Thursday, March 31, 2016

እውነተኛ ታሪክ በግሌ የማውቀው በወያኔ ትግሬ በመርዝ ተመርዞ ለተገደለው ወንድማች ባሻ ጥጋቡ ነፍስ ይማር!


የአርማጭሆ ሰዉ አብርሃጅራ የነበረዉን የመለስ ቢልቦርድ አዉርዶ ባሻ ጥጋቡ ሆይ ራዕይህን እናስቀጥላለን የሚል ጥቅስ ጽፎ ሰቀለበት!!
ይህ ጽሁፍ ስለ ጀግናዉ እና ድንበር ጠባቂዉ የአርማጭሆ ሰዉ ባሻ ጥጋቡና አርማጭሆ መሳጭ ታሪክ ይዟልና ተከተሉኝ!!
አርማጭሆ በሰሜን ጎንደር ዞን የሚገፈኝ ሲሆን በምዕራብ አርማጭሆ እጅግ ሰፊ የሆነና ለም መሬት በሱዳን መንግስት ቁጥጥር ስር መሆኑን በተለያዩ የአርማጭሆ አካባቢ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች ነግረዉኛል፡፡በዚህ አካባቢ የነበሩ ቦታዎች ሁሉ አረብኛ ትርጓሜ እየተሰጣቸዉ ነዉ ፡፡በእርግጥ ቀደም ባሉት ጊዜያትም ቢሆን ብዙ ቦታዎች የአረብኛ ትርጓሜ ያላቸዉ አሉ፡፤ለምሳሌ አብደራፊ የሚባለዉ ከተማ ስያሜ‹‹አብደላፊ››ከሚል የአረብኛ ቃል የተገኘ ሲሆን ትርጉሙም አብደላ አለ የሚል ነዉ፡፡ያ ማለት ግን አካባቢዉ የሱዳን ነዉ ወይም ነበረ ማለት አይደለም፡፡ህዝቡ አረብኛን አቀላጥፎ ይናገራል፡፡የሆነዉ ሆኖ በርካታ ኪሎሜትሮችን የሚሸፍን መሬት ከ2000ዓ.ም በፊት በእኛ ገበሬዎች ስር የነበረ መሬት አሁን ከዚህ የለም፡፡ ህዝቡም በስጋት ሌሎች የተረፉ ድንበር ላይ ያሉ አረብኛ ስያሜ ነበራቸዉን ቦታዎች ሁሉ ወደ አማራኛ እየቀየራቸዉ ነዉ፡፡ለምሳሌ ያክል ቀድሞ ‹‹ኮርኹመር ››ትባል የነበረችዉ ትንሽየ መንድር አሁን‹‹ጠፈረወርቅ›› ተብላለች፡፡
አሁን የጀግናዉን የአርማጭሆ ሰዉ የ ባሻ ጥጋቡን ጉዳይ እናንሳ፡፡
ባሻ ጥጋቡ በሱዳን የገደራፊ ግዛት ስሙ የናኘ ነበር፡፡ባሻ ጥጋቡ ለተበደለ ሰዉ የሚቆምና በሀይለኛነቱ የሚፈራ የራሱ ሚሊሻዎች የነበሩት አንድ የአርማጭሆ ግለሰብ ነዉ፡፡እንዲያዉም ሱዳኖች ‹‹ባሻ ጥጋቡ ይቅር እንጅ መለስስ ይምጣ››ይሉ እንደነበር ይወራል፡፡ድፍን አርማጭሆ ፍትህ ሲጎድልበት የሚያመለክተዉ ለምዕራብ አርማጭሆ ፖሊስ አሊያም አስተዳደር ጽ/ቤት አልነበረም ለባሻ ጥጋቡ እንጅ፡፡ባሻ ጥጋቡ በደል ያደረሰዉን ሰወ ወዲያዉኑ እንዲያስተካከል የፍትህ ርትዕትን ያስጠብቃል፡፡ የሱዳን መንግስት ለም የሆነዉን የአርማጭሆ መሬት በወሰደ ጊዜ የባሻ ጥጋቡን መሬት ማንም ሊደፍረዉ አልቻለም፡፡እንደሚባለዉ የባሻን መሬት አልፈዉ ሱዳኖች ወደ መሀል ሲገቡ መካከል ላይ የባሻ መሬት ይገኛል፡፡ ሆኖም ሰዉ ሆኖ ከሞት የሚያመልጥ የለምና ይሀ ጀግና በ2005ዓ.ም ታሞ ከዚህ አለም ተለየ(እርግጥ ነዉ ለህክምና አዲስ አበባ በሄደበት ወቅት ሆን ተብሎ ተገድሏል የሚባል ሀሜትም አለ)፡፡
የባሻ ጥጋቡ ተዝካር እለት አንድም የአርማጭሆ ሰዉ አልተጠራም ነገርግን አንድም የአርማጭሆ ሰዉ የቀረ የለም፡፡ ህዝቡ አዘነ ተዝካሩን ተሰባስቦ አወጣ፡፡ የባሻ ጥጋቡን ሞት የሰሙ ሱዳናዊያን የባሻን የእርሻ መሬት ለመቀማት የባሻ ጥጋቡን ካንፕ ወረሩት ፡፡ በዚህ ጊዜ የሚገርም ነገር ተከሰተ ፡፡አንዲት የአርማጭሆ መነኩሴ ቆባቸዉን ጥለዉ ክላሽ አንግተዉ ‹‹ገና ለገና››ባሻ ሞቷል ተብሎ ርስቱን ሊደፈር ነዉ››በማለት ለጦርነት ሄዱ፡፡አብራሀጅራ የነበረዉን የመለስ ቢልርድ የአርማጭሆ ሰዉ አዉርዶ በምትኩ ባሻ ጥጋቡ ሆይ ራዕይህን እናስቀጥላለን የሚል ጥቅስ ጽፈዉ ሰቀሉበት፡፡ይህ ተረት ተረት አይደልም ትናንት በጀግኖች የአርማጭሆ ልጆች የተፈጸመ እዉነታ እንጅ፡፡
(የአማራ ህዝብን በደል በጉራፈርዳ በአመያ በቡንሻንጉል በሁመራ ወልቃይት ቋራ ቦታዉ ድረስ እየተመለከተ መረጃ የሚያደርሰን ሙሉቀን ተሰፋዉ ከአዘጋጀዉ የቀለም ቀንድ ጋዜጣ ቅጽ 3ቁጥር 35መጋቢት 20 2008ዓ.ም እትም የተወሰደ)
ክብር ለሚገባዉ ክብር እንስጥ!!
ድል ለ ሰፊዉ የአማራ ህዝብ!!!

Desalegn Bete Amhara'

No comments:

Post a Comment