የተደበቀው የህወሓት ማንነት ከደደቢት እስከ ቤተ መንግስት
ክፍል አምስት
==============================================
"...ሰፊው የትግራይ ህዝብ ስራ አጥቶ በሴተኛ አዳሪነትና ስደት ብቻ ሳይሆን በርሃብ፣ በድንቁርና እና በሽታ እየተሰቃየ በመኖሩ ምክኒያት ጠብመንጃ አንስተን በርሃ ለመውረድ ቻልን..."
ብሎን ነበር ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ያኔ በሽፍትነት ዘመኑ በ1968 ዓ.ም ባሳታመው የፖለቲካ ፕረሮግራሙ ከወደ ደደቢት፡፡
ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ይህን ካለ ከ40 ዓመታት በኋላ ዛሬም ረሃብ፣ በሽታ፣ ስራ አጥነት፣ ሴተኛ አዳሪነት፣ ድንቁርና እና ስደት አለ፡፡ እንዴውም ያን እሱ የተቸውን ዘመን በመሚያስመግን ሁኔታ፡፡ ታግየለታለሁ የሚለውን ትግራይን ጨምሮ መላው የኢትዮጵያ ወጣት በየቀኑ በግፍ ይሰደዳል፡፡
ስደትን አስቆማለሁ ብሎ ጠብመንጃ ያነሳው ህወሓት በስልጣን ዘመኑ ለዕልፍ አዕላፍ ኢትዮጵያዊያን ተሰዶ በባህር በዱር በገደልና በበርሃ ማለቅ ዋነኛ ምክኒያት ሆነ፡፡
ድህነትን ከአገራችን ምድር አጠፋለሁ ብሎ ታጥቆ የተነሳው ህወሓት ኢትዮጵያን ከኒጀር ቀጥላ የዓለም ሁለተኛዋ መናጢ ደሃ አገር ሆና በውርደት መዝገብ ስሟ እዲሰፍር አድርጎ ገናና ታሪኳን ሙልጭ አድርጎ ከምድረ ገፅ አጠፋው፡፡
ኮሌጅ የበጠሱ ወጣቶች የህወሓት ትምህርት ሜኒስቴር የሰጣቸው ክርታስ እንጀራ ሊያስቆርሳቸው ባለመቻሉ ረጅም የስደት ጅረት በመፍጠር ልክ እንደወንዞቻችን የተፈጥሮ ሀብታችንን ተሸክመው ያለማቋረጥ ወደ ውጭ መፍሰሳቸውን ቀጥለዋል፡፡ የመን ውስጥ ብቻ 800 ሺህ ወጣቶች እንደሚገኙ ዓለም አቀፍ የፍልሰት ድርጅት /I.O.M/ ያወጣው ሪፖርት ያረጋግጣል፡፡
"ተስፋ ብቻ ያዘሉ ፍሬ ቢስ ባዶ አዎጆችና መግለጫዎች በየጊዜው ይለፈፋሉ፡፡ እነዚህ ከእውነት የራቁ መግለጫዎችና ጽሁፎች በመገናኛ መስመሮች በጭቁን ህዝብና በአገር ስም ይታወጃሉ፤ የዓዋጆች ዓላማ የህዝቡን አስተሳሰብ ለማደናገርና ወታደራዊ ደርግ በስልጣን ለመቆየት ያለው ፍላጎት እደዚሁም ቡድናዊ ጥቅም ለመጠበቅ ሆን ተብሎ የሚደረግ የፖለቲካ ፕሮፓጋንዳ ነው..." በሽፍትነት ዘመኑ ይህን ይፅፍ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ በለስ ቀንቶት ከደደቢት ምኒልክ ቤተ መንግስት ከገባ በኋላ "የላም አለኝ በሰማይ" አሰልቺ ዲስኩሩን ውሽንፍር ከጠባቡ የአዕምሮው አድማስ ወደ ሰፊዋ ምድር እያወረደና የመኖር አድባር ተራሮችን በሃሰት መባርቅት እያረሰ የፈጠራቸው በተስፋ ውሃ የተሞሉ ኩሬዎች ግማት ህዝብ አፍንጫና አፍን በእጆቹ ሸፍኖ ሽሽትን እንዲመርጥ ጋበዘው፡፡ ህዝቡን ከመደናገር ጉድጓድ እግሮቹን አውጥቶ ለቡድናቸው ጥቅም ብቻ የቆሙ ስልጣናቸውን ለማራዘም ከሚያደርጉት የማወናበድ ድርጊት ሊያባንነው የተነሳው ህወሓት የኢትዮጵያን ህዝብ የባሰውን ወደ መደናገር ሸለቆ በመወርወር ከሸለቆው አፋፍ ላይ የሚገኝ የስልጣን ጉብታ ላይ ተኮፍሶ ወደታች አዘቅዝቆ እያየ በመገልፈጥ ለ24 ዓመታት በመከራው አላገጠበት፡፡
የሚሊየነር ቡድኖችን ፈጥሮ ሚሊዮኖችን የበይ ተመልካች አደረጋቸው፤ ጫት አቅራቢ፣ መጠጥ ቸርቻሪ ሆኖ የወጣቶችን አዕምሮ በማደንዘዝ ሃሳባቸውን አኮላሽቶ በአጭር በማስቀረት በቁማቸው እንዲያንቀላፉ አደረጋቸው፡፡
"ጊዜው ያለፈበት የኢኮኖሚ ስርዓት ባስከተለው ብዝበዛ ምክንያት በህብረተሰቡ ውስጥ ያሉት መሰረታዊ ችግሮች ድንቁርና፣ በሽታ፣ ድህነትና ርሃብ የመሳሰሉ እንደዚሁም መደቦችና የመደብ ብዝበዛ ለማጥፋት ህወሓት የማያቆርጥ ትግል ታደርጋለች..." ሲል በፖለቲካ ፕሮግራሙ ላይ የፃፈው ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ራሱን በበዝባዦች መደብ ላይ አስቀምጦ ብቸኛው በዝባዥ ሆኖ በወፍ ዘራሽነት በኢትዮጵያ ጥቁር አፈር ላይ በመብቀል ልክ እንደ ባህር ዛፍ ስሩን አስረዝሞ የሌሎች ተክሎችን ምግብና ውሃ እየተሻማ አጠውልጎ በቁማቸው አደረቃቸው፡፡ ኢትዮጵያችን የድንቁርና፣ በሽታ፣ ድህነት፣ ርሃብና ስደት አሜኬላ ከባህር ዛፍ እግር ስር በቅለው የተንሰራፉባት ምድር ሆነች፡፡ በተጨማሪም ህወሓት የፖለቲካ እሳት መንዶውን ባንድ እጁ የማህበራዊ ሾተሉን በሌላኛው ዕጁ አንስቶ በህዝቡ ገላ ላይ እያሳረፈ 40 በመግረፍ አገራችንን የባሰውኑ ምድራዊ ሲኦል አደረጋት፡፡ በዚህ የተነሳ ዜጎች ሲኦልን ሽሽት ግን ወደ ሌላኛው ይሻላል ብለው ወደ ገመቱት ሲኦል መጓዛቸውን ያለምንም ፋታ ተያያዙት፡፡ በህወሓት ኃጢያት ተኮንነው ገኀነም በመግባት ትልቅ ዋጋ በመክፈል ላይ ናቸው፡፡
ትናንትና በስለት አንገት አንገታቸውን የታረዱት ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች በግፍ የፈሰሰ ደም ከሊቢያ ምድር ላይ ሳይደርቅ ዛሬ ደግሞ ሱዳን ላይ በርካታ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ እየተገደሉ ኩላሊታቸው በመውጣት ላይ ነው፡፡
