Monday, March 21, 2016

በኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉንም ወገኖች ያካተተ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋምና አገሪቱን እንዲታደጋት አንድ የተቃዋሚ መሪ ጠየቁ፣በእስራኤል የሚገኙ በሺህ የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዊያን በቴላቪቭ መንግስት ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ወጡ፣ ሁለት የጅቡቲ የጦር ምርኮኞች ከኢርትራ እስር ቤት አምለጠዋል፣13 እስረኞችም በኢርትራ ማጎሪያ ቤት ይገኛሉ ተብሏል ፣የኢትዮጵያው አገዛዝ ይምጡልኝ ብሎ አልቀበላቸውም ብሎ የመለሳቸው አራት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በመጪው አርብ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ፣ምዕራባዊያን አገራት እና ለጋሾ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያለውን የሰብዊ መብት ረገጣ ችላ እንዳይሉ ተጠየቁ የሚሉና ቃለ መጠይቅ ከሕጋዊው መኢአድ ፕሬዝዳንት፣ከድምጻዊ ዳዊት መኮንን(አኑፌን ጂራ)፣ከወልቃይት ጠገዴ የልሳነ ግፉአን ድርጅት ተጠሪ እና ልዩ ወቅታዊ ሌሎችም

<…ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ሁኔታ እጅግ አደገኛ ነው።ለውጥ እንዲመጣ የሚሰራው ተቃዋሚ የግድ በጋራ መምከርና በአንድ ላይ መቆም ያለበት ወሳኝ ወቅት ነው።መንግስት ገድዬ አስሬ ሕዝቡን ጸጥ አደርጋለሁ የሚለው የሚቻል አይደለም። ሕዝቡ ከተባበረ መሳሪያ የያዘውም አልተኩስም የሚልበት ጊዜ ይመጣልተቃዋሚዎችበትላንትና ጉዳይ መጨቃጨቅ ወደሁዋላ መሄድ የለባቸውም ወደፊት የአገሪቱን ህልውና ለማቆየት ተነጣጥሎ ሳይሆን ሁሉም በጋራ አንድ ላይ መቆም አለበት ይሄካልሆነ ግን የጋራ አገር … >
አቶ ማሙሸት አማረ ሕጋዊው የመኢአድ ፕሬዝዳንት በወቅታዊ የአገሪቱ ጉዳይ ላይ ከሰጡን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ   (ሙሉውን ያዳምጡት)
<…ወሰኔን የማያውቅ አለወሰኔም አምቦ ገላ ገልገላም የቆዩ የሕዝብ ዜማዎች ናቸው እኔ እንደገና ዘፈንኳቸው። ኦሮሞ አንድን ነገር አለምክንያት አይናገርም  አምቦሲመሻሽ ይላል …ሕዝብ ከሕዝብ ጋር ተጋጭቶ አያውቅም የሚያጋጩት ስርዓቶች ናቸው። እነሱ እርስ በእርስ ለማጋጨት የቤት ስራ ሰጥተውናል የነሱን የቤት ስራ ወደጎን …>>
ድምጻዊ ዳዊት መኮንን(አኑፌን ጂራስለአዲሶቹ ዜማዎቹ እንዲያወጋን ካብዘነው    ከሰጠን ቃለ መጠይቅ የተወሰደ ( ሙሉውን ያዳምጡት)
<…በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ላይ የሕወሃት አገዛዝ የከፈተው የዘር ማጥፋት ወንጀል ወደር የለውም  የዛሬውም በጠለምት የተነሳው ተቃውሞ በሕጋዊመንገድ የህዝቡን ጥያቄ ለማቅረብ ከተነሱ ኮሚቴዎች ውስጥ የወጣት ሉላይን ታፍኖ መወሰድን በመቃወም ነው እነሱ ከትግራይ አምጥተው ያሰፈሯቸው እናያስታጠቋቸው ወደላይ ከሕዝቡ ፊት ተኩስ ከፈቱየትግራይ ነጻ አውጪ ለመሬት መስፋፋት ሲል በወልቃይት ላይ የሚያደርሰውን ግፍ ለማዳፈን ጥያቄውንአልቀበልም ብሎ ከዚህ ቀደም ከትግራይ አምጥቶ ካሰፈራቸው ስድት መቶ ሺህ ሰፋሪዎች በተጨማሪ ሰማ አምስት ሺህ አሁን አምጥተው ሪፈረንደም እናደርጋለን ይላሉይሄ ተቃባይነት የለውም …>
አቶ ቻላቸው አባይ የወልቃይት ግፉአን ማህበር ተጠሪ በአሁኑ ወቅት በጠለምት የተነሳውን ሕዝባዊ ተቃውሞ አስመልክቶ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ከሰጡን ምላሽ(ሙሉውን ያዳምጡ)

