ዘ-ሐበሻ ከአርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ እንዳገኘችው መረጃ ከሆነ ብረት አንስተው በበረሃ የመሸጉ አራት ታላላቅ የነፃነት ድርጅቶች አምባገነኑን የህወሓት አገዛዝ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በጋራ ደምስሰው ግብአተ መሬቱን ለመፈፀም ተጣምረው “የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ” የሚል አዲስ ድርጅት መሰረቱ፡፡
ተጣምረው የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄን የመሰረቱት አራቱ ታላላቅ የነፃነት ድርጅቶች የአፋር ድርጅቶች የጋራ ንቅናቄ፣ የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ፣ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ንቅናቄ እና አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ናቸው፡፡
የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ /በአጭሩ የአገር አድን ንቅናቄ/ የተቋቋመው ጳጉሜ 3 ቀን 2007 ዓ.ም ሲሆን የንቅናቄው ምክር ቤት፣ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ እና የተለያዩ መምሪያዎች ተቋቁመው ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ሊቀመንበር እና ታጋይ ሞላ አስገዶም ም/ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል፡፡
የኢትዮጵያ አገር አድን በዴሞክራሲ የጋራ ንቅናቄ ከአራቱ አባል ድርጅቶች የተውጣጣ እጅግ በጣም ግዙፍ አገር አድን ሰራዊት አቋቁሟል፡፡
- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/46520#sthash.3E2Dp0za.dpuf
No comments:
Post a Comment