Tuesday, March 29, 2016

የህወሓት አገዛዝ የ24ኛ ክፍለ ጦር በርካታ ወታደራዊ አዛዦችን በቁጥጥር ስር አዋለ፡፡(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


ከሰሞኑ በቁጥጥር ስር ከዋሉት በርካታ የህወሓት የጦር መኮንኖች መካከል ኮሎኔል ባምላኩ እና ሻለቃ ተካ የተሰኙት ይገኙበታል፡፡
ህወሓት የ24ኛ ክፍለ ጦር አዛዦችን እየለቀመ ያሰረው በክፍለ ጦሩ ውስጥ በተፈጠረው ውስጣዊ አለመተማመንና ጥርጣሬ መሆኑ ታውቋል፡፡

ከታሰሩት የህውሓት የጦር መኮንኖች መካከል ሰሙ ከላይ የተጠቀሰው ኮሎኔል ባምላኩ ከዚህ ቀደም በ2007 ዓ.ም ከመተማ እና አካባቢው 9 ወጣቶችን በቁጥጥር ስር በማዋል ሁመራ ወደሚገኘው በመቶ አለቃ ይስሃቅ የሚመራ የዚሁ የ24ኛ ክፍለ ጦር ክፍል የሆነ ገዳይ ቡድን በማስረከብ ተረሽነው አስከሬናቸው በተከዜ ወንዝ አቅራቢያ እንዲቀበር ያደረገ ጨፍጫፊና ወንጀለኛ ነው፡፡

No comments:

Post a Comment