እልቂቱ፣ ግፍና መከራው፣ መሰደድና መፈናቀሉ፣ ፍዳና ሰቆቃው፣ በስለት መታረዱና በጥይት መጨፍጨፍ፣ ውርደትና ክብር ማጣቱ... በሰው አገር ብቻ ሳይሆን በገዛ አገራችንም በባሰ ሁኔታ መፈፀሙ የእኛን የኢትዮጵያዊያንን ችግር እጥፍ ድርብ ያደርገዋል፡፡ ወጣቶች ከመከራ ላይ የመከራ ካባ ደራርበው እንዲለብሱ ከሰቆቃ ላይ ሌላ የሰቆቃ ሸማ እዲጎናፀፉ ያደርጋቸዋል፡፡
ሳዑዲ አረቢያ ላይ የደረሰው መፈናቀል በኢትዮጵያችን ምድር ላይም በህወሓት ተከስቷል፡፡ ኢትዮጵያዊያን በቋንቋቸው ዘራችሁ ሌላ ነው ተብለው ከቤንች ማጅ ዞን ጉራ ፋርዳ ወረዳ ከሌሎችም በርካታ አካባቢዎች ቤት ንብረታቸውን እየተነጠቁ በተደጋጋሚ ተባረዋል፡፡
በቅርቡ በሊቢያ ውስጥ በአይሲስ የተፈፀመው የ30 ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን በስለት መታረድና በጥይት መጨፍጨፍ፤ አርባ ጉጉ በደኖ ላይ ዘራችሁ ሌላ ነው ተብለው ዕልፍ አዕላፍ ኢትዮጵያዊያን ገና ነብስ ያላወቁ ህፃናት፣ ነብሰጡር ሴቶችና አዛውንቶች ሳይቀሩ በስለት ታርደዋል፤ ህወሓት በሳለው ጎራዴ አካላቸው ልክ እንደ ዶሮ ተበልቷል፡፡
ጋምቤላ ውስጥ አኙዋኮች ብቻ እየታደኑ በህወሓት ሰራዊት መትረየስና ክላሽን ኮቭ ተጨፍጭፈዋል፡፡
በ1997 ዓ.ም ድምፃችን ተዘረፈ ብለው ለተቃውሞ ሰልፍ አደባባይ የወጡ ወጣቶች ከትምህርት ቤት የሚመለሱ ህፃናትን ጨምሮ በአልሞ ተኳሽ ግንባር ግባራቸውን ተመትተው ሰቅጣጩ አስከሬናቸው በየጎዳናው ተልከስክሷል፡፡
የህወሓት ድብቅ ሴራዎች
ህወሓት በሽፍትነት ዘመኑ 17 ዓመታት ሙሉ ሴራ ሲጎነጉን፣ ሸፍጥ ሲሰራ፣ የተንኮል ዕቅድ ሲነድፍ፣ የጠልፎ መጣል ስልት ሲያቀነባብር፣ ያለምንም ድካምና ዋጋ እንዲሁም ዕውቀት የስልጣን ኮረቻ ላይ ለመፈናጠጥ የሚያስችለውን የሀሳብ ቀመር ሲቀምርና የዘር ሂሳብ ሲያሰላ ነበር የኖረው፡፡ ህወሓት በአውደ ውጊያ ካሳለፋቸው ዓመታት ይልቅ በየዋሻውና በየሸለቆው አድፍጦ የጥፋት ሴራ ሲጠነስስ የነበረባቸው ዓመታት ይበልጣሉ፡፡
የግራ ርዕዮተ ዓለም የሚያራምዱትን ሲያገኝ የሶሻሊስትነት ካባ ደርቦ በመቅረብ የቀኝ ርዕዮተ ዓለም ከሚያራምዱት ፊት ደግሞ ማርክሲስት ሌኒንስት ካባውን ሳያወልቅ የሌበራልነት ካባ በላዩ ላይ ደርቦ በመታየት እንደ እስስት ቆዳውን በመቀያየር በመስሎ አዳሪነት ባህሪውም የሚያክለው የለም፤ ሴተኛ አዳሪው ድርጅት ህወሓት፡፡
ህወሓት በሽፍትነት ዘመኑ ከአረብ አገራት እርዳታ ለማግኘት በማለም የውጭ ጉዳይ ኃላፊ የነበረውን ስዩም መስፍንን ስሙን ቀይሮ ስዩም ሙሳ ተብሎ እንዲጠራ አድርጓል፡፡
