Thursday, March 10, 2016

የኦሕዴድና የብአዴን አባላት ራሳቸውን ነጻ የሚያወጡበት ግዜ ላይ መሆናቸውን ሊገነዘቡ ይገባል:ነገን አትፍሩት!



የኦሕዴድና የብአዴን አባላት ራሳቸውን ነጻ የሚያወጡበት ግዜ ላይ መሆናቸውን ሊገነዘቡ ይገባል:ነገን አትፍሩት!

Minilik Salsawi - Ethiopian DJ - የኦሕዴድ ይሁን የብአዴን አባላት በባርነት ውስጥ መሆናቸው እሙን ነው:;ሃሳባቸውን በነጻነት መግለጽ አይችሉም ወክለነዋል ስለሚሉት ሕዝብም መናገር አይደለም መተንፈስ አይችሉም::ይልቅ በሙስና ውስጥ ተዘፍቀው ነገን እንዲፈሩ ሕወሓት ጢባጢቤ እየተጫወተባቸው ነው::አገሩ አየሩ አፈሩ መንደሩ ሕዝቡ ለውጥ ለውጥ እየሸተተ ያለበት ብሩህ ዘመን ላይ ደርሰናል ስለዚህ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ካድሬዎች የሕዝቡን ንቃተ ሕሊና ሊጋሩ ይገባል:: እስከመቼ ድረስ የሕወሓት መጠቀሚያ ሆናቹ ከሕዝብ ተጣልታችሁ ትኖራላችሁ::መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃገር ቤት ይሁን በውጪ ያለው በሕወሓት ላይ ከንፈሩን ነክሷል::ትግሉን አቀጣጥሏል::ራሳችሁን መርምሩ ሕዝብን አሊያም ውድቀትን መምረጥ የናንተ ድርሻ ነው::ሕዝብ ያነቃነቀውን ካልነቀለ ወደ ቤቱ አይገባም!!!
የቀድሞውን ወታደራዊ ስርኣት ለመጣል የአሁኑን የሽምቅ ሽብራዊ መንግስት ለማንገስ በበረሃ ትግል የተሳተፉት የኢሕኣዴግ ድርጅቶች በሃገሪቱ የትግል ታሪክ ውስጥ ጉልህ ድርሻ አላቸው::በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስራትን ለማስፈን እጅ ለእጅ ተያይዘን በጋራ ታግለን ህዝባዊ ነጻነትን እናረጋግጣለን በማለት ጫካ የተደባለቁት ድርጅቶች የትግራይን ህዝብ ነጻ በማውጣት ታላቋን ትግራይን እፈጥራለሁ ያለውን ሕወሓት የትግሉ ስኬት ሲከሽፍበት ኢሕዴንን እና ኦሆዴድን በመንተራስ ተረማምዶ ለስልጣን ከበቃ 25 ድፍን አመታትን አስቆጠረ::
በ25 አመት የስልጣን ቆይታው የኢሕዴንን እና የኦሕዴድን የትግል አስታውጾ ላማኮላሸት እና ከታሪክ ሂደት መስመር ለማሳት የተጠቀመባቸው ዘዴዎች እና ወታደራዊውን እና የደህንነቱን ተቋም በአንድ ብሄር በማጠር አባል ድርጅቶቹ እና አባላቱ መላወሻ እንዲያጡ ሲሰራ በአደባባይ ታይቷል::ከአቶ ታምራት ላይኔ የፖለቲካ ጠለፋ ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ ቁጥራቸው ይህ ነው የማይባሉ የኢሕዴን ታጋዮች እና ካድሬዎች በተለያዩ የወንጀል ልጣፎች ከያሉበት ተጠልፈው ወደ ሞት እስር እና ስደት ተግዘዋል:: የኦህዼድ አባላትንም እንዲሁ በመጥለፍ በፖለቲካዊ የኦነግ ታርጋ በማሰር በመግደል እና በተለያዩ ጥቅማጥቅሞች በማሸት አንደበታቸውን አሽጎታል:: ይህ የሕወሓት ስራ ማንም የሚያውቀው እና ጸሃይ የሞቀው ሃቅ ነው:: ቢተነተን የማያልቀው የሕወሓት የውስጥ እና የውጭ ሽብር የሚጋለጥበት ቀን መድረሱ የብኣዴን እና የኦህዴድ አባላት ተግተው በመስራት ላይ መሆናቸውን ሌሎችንም ካድሬዎች እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል::

