Monday, March 21, 2016

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ) ትግራይና ወልቃይትን የሚያገናኙ ጎዳናዎች መዘጋታቸው ተነገረ፤ ፌደራል ፖሊስና የትግራይ ልዩ ኃይል የወልቃይትን ምድር ወሮታል፡፡


የወልቃይት ህዝብ ያነሳውን የአማራ ማንነት ጥያቄ ለመቀልበስ ህወሓት አጠናክሮ የጀመረውን በህብረተሰቡ ዘንድ ተቅባይነት ያላቸውን ግለሰቦች አፍኖ ድብዛቸውን የማጥፋት ተግባር በመቃወም የወልቃይት ህዝብ እርምጃ መውሰድ ጀምሯል፡፡ በመሆኑም ዋና፣ ዋና መንገዶችን በጠብመንጃ አጥሮ በመዝጋት ተከዜን ተሻግሮ ከትግራይ ወደ ወልቃይት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በመግታት ላይ ነው፡፡
የወልቃይት ታጣቂ ኃይሎች ከወለቃይትና ትግራይ ወሰን ላይ በመመሸግ በእግርም ወደ ወልቃይት የሚጓዙ ሰዎችን መታወቂያ መጠየቅ ጀምረዋል፡፡
በአዲ ጎሹ በኩል ከትግራይ ወደ ወልቃይት የሚያስገባው አውራ ጎዳና እና እንዲሁም በተጨማሪ ከሁመራ ወደ ጎንደር የሚሄደው መንገድ በወልቃይት ታጣቂ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ውለው ተዘግተዋል፡፡ 
ትናንትና ጠዋት ከወደ ትግራይ የተነሳች መኪና “ካዛ” ላይ መሽገው በነበሩት የወልቃይት ታጣቂዎች ተኩስ ተከፍቶባታል፡፡

ህወሓት ከትናንት ወዲያ አፍኖ የወሰዳቸው የወልቃይት የአማራ ማንነት ጥያቄ አስተባባሪ ኮሚቴ አባል የሆኑት “አቶ ሊላይ ብርሃነ” ደብዛ መጥፋትና “ሩዋልሚ” ከተባለ ወንዝ ዳር አንድ ማንነቱ ሊለይ ያልቻለ አስከሬን መገኘቱ የህዝቡን ቁጣ እንዳባባሰው ተገልጿል፡፡
እናም ህወሓት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ፌደራል ፖሊስና የትግራይ ክልል ልዩ ኃይል ጦር በወልቃይት ምድር አሰራጭቶ በተለይም ደግሞ ዳንሻ በሰራዊት ተከባ ትገኛለች፡፡ የወልቃይት ህዝብና የትግራይ ልዩ ኃይሎች በመዋጋት ላይ ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment