በኤፈርት ስር የሚገኘው የትራንስ ኢትዮጵያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሰራተኞች የሆኑ ከ200 በላይ የከባድ ጭነት መኪና ሹፌሮች “በኦሮምያ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር ለህይወታችን አስጊ በመሆኑና በፌደራል ፖሊስ እየተጠበቅን መስራት ስላስጨነቀን ችግሩ እስኪፈታ ድረስ ስራ እናቆማለን” የሚል መልእክት ያለው ደብዳቤ መቐለ ለሚገኘው ለትራንስ ኢትዮጵያ መስርያ ቤት በማስገባት ግልባጩን ለትግራይ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ኣባይ ወልዱ ለመላክ እየተዘጋጁ መሆኑን የአረና ፓርቲ አመራር የሆነው አምዶም ገ/እግዚአብሄር በማህበራዊ ድረ ገጹ አስፍሯል።
የከባድ ጭነት ተሽከርካሪ ሹፌሮቹ “እኛ አገራችን እያገለገልን ሳለ በኦሮምያ ያለው የፀጥታ ሁኔታ ለህይወታችን አ ስጊ ሆኖብናል፣በፌደራል ፖሊስ እየታጀብን መንቀሳቀስም ሰልችቶናል። መንግስት ፀጥታውን በአስተማማኝ ሁኔታ ሲያስከብር ወደ ስራችን እንመለሳለን” በማለት ውሳኔያቸውን አስታውቀዋል።
የኤፈርት ሃብት በትግራይ ህዝብ ስም የተከፈተ ኢንደውመንት ቢሆንም እስካሁን ከ10 በማይበልጡ የህወሓት መሪዎች ብቻ የሚሽከረከርና ኦዲት ተደርጎ የማያውቅ ግዙፍ ካፒታል የሚያንቀሳቅስ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል።
የኢህአዴግ መንግስት በኦሮሚያ ክልል የተነሳበትን ተቃውሞ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በመግለጽ ተቃውሞ ይደረግባቸው በነበሩ ከተሞች ውስጥ የሚገኙ ትምህርት በቤቶችና የንግድ እንቅስቃሴዎች ወደመደበኛ ተግባራቸው መመለሳቸውን ቢገልጽም የትራንስ ኢትዮጵያ የከባድ ጭነት መኪና ሹፌሮች የወሰዱት የስራ ማቆም አድማ አካባቢው መንግስት እንደሚለው ወደመደበኛ ሰላማዊ ሁኔታው ላለመመለሱ አይነተኛ ማሳያ ይሆናል፡፡
ምንጭ -አምዶም ገ/ስላሴ
Extraordinary Post !! Extremely intriguing theme will bookmark your for visit again..nice post.......
ReplyDeleterental mobil cibinong bogor