በገዛ ሃገራቸው በድርቅ እና በረሃብ እያለቁ እየተሰደዱ እየተገደሉ ጥያቄያቸው አልሰማ ያሉት የኦሮሞ እና የአማራ ህዝቦች ኦሕዴድ እና ብአዴንን የመሰለ አሳፋሪ ድርጅት በታሪካቸው ተጋርጠውባቸው አሊያም ባንዳ ሆነው አስፈጅተዋቸው አያውቁም። በጣሊያን ወረራ ጊዜ ለቅኝ ገዢዎች ያደሩ ባንዶች እንኳን ከዛሬዎቹ ኦሕዴዾችና ብአዴኖች የተሻለ ክብር ነበራቸው። ከዛሬዎቹም በተሻለ የድሮ ባንዶች በጌቶቻቸው ጣሊያኖች የሚሉት ይደመጥ ነበር። ኦሕዴድ እና ብአዴን ግን ራሳቸውን ከባንዳነትም አውርደው ባርነት ደረጃ ላይ የጣሉ ከመሆንም አልፎ ባሪያ ሆነው ተለጎመው በመነዳታቸው የሚደሰቱ ሆዳም ሰዎችን የሰበሰቡ ድርጅቶች ናቸው። ኦሕደዽ እና ብአዴን አለቃቸው ሕወሓት ያዘዘውን በመፈጸም የሚረኩ ጥርቅሞች ናቸው። አጉርሱኝ ሲላቸው ያጎርሳሉ፤ጉረሱ ሲላቸው በደስታና በችኮላ ተስገብግበው ይጎርሳሉ።
የብኣዴን እና የኦህዴድ አመራሮች እና ካድሬዎቻቸው ራሳቸውን ከሕወሓት የበላይነት የማላቀቅ ግዴታ አለባቸው::የሕወሓት የበላይነት ከምን የመጣ ነው? ትግል ከሆነ ሁሉን እኩል ድርሻ ያለውን ትግል በጋር ታግለው ነው ወታደራዊውን ስርኣት ያስወገዱት ለሕወሓት ብቻ ማን ይህን እድል ሰጠው? ሕወሓት ብቻውን አልታገለም ብኣዴንም የራሱ ድርሻ ኦሕዴድም የራሱ ድርሻ አለው:; የአማራውና የኦሮሞው ህዝብ ኢሕዴን/ብኣዴንን አይተው ኦሕዴድን አይተው እንጂ ለሕወሓት ሲሉ የእትዮጵያን መሬት በመምራት አልተባበሩም ስለዚህ የብኣዴን እና የኦሕዴድ አመራሮች እና ካድሬዎች ሊገነዘቡት የሚገባው ጉዳይ ትግሉ ሕወሓት ብቻ የመራው ያደራጀው ያሸነፈው አለመሆን እና የድርጅቶቹም ድርሻ እኩል መሆኑን ነው::
በመከላከያው እና በደህንነቱ ዘርፍ ከፍተኛውን ቦታ በመቆጣጠር ሌላውን የእንጀራ ልጅ ያደረጉት ሕወሓቶች የበረሃውን ዳገት እና ቁልቁለት እነሱ ብቻ የተወጡት አድርገው በማቅረብ የቀሪውን ታጋይ ደም እና ድካም ጥላሸት እየቀቡት ነው::የሕወሓት የበላይነት እንዲያበቃ በመከላከያው እና በደህንነት ተቋማት ውስጥ ያሉ የብኣዴን እና የኦሕዴድ ታጋዮች የራሳቸውን አስታውጾ ሊያበረክቱ ይገባል::የትግራይ ሕዝብንም እንደ አረና ካሉ ፓርቲዎች ጋር በመተባበር ከሕወሓት ጫና እና አፈና ልታላቅቁት ይገባል::የፖለቲካ ባርነት እንዲቆም ትግሉን የማቀጣጠል ሃላፊነት አለባቸው:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment