Friday, March 11, 2016

(የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ)


የህወሓት አገዛዝ በተለያዩ መሸንገያዎች በማታለልና አስገድዶ በማፈን ያለፍላጎታቸው ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ማዕከል ያስገባቸውን ወጣቶች በለብለብ አሰልጥኖ በማውጣት በየግንባሩ ለእርድ አሰለፋቸው፡፡
ተገደውና ተታለው ወደ ብርሸለቆ ማሰልጠኛ ማዕከል ከወራት በፊት የገቡት ስራ አጥ የሆኑ አፍላ ወጣቶች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ነበር እንደነገሩ የተሰጣቸውን የለብለብ ስልጠና ጨርሰው በመውጣት በየግንባሩ የተበተኑት፡፡
ከእነዚህም ህወሓት ለስልጣኑ መሰዋዕት ሊያደርጋቸው በብር ሸለቆ ማሰልጠኛ ማዕከል አሰልጥኖ ካወጣቸው የድሃ ልጅ ለጋ ወጣቶች መካከል 1180 የሚሆኑት ከሰኞ ዕለት ጀምሮ በጎንደር በኩል ወደ ዳንሻ እና ሁመራ ተጓጉዘው 24ኛ እና 5ኛ ሜካናይዝድ ክፍለ ጦሮችን ተቀላቅለዋል፡፡ ቀሪዎቹ ደግሞ ወደ አፋር ክልል በረሐሌ ተጭነዋል፡፡
የቆየው ሰራዊት በስርዓቱ ተማሮና ተስፋ ቆርጦ ያለማቋረጥ በገፍ እየከዳ መሆኑን ከዚህ ቀደም በተደጋጋሚ መዘገባችን አይዘነጋም፡፡

No comments:

Post a Comment