Thursday, March 17, 2016

በሃረር አዲስ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ለመመልመል የተደረገው ጥረት አልተሳካም


ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ወከል እንዳለው፣ ሰሞኑን አዲስ ምልምል ወታደር ለመቅጠር ተደጋጋሚ ማስታወቂያ ቢወጣም፣አልተሳካም። የመንግስት ካድሬዎች በመኪኖች ላይ እየዞሩ " ለወታደሮች ቤት እንደሚሰጡ" እየገለጹ፣ እንዲመዘገቡ ቢቀሰቅሱም፣ እስካሁን የሚመዘገብ ወጣት መጥፋቱን ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ ጠቅሷል። ትናንት በተለያዩ ምክንያቶች የተገለሉ የቀድሞ ወታደሮችና የፖሊስ አባላትን ለስብሰባ ተጠርተው የነበረ ቢሆንም፣ በቂ ተሰብሳቢ ሊገኝ ባለመቻሉ ተሰርዟል። በሌሎችም ወረዳዎች ተመሳሳይ ሁኔታ መፈጠሩን ወኪላችን ገልጿል። የስብሰባው አላማ በጸጥታ ጉዳይ ከሰራዊት አባላት ጋር ለመነጋገር የሚል ነበር።

No comments:

Post a Comment