ህወሓት ገና ስሙን ሳይቀይር ተሓህት/ተጋድሎ ሓርነት ህዝቢ ትግራይ/ ይባል በነበረበት ወቅት ግገሓት/ ግምባር ገድሊ ሓርነት ትግራይ/ ከተባለው ከእሱ በፊት ተመስርቶ በትግራይና በኤርትራ አዋሳኝ መሬቶች ላይ ይንቀሳቀስ በነበረው የታጠቀ ድርጅት ጋር ሙሉ በሙሉ ውህደት ለመፈፀም ስምምነት ላይ ደርሳል፡፡ ቀጥሎም ሁለቱ ድርጅቶች ማለትም ተሓህት-ህወሓት እና ግገሓት ውህደት ወደሚፈፅሙበት ቦታ ምስራቅ ትግራይ ዘገብላ ተብላ ወደ ምትጠራው ቦታ ሰራዊታቸውን ወስደው ካሰፈሩ በኃላ አመሻሽ ላይ የተሓህት-ህወሓት አመራሮች ቀን ሲሸርቡት የዋሉትን ሴራ ለሰራዊታቸው በጠቅላላ በምስጢር እዲተላለፍ አደረጉ፡፡ ይህም እያንዳንዱ የተሓህት-ህወሓት ታጋይ ከግገሓት ታጋይ ጋር ጥንድ ጥንድ እየሆኑ እንዲተኙና ግገሓቶች እንቅልፍ ወስዷቸው የተኩስ ትዕዛዝ እስኪተላለፍ በንቃት እዲጠባበቅ የሚል ነበር፡፡
ከዚያም እኩለ ሌሊት ላይ የግገሓት ሰራዊት በእንቅልፍ ላይ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ የተሓህት-ህወሓት ታጋዮች ከጎን ከጎናቸው ከተኙ የግገሓት ታጋዮች ላይ እንዲተኩሱ በምልክት ትዕዛዝ ተሰጥቷቸው ለውህደት የመጣው የግገሓት ሰራዊት ከነመሪዎቹ በእንቅልፍ ላይ እንዳለ ተጨፍጭፎ ሙሉ በሙሉ ተደመሰሰ፡፡
ምክትል ፕረዝዳንቱን ፍስሃ ደስታን ጨምሮ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ከፍተኛና ዝቅተኛ የደርግ ባለስልጣናትን ራሱ ደርግ እንዲረሽናቸው ህወሓት በ1970 ዓ.ም አንድ ሴራ ጠንስሶ ሙሉ በሙሉ ተሳክቶለታል፡፡
ህወሓት ደርግ እንዲረሽናቸው የሚፈልጋቸውን በከፍተኛና ዝቅተኛ የመንግስት አመራር የሚገኙ የትግራይ ብሄር ተወላጆችን ስም ዝርዝር በቀላሉ ሊሰበር በሚችል ኮድ በማስፈር እና ለህወሓት የሰሩትን ስራ ከጎን በመፃፍ ሐሰተኛ ደብዳቤ አዘጋጅቶ የከተማውን የህቡ እንቅስቃሴ ከሚመራው ተክሉ ሃዋዝ የተባለ ታጋይ ለሊቀመንበሩ አባይ ፀሃዬ የተላከ በማስመሰል ሶስት ታጋዮች ደብዳቤውን ይዘው ወደ አክሱም ከተማ እዲገቡ ካደረገ በኃላ ራሱ በተዘዋዋሪ መንገድ ጠቁሞ በደርግ ደህንነቶች ቁጥጥር ስር እንዲውሉ አስደርጓቸዋል፡፡
ከዚያም ከተክሉ ሃዋዝ ለአባይ ፀሐዬ እንደተላከ ተደርጎ የተዘጋጀው ደብዳቤ ከደርግ ደህንነቶች እጅ ይገባና ወደ መቀሌ ተልኮ ኮዱ ተሰብሮ ሰም ዝርዝራቸው ሰፍሮ የተገኙት በከፍተኛና ዝቅተኛ የመንግስት አመራር ውስጥ የሚገኙ ዕልፍ አዕላፍ የትግራይ ተወላጆች እየታደኑ ወደ ወህኒ ተወስደው አሰቃቂ ምርመራ ከተደረገባቸው በኋላ ያለ ኃጢያታቸው ተረሸኑ፡፡
