈታችን ሀዘን ከመቀመጥ ውጪ የምናተርፈው የለም። በዳዮችም ሆኑ ተበዳዮች እንኳን ነፍሳቸው አጥንታቸውም ስለማይገኝ ይቅርታ ጠያቂም ሆነ ተጠያቂ አይኖሮም። ይህን ምዕራፍ ዘግተን አዲሲቷን ኢትዮጵያ ለመመሥረት በሕብረት እንታገል። የውደቁትን ልጆቻችንና ቤተሰቦቻችንን መስዋዕትነት ዋጋ አናሳጣው።
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሣት) ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ በወያኔ ለታፈነው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዓይንና ጆሮ ሆኖ የሚያደርገው አስተዋፅዖ ከፍተኛ ነው። በመሆኑም ወያኔና ደጋፊዎቹን ጨምሮ በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከፍተኛ ተደማጪነት አትርፏል። ኢሣት ከሚያቀርባቸው ዝግጅቶች ውስጥ መነጋገሪያ የሆኑ ፕሮግራሞች አልጠፉም።
ፀረ – የኢትዮጵያ አንድነት፣ ፀረ – ክርስቲያንና ፀረ – አማራ የሆነው ጃዋር መሐመድ በፖለቲካ ተንታኝነት በተደጋጋሚ በኢሣት ቀርቧል። ጃዋርን ከተደበቀበት ጉድጓድ አውጥቶ ለታዋቂነት ያበቃው ኢሣት ነው። ጃዋር በአንድ ጉዳይ ላይ በአማርኛ፣ በኦሮሞኛና በእንግሊዝኛ የተለያዩ መግለጫዎችን የሚሰጥና የሚያምታታ ግለሰብ ነው። የፖለቲካ ብስለት የሌለውን በተልይ በወያኔ ዘመን የሕወሓትን የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ እየተጋተ ያደገውን ወጣት ከነመለስ ባልተናነሰ ግራ በማጋባት አንዱን ብሔረሰብ ከሌላው ብሔረሰብ ጋር በማጋጨት ጊዜውን የሚያጠፋ ነው። በመሆኑም ይህ ፀረ – ሠላምና ፀረ – አንድነት አቋም ያለው ሰው በተደጋጋሚ በኢሣት መቅረቡ ከድርጅቱ ዋና ዓላማ ጋር የሚቃረን ስለሚሆን ቢስተካከል መልካም ነው።
ጁነዲን ሳዶ ከጋዜጠኛ ሲሣይ አጌና ጋር ቃል ምልልስ አድርጓል። በእርሱ ዘመን እሥር ቤት ስላጎራቸው የኦሮሞ ልጆች፣ ሰለገደላቸውና ወደ ስድት ሲሄዱ ሜዲቴሪያኒያን ባሕር ውስጥ ስላለቁት የኦሮሞ ተወላጆች፣ በአጠቃላይ ስለ ኢትዮጵያ ልጆች ሰቆቃ ገን ትንፍሽ አላለም። ወያኔ በሙስሊሙ የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ከሊባኖስ አልሐባሽ የተባለ ሃይማኖት አምጥቶ ለመጫን ሲሞክር ጁነዲን ሣዶና ሚስቱ ደግሞ በሳዑዲ አረቢያ ተገዝተው የ14ኛው ክፍለዘመን የሻእሪያ ሕግንና ዋሀቢዝም የተባለውን የእስልምና እምነት ዘርፍ ኢትዮጵያ ላይ ለማስፈን ሲሯሯጡና ሚስቱ አዲስ አበባ ከሚገኘው የሳዑዲ ኤምባሲ ገንዘብ ተቀብላ ስትወጣ ስትያዝ፣ እርሱ ፈርጥጦ ከሀገር ወጥቷል። መልኩና ሥራው የእባብ የሆነው ይህ በኦሮሚያ ብዙ አማሮች ላይ ዘግናኝ ሰቆቃዎችን የፈፀመው የመለስ ዜናዊ ቀኝ እጅ የኦሕዴድ አመራር አባል የሠራቸው ወንጀሎች ማስረጃዎች ተሰብስበው ለዓለም – አቀፍ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት መቅረብ ሲገባው በኢሣት መስኮት ብቅ ብሎ በአፄ ሚኒሊክ ጊዜ ተፈፀመ የሚለውን የፍብረካ ወንጀል ማብራራት ነበረበት ወይ? ሁሉም ሰው ከሚያውቀው ወያኔ ሲነዛው ከኖረው የጥላቻና የሐሰት ፕሮፓጋንዳ የተለዬ ከእርሱ የተገኘ መረጃ አለ ወይ?
የቀድሞ የኦሕዴድ አባልና የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት መቶ አለቃ ተሻለ አበራ በለንደን ስቱዲዮ ቃለ – መጠይቆች ሰጥቷል። ተሻለ የሚሰጣቸው መልሶች በሙሉ በጥንቃቄ የተሞሉ ኦሮሚያ የኢትዮጵያ አካል እንደሆነች የማያመልክቱ፣ የእርሱም እጅ ስላለብት በኦሕዴድ ሰልተፈፀሙት ከፍተኛ በደሎች በማድበስበስ የታለፉ ነበሩ። መቶ አለቃ ተሻለ ኢትዮጵያ እየፈራረሰች ነው ብሎ የሚያስብ ለኦሮሞ ወያኔ የተሻለ ነው ብሎ የሚያምን ፅንፈኛ፣ ፀረ – የኢትዮጵያ አንድነት አቋም ያለው ሰው እንደሆነ የሚያመለክቱ መረጃዎችን የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ ወደፊት የሚያቀርበው ይሆናል። ኢሣትን ተጠቅሞ የለንደኑና የአትላንታውን የኦሮሞ ድርጅቶችን ስብሰባ አስተዋውቆበታል።
ኢሣት የኢትዮጵያ አንድነት ኃይሎች ንብረትና መጠቀሚያ እስከሆነ ድረስ ግለሰቦችን ለቃለ – መጠይቅ ከማቅረቡ በፊት ማንነታቸውንና አቋማቸውን ከየአቅጣጫው ማጣራት ይኖርበታል። ይህ ካልተቻለ ፕሮግራሙን አርሞ ማቅረብ ወይም እንዳለ አለማቅረቡ ይመረጣል።
“የምጽፈው ሁሉ ባይተች ኖሮ፣ መጻፌን አቆም ነበር”
ቭላድሚር ኤሊች ሌኒን።
ጽሑፌ ለትችት ክፍት ነው።
shegyen@gmail.co