Friday, March 11, 2016

በምዕ/ጎጃም ሰሜን አቸፈር ውስት የምትገኘው የቁንዝላ ከተማ ከባድ ውጥረት ውስጥ ገብታለች ።

በኢንስፔክተር አትንኩት የተመራ ሂድ ባሉት የሚሄደ የእንስሳን ባህሪ የተላበሰ የፖሊስ መንጋ ቁንዝላን ፖሊስ ጣቢያ ተሰባስበዋል ።ከዱርቤቴ እስከ ቁንዝላ ፣ ከዝህብስት እስከ ጉግ አባይ ማዞሪያው ድረስ የአዴሃን የትግል ጥሬ ወረቀቶች እያስተጋቡ ከመሆኑና አቸፈር ወንድየ በጋራ ባበረ ክንዱ ቀጠናውን በግንዛቤ ገንብቴ የእሳት ቀጥና ለማድረግ በአንድ ቋንቋ ለመምከር መደራጀቱን ያወቀው መራሹ የወያኔ መንግስት ደንግጧል።ፖሊህ የህዝብ ሁኖ ሳለ የራሱን ወንድሞት፣ እህቶች ፣አባቶችና እናቶች ለመደብደብና አመለካከት ለማስቀየር ፖሊስና ህዝቡ ተፍጠዋል ።ዛሬ የአዴሃን የትግል ጥሪ በተለጠፈበት ከተማ ቁንዝላ ፦
እነሱም ይላሉ ተኩሰንም አንስት ፣
እኛም እንላለን ቃታም አናስከፍት ።
በማለት የአዴሃን ልጆች መልዕክተ አዴሀንን ለጥፈው አድረዋል ፣ቁንዝላ በአዴሃን የትግል ጥሪ ወረቀት አሸብርቃ አድራለ ።አርሶ አደሮቻችንም ፖሊስ ሳይቀዱት ለማንበብ ተግተዋል ። እየተደበደቡም ቢሆን ለማንበብ ደርሰዋል ።

በመጨረሻም የአድርሱልን መልዕክት 
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ኢንስቴክተር አትንኩት ጊዜ አላፊ ነው ።ጊዜ ሲያልፍ የበደልህን መጠን ህዝቡ ላይሰፍርልህ ይችላል ንቆ ይተውሃል የላይኛው ጌታ ግን የግፍ መጠንህን ይለካልና በልኬታህ ልክም ትቀጣበታለህ ።ወያኔ ይወድቃል እናም ወደ ትግራዋይ ይሄዳል አንተ ግን ከወገንህ ጋር እዚሁ ትቀራለህ ያኔ የወገንህ በደል አንድ በአንድ ሲዘረዘርልህ ህሊናህ በፅኑ ታሞ ላብድ ነው ይልሀል ከህሊና ጋር መጣላት ከባድ ነውና እባክህ ህዝቡን አታሰቃየው እየነዳህ ያመጣኸውን የፖሊስ መንጋ ይዘህ ውጣ በወቅቱ ከቁንዝላ ሲቀጥል ከአቸፈር አናት ላይ ውረድ የሚያዋጣህ አማራው ወገንህ ነው ።
የህዝብ እንባ ሁሌም አሸናፊ ነው !! ክብርና ሞገስ ይህን ተግባር ለሰራችሁ ጓዶች 
ድል ለአዴሃን!!
ድል ለጭቁኑ ህዝብ !!

No comments:

Post a Comment