በኦሮሚያ ክልል የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የተወሰዱ የመብት ረገጣዎችን የዳሰሰ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት ሲዳሰስ(ልዩ ጥንቅር)
የዲሞክራቲክ ኮንጎን ምስቅልቅል ለመቀየር ገንዘባቸውን እና ራዕያቸውን በመሰነቅ ከአሜሪካው የኮለራዶ ግዛት ወደ አገራቸው ለመግባት የቆረጡት ቱጃር መጻኢውጥን እና ምኞት ሲቃኝ (ልዩ የዜና ዳሰሳ)
ልዩ ጥንቅርሌሎችም
ዜናዎቻችን
በኢትዮጵያ ውስጥ  ሁሉንም  ወገኖች ያካተተ  የሽግግር መንግስት  እንዲቋቋምና አገሪቱን እንዲታደጋት አንድ የተቃዋሚ መሪ ጠየቁ
በእስራኢል የሚገኙ በሺህ የሚቆጠሩ ቤተ እስራኤላዊያን በቴላቪቭ መንግስት ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ወጡ
ቀለማችን ቢለወጥ ኖሮ ይህ ሁሉ በደል እና ግፍ አይደረሰብንም ነበር “የህግ አረቃቂዎች
ሁለት የጅቡቲ የጦር ምርኮኞች ከኢርትራ እስር ቤት አምለጠዋል፣13 እስረኞችም በኢርትራ ማጎሪያ ቤት ይገኛሉ ትብሏል
የኢትዮጵያው አገዛዝ ይምጡልኝ ብሎ አልቀበላቸውም ብሎ የመለሳቸው አራት ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በመጪው አርብ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ
 በሶማያ የሚገኝው የኢትዮጵያ ጦር የገንዘብ እጥረት እንዳይገጥመው ተሰግቷል፣አለማቀፉ ማህበረስብ ችግሩን እንዲቀረፍ ጥሪ ቀረቧል
ምእራባዊያን አገራት እና ለጋሾ ድርጅቶች በኢትዮጵያ ያለውን የሰበዊ መብት ረገጣ ችላ እንዳይሉ ተጠየቁ
ርሃቡን በቁጥጥር ስር እንዳረጋለን ያሉት አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ አለማቀፉ ማህበረሰብ ካልደረሰልን ሁኔታዎች ይከፋሉ ሲሉ ጥሪ አቀረቡ
<<ወሬ ብቻውን ፋይዳ የለውም>> አቶ ሃይለማሪያም ለአለማቀፉ ማህበረሰብ የላኩት ሰሞነኛ መልእክት
ፕሬዝዳንት ኦባማ አገራቸው ከወራት በፊት ከአሸባሪነት መዝገብ ስሟን ወዳወጣቻት ኩባ ከነቤተሰባቸው ተጉዋዙ
ሌሎችም ዜናዎች አሉ
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትርዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወልብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል።
ዘወትር በድህረ ገጻችን፣  googel app store Hiber Radio ወደ ስልክዎ በመጫን ካልሆነም በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

3 comments:

  1. ሰላም,
    እኔ ለድርጅቶች, መ / ቤቶች, ድርጅቶች, ወዘተ 2% ወለድ እዳ የሚሆን ገንዘብ ብድር የሚያቀርብ ብድር የሰጠው የብድር ብድር አቅራቢው እኔ ጆሴፍ ጆርሃል ነኝ. ዕዳዎን ለመክፈል ፈጣን ብድር ይፈልጋሉ? ንግድዎን ለማሻሻል ብድር ይፈልጋሉ? ባንኮች እና ሌሎች የፋይናንስ ድርጅቶች ተቀባይነት አላገኙም ማለት ነው? የተበዳሪ ብድር ወይም ወለድ ያስፈልግዎታል? ሁሉም ችግሮችዎ ተጠናቀዋል ሁሉም የፋይናንስ ችግሮችዎን ያለፈ ጊዜ እናደርጋለን.
    ተጨማሪ ዝርዝሮችን ለማግኘት በ (Joshhawleyloanfirm@gmail.com) በኩል ኢሜይልዎን ያነጋግሩ.

    ከሰላምታ ጋር!

    ReplyDelete
  2. ፈጣን ብድር ይፈልጋሉ? በሚፈልጉት ብድር ልንረዳዎ እንችላለን.
    ለንግድ ሥራ ልማት የግል ብድር እና ብድር እንሰጣለን.
    የግል ብድር (ከ $ 1,000 እስከ 550,000 ዶላር)
    የንግድ ብድር (ከ $ 5,000 እስከ $ 100,000,000)
    ዓመታዊ የወለድ መጠኑ 3% ነው.
    ኢ-ሜል: (allstaeloanservicecompany@gmail.com)

    ከሰላምታ ጋር
    አቶ Asif Lotia
    ሁሉም የመንግስት የብድር አገልግሎት ፋይናንስ ኩባንያ
    ኢሜል: (allstaeloanservicecompany@gmail.com)
    ምን APP-CONTACT NUMBER +919629412483

    ReplyDelete
  3. Have you been looking for financing options for your new home purchase, construction, real estate loan, refinance, debt consolidation, personal or business purpose? Welcome to the future! Financing made easy with us. Contact us as we offer our financial service at a low and affordable interest rate of 3% for long and short loan term, with 100% guarantee loan, Interested applicant should contact us for further loan acquisition procedures via: joshuabenloancompany@aol.com

    ReplyDelete