Monday, March 14, 2016

የወቅታዊ ተግባራዊ ትግል (ወተት) መልዕክት: በግልጽ ጦርነት ውስጥ ካልሆን በህቡዕ ጦርነት እንሳተፍ !(ክፍል 1)


የህወሓት/ኢህአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝን አዳክሞ ለመጣል እና የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሁንታ ያገኘ መንግሥት ለመመሥረት የሚደረገው ሁለገብ ትግል ዘርፈ ብዙ ነው። በህወሓት/ኢህአዴድ ላይ የታወጁ የጦርነት ዓይነቶች “ግልጽ ጦርነት” እና “ህቡዕ ጦርነት” ብለን በሁለት ልንከፍላቸው እንችላለን።
የግልጽ ጦርነት ዓይነቶች ብዙ ቢሆኑም እንኳን አንድ የጋራ ባህሪያቸው በሁለቱም ወገን ተፋላሚዎች በኩል እየፎከረ፣ እየሸለለ፣ እያወገዘ ምሬቱን በገሀድ እየገለፀ ያለ ሠራዊት አለ። በትጥቅ ትግል የተሰማሩ ጓዶች የትኛውም ስልት ይጠቀሙ ከጠላት ጋር ግልጽ ጦርነት ውስጥ ገብተዋል። በደል በዝቶባቸው ባዶ እጃቸውን አደባባይ የወጡ የሕዝባዊ እምቢተኝነት አርበኞችም እንደዚሁ ከጠላት ጋር ግልጽ ጦርነት ገብተዋል።
በአንፃሩ ደግሞ ጦርነት ውስጥ መሆናቸው እንኳን ሳይገልጹ በህቡዕ አምባነኑን ሥርዓት እየተፋለሙ ያሉ ወገኖች አሉ። የዚህ ጦርነት ውጤት እንጂ ተፋማላዎቹ አይታዩም፤ እነማን እንደሆኑ መለየትም ከባድ ነው። አምባገነን ሥርዓቱ ዘይት እንዳጣ መዘዉር እርስ በርሱ ሲፋተግና ሲያልቅ ይታያል፤ ማን ዘይቱን እንደነፈገው ግን በግልጽ የሚታወቅ ነገር አይኖርም። 
ህቡዕ ጦርነት እንደ ግልጽ ጦርነት ሁሉ ጠላትን የማዳከም ከፍተኛ አቅም አለው። ግልጽ ጦርነት እና ህቡዕ ጦርነት ተደጋግፈው ከሄዱ ባነሰ ወጪና ድካም አምባገነን ሥርዓትን ማዳከም ቀጥሎ ጨርሶ ማንበርከክ ይቻላል። በግልጽ ጦርነት እየተሳተፍን ካልሆነ በህቡዕ ጦርነት መሳተፍ ሁሌም በእጃችን ያሉ አማራጭ ነው።

ስለዚሆነም የዛሬው የወተት መልዕክት “በግልጽ ጦርነት ውስጥ ካልሆንን በህቡዕ ጦርነት እንሳተፍ!” የሚል ነው። “እንዴት?” የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ከዚህ በታች የሚቀርበርበው አጭር ማብራሪያ ተዘጋጅቷል።
እያንዳንዱ ነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ሊሳተፍባቸው የሚችሉ የህቡዕ ጦርነት ስልቶች በርካታ ቢሆኑም አሻጥር፣ የስነ-ልቦና ጦርነት፣ የኢኮኖሚ ጦርነት፣ እና ኢህአዴግን እርስበርሱ ማናከስ የተባሉት ለአብነት ቀርበዋል።
ሀ. አሻጭር (sabotage) - አንድን አምባገነን የአገዛዝ ሥርዓት ለማዳከም በሥራ ከሚውሉ የህቡዕ ጦርነት የትግል ስልቶች በቀዳሚነት የማነሳው አሻጥርን ነው። “አሻጥር” የሚለው ቃል ለቅን አሳቢዎች አሉታዊ መልዕክት ይኖረው ይሆናል፤ ይህን ለመከላከል “አሻጥር ለምን ዓላማ?” እና “አሻጥር በማን ላይ?” ተብሎ መጠየቅ ይኖርበታል። የበዳዮች፣ ግፈኞች፣ ገዳዮችና ዘራፊዎች ሥራ ስኬታማ እንዳይሆን አሻጥር መሥራት ከስነምግባር አንፃር የሚያስመሰግን ተግባር መሆኑ አጽንኦት ሊሰጠው ይገባል።
የአገራችን ወታደሮችና ፓሊሶች “ሥራዬ ነው” ወይም “የታዘዝኩትን መፈፀም ሙያዬ ያስገድደኛል” እያሉ እራሳቸውን በመሸንገል ወገኖቻቸውን ይደበድባሉ፣ ይገድላሉ። ህሊና ለአለቃ ትዕዛዝ ይቅርታ አታደርግምና እነዚህ ሰዎች ወደ ህሊናቸው በተመለሱ ጊዜ ከገዛ ራሳቸው ጋር መጣላታቸው አይቀርም። ህሊና ብቻ ሳይሆን ፍትህም ይቅርታ አታደርግላቸውም። እነዚህ ወገኖች ግን የታዘዙትን እየፈፀሙ ያሉ መስለው ተቃራኒውን በመፈፀም በህቡዕ ጦርነት ሥርዓቱን መፋለምና ከህሊናቸው ጋር ታርቀው መኖር ይችላሉ። የሚገርፉ መስለው ባለመግረፍ፤ የሚገድሉ መስለው ጥይት በመጨረስ፤ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እስረኞችን በማስመለጥ፤ የነፃነት ታጋዮችን ቢያዩም እንዳላዩ ሆነው በማለፍ፤ የመሥሪያ ቤታቸውን የምስጢር ሰነዶች ለነፃነት ታጋዮች አሳልፈው በመስጠት፤ በአቅርቦት እጥረት ወይም በተሳሳተ እቅድ ምክንያት ኦፕሬሽኖት እንዲሰናከሉ በማድረግ፣ ... ወዘተ በህቡዕ ጦርነት በመሳተፍ በግልጽ ሥርዓቱን በመዋጋት ላይ ያሉ ወገኖችን ማገዝ ይችላሉ።
በመብራት ኃይልና በቴሌኮሚኬሽን መሥሪያ ቤቶች ውስጥ የሚሠሩ ወገኖች ሙያቸውና የሥራ ኃላፊነታቸው ተጠቅመው በአገዛዙ ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የሚያስከትሉ የመሣሪያዎች ወይም የሲስተም ብልሽቶችን ማድረስ፤ ፕሮጀክቶችን ማጓተት ወይም ማሰናከል ይችላሉ። በፋይናንስ ተቋማት ውስጥ የሚሠሩ ወገኖች በእጃቸው ትልቅ መሣሪያ እንዳለ ይገንዘቡ - ያለ እነሱ አገልግሎት ኤፈርትም ሆነ ሌሎች የሥርዓቱ አገልጋይ ቢስነሶች አገራችንን ማራቆት አይችሉም። በገንዘብ ዝውውራቸው ላይ እንቅፋቶችን መፍጠር፤ ሂሳቦቻቸውን ማዛባት፤ ጠበቅ ያለ ቁጥጥር ማድረግ፤ ህገወጥ ድርጊቶቻቸውን በማስረጃ ማጋለጥ (በህግ ባይቻል ለአደባባይ ዜና ማብቃት) ... ወዘተ እና ሌሎች በርካታ እዚህ ላይ ያልተፃፉ ነገሮችን ማድረግ ይችላሉ። የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን (IT) ባለሙያዎች ሙያቸውን ተጠቀመው የአምባገነን ሥርዓቱን የ IT ሲስተም ማበላሸት ይችላሉ። እንዲህ ለማድረግ የሚደፍሩ ወገኖች በህቡዕ ጦርነት ውስጥ በግንባር የተሰፉ፤ በግልጽ ጦርነት በግንባር ከተሰፉ ጓዶች እኩል ክብር የሚሰጣቸው ናቸው።
የህቡዕ ጦርነት ተሳታፊዎች በተራቀቁ የሙያ መስኮች ውስጥ ያሉ ሰዎች አድርገን መውሰድ የለብንም። ገበሬዎች የመንግሥት ግብር ሲበዛባቸው በግልጽ ከማመፃቸው በፊት ግብርን ማዘግየት፤ ግብር ሰብሳቢውን ማጉላላት፤ ምርታቸውን ቀንሰው መናገር ይችላሉ። ቅራኔዎቻቸውን በባህላዊ መንገድ በመፍታት ወደ ፓሊስና ፍርድ መሄድን ነውር ሊያደርጉት፤ ቀጥሎ፣ “አትድረሱብን አንደርስባችሁም” ሊሏቸው ይችላሉ። ነጋዴዎች ከውጭ የሚያስገቧቸው ሸቀጦችን ዋጋ ማዛነፍ፤ ሰው ሰራሽ እጥረት መፍጠር፤ “አትሽጡ” የተባሉትን በድብቅ መሸጥ፤ “ሽጡ” የተባሉትን አለመሸጥ ይችላሉ። የመንግሥት ሠራተኞች ሥራን ማጓተት በቀላሉ ተግባራዊ ሊያደርጉት የሚችሉት ስልት ነው። የጽዳት ሠራተኞች፣ የጥበቃ ባለሙያዎች፣ የመዝገብ ቤት ሠራተኞች ... ወዘተ በሥራ ላይ በመለገም ብቻ ውጤታማ ተግባራትን ማከናወን ይችላሉ፤ እነዚህ ወገኖች ለብዙ ምስጢራዊ ሰነዶች ቅርብ በመሆናቸው በግልጽ ጦርነት ውስጥ ያሉ ወገኞችን በከፍተኛ መጠን መርዳት ይችላሉ። በአጭሩ የመንግሥት ሠራተኞች አምባገነኑን ሥርዓት የሚያስወቅሱ በርካታ ተግባራትን ማከናወን ይችላሉ። አሻጥር እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በቀላሉ ሊሳተፍበት የሚችለው የህቡዕ ጦርነት ስልት ነው። 
.......... ይቀጥላል ...

No comments:

Post a Comment