ህወሓት ባዘጋጀው ሃሰተኛ ደብዳቤ ላይ አባሎቹ እንደሆኑ አስመስሎ ስማቸውን ከዘረዘራቸው የትግራይ ተወላጅ ከሆኑት የደርግ አመራሮች ምንም ሳይሆን የቀረው ፍሰሃ ደስታ ብቻ ነበር ፡፡
ህወሓት ከተመሰረተበት ከ1967 ዓ.ም እስከ 1977 ዓ.ም ድረስ በነበሩት 10 የሽፍትነት ዓመታት ውስጥ ከአመራሩ ውጭ ያሉ ታጋዮች ፆታዊ ግንኙነት ካደረጉ ያለምንም ምህረት ይረሸኑ ነበር፡፡ በመሆኑም ፆታዊ ግንኙነት አድርገው የተነቃባቸው የህወሓት ታጋዮች ከመረሸን ለመዳን ለደርግ እጃቸውን ይሰጡ ነበር፡፡
በፆታዊ ግንኙነት ምክንያት በየጊዜው የሚከዱ ታጋዮችን ደርግ በጥሩ ሁኔታ እደሚቀበላቸው መረጃው የደረሰው ህወሓት ይህን ተንተርሶ ሴራ ጠነሰሰ፡፡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ሴት ታጋዮችን ፆታዊ ግንኙነት አድርገው እንዲያረግዙ ቀጭንና የማያዳግም መመሪያ አወረደ፡፡
መመሪያ የተሰጣቸው በርካታ ሴት ታጋዮች ካገኙት ወንድ ታጋይ ጋር ሁሉ ልክ እንደ እንስሳ ፆታዊ ግንኙነት በማድረግ አርግዘው የህወሓትን መሪዎች ቀጭን ትዕዛዝ ተግባራዊ አደረጉ፡፡ ቀጥሎም የህወሓት መሪዎች እርጉዞቹ ታጋዮች ለደርግ እጃቸውን ሰጥተው በምስጢር እንዲሰልሉ አዘዙ፡፡
ይህ የሰውን ልጅ ከሰውነት ወደ እንስሳነት ተራ የሚያወርድ ሴራ እና ለስልጣን ሲባል በሴት ልጅ ላይ የተፈፀመው ግፍ በሴት ታጋዮች ላይ የሞራል ውድቀትና ሰቆቃ ከማስከተሉ በስተቀር ለህወሓት ከዚህ ግባ የሚባል ውጤት አላስገኘለትም፡፡
በጦር ሜዳ ተዋግቶ ከማሸነፍ ይልቅ በቀበሮ ጉድጓድ ውስጥ አድፍጦ ሴራ መጎንጎን የሚቀናው ህወሓት ደርግን ከትግራይ ህዝብ ነጥሎ እሱ ሰፊ ድጋፍ የሚያገኝበትን ሌላ ሼር ደግሞ ጠነሰሰ፡፡
እሱም “የሀውዜን ጫፍጨፋ” በመባል የሚታወቀው ነው፡፡ ህወሓት በፀራራ ፀሀይ በገበያ ቀን ሰራዊቱን በሀውዜን ከተማ እንዲያልፍና ከፊሉ ደግሞ በግቢያተኛው መካከል እንዲሰራጭ በማድረግ እና በተዘዋዋሪ መንገድ ለማድረግ ደህንነት ቢሮ ጥቆማ በመስጠት ህዝቡን በአውሮፕላን ቦምብ አስጨፈጨፉት፡፡ አስቀድው ባዘጋጁት የቪድዮ ካሜራም በቀጥታ በመቅረፅ ለዓለም አሰራጭተው እንወክለዋለን በሚሉት የትግራይ ህዝብ ሞት የፖለቲካ ትርፍ አጋበሱበት፡፡
ህወሓት በበረሃ አያለ ህዝቡን ለሰራዊትነት ሲመለምል ፈቃደኛ ያልሆኑ ወጣቶችን ቀሚስ አልብሶ በአደባባይ እያዞረ በህዝቡ ፊት ያሸማቅቃቸው ነበር፡፡
ከአርበኞች ግንቦት 7 ህዝብ ግንኙነት
No comments:
Post a Comment