Saturday, March 19, 2016

የወቅታዊ ተግባራዊ ትግል (ወተት) መልዕክት: በግልጽ ጦርነት ውስጥ ካልሆን በህቡዕ ጦርነት እንሳተፍ !(ክፍል 3)ዶ/ር ታደሰ ብሩ

 እያንዳንዱ ነፃነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ ሊሳተፍባቸው ከሚችሉ የህቡዕ ጦርነት ስልቶች ውስጥ አሻጥር፣ የስነ-ልቦና ጦርነት፣ የኢኮኖሚ ጦርነት፣ እና ኢህአዴግን እርስበርሱ ማናከስ የተባሉት ለአብነት እንደማቀርብ ቃል ገብቼ “አሻጥርን” እና “የስነልቦና ጦርነትን” በክፍል 1 ና 2 ተመልከታል። ይህ ክፍል የኢኮኖሚ ጦርነት ላይ ያተኩራል።
ሐ. የኢኮኖሚ ጦርነት - ከሁሉን ጠቅላይ (totalitarian) አገዛዝ ጋር የሚደረገው ትግል አስቸጋሪ ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱ ሥርዓቱ ራሱን የአገሪቱን ሀብት ባለቤት የሚያደርግ መሆኑ ነው። አገዛዙን ታማኝነትን ይገዛል፤ በአገዛዙ ተጠቃሚ የሆኑ ቡድኖችና ግለሰቦች ሥርዓቱን ለመከላከል የግል ፍላጎት እንዲኖራቸው ያደርጋል። በአንፃሩ አገዛዙን የሚቃወሙ ቡድኖችም ሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በኢኮኖሚ እንዲዳከሙና በድህነት እንዲማቅቁ ይደረጋል።
በአሁኑ ሰዓት በአገራችን ማን ሀብታም፣ ማን ደግሞ ድሀ መሆን እንዳለበት የሚወስነው ህወሓት ነው። በዚህም ምክንያት ጥቂት የህወሓት ባለሟሎች እና ከየክልሉ የመለመሏቸው አገልጋዮች ከዚህ በፊት ሆኖ በማያውቅ መጠን ሀብት ያጋበሱ ሲሆን በቁጥር እጅግ የበዛው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአስከፊ ድህነት እየማቀቀ ነው። እዚህ ሀቅ ላይ ቆመን ስናየው ነው በአገዛዙ ላይ የኢኮኖሚ ጦርነት ማወጅ ፍትሀዊ መሆኑን የምንረዳው።
ተግባራዊ ልናደርጋቸው የሚገቡ በርካታ የኢኮኖሚ ጦርነት ስልቶች አሉ፤ ዋና ዋናዎቹን ከዚህ በታች አቀርባለሁ።
1. ገንዘብ - ለኢኮኖሚ ጦርነት ቀዳሚ ትኩረት የሚሻው ለግብይት የሚውለው ወረቀት ወይም ገንዘብ ነው። የገንዘብ ዝውውርን የሚያዛቡ እርምጃዎች የመንግሥትን ሥልጣን የያዘ ጠላትን ኢኮኖሚ የማናጋት አቅማቸው ከፍተኛ ነው።(በነገራችን ላይ፣ ህወሓት በረሀ እያለ ከአልባኒያ የተቀበለው ትልቁ ስጦታው የገንዘብ ማተሚያ ማሽን እንደነበር ይነገራል) ከቅርብ ጊዜ ታሪካችን ገንዘብ ላይ ያተኮረ የተቀናጀ ተቃውሞ እኔ የማውቀው የሙስሊም ወገኖቻችን ጠርተውት የነበረው የሳንቲሞች መሰብሰብ ዘመቻ ነበር። ይህ መበረታታ የሚገባው ጥሩ ጅማሮ ነው፤ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ግን ወደ ወረቀት ገንዘብ (የብር ኖቶች) ማሳደግ ይገባል።
በቀላሉ ሊታሰብባቸው የሚገቡ የኢኮኖሚ ጦርነት ስልቶች አሉ። 
— ለሥርዓቱ የተለየ ቅርበት ካላቸው ባንኮች (ለምሳሌ ውጋገን፣ አንበሳና አባይ ባንኮች) ገንዘባችን ማውጣት ያለብዙ ችግር ሊተገበር የሚችል ነገር ነው። 
— በውጭ አገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚገኙ ዘመዶቻቸው የሚልኩት ገንዘብ የሥርዓቱ አገልጋዮችን በማይጠቅም መንገድ ማድረግ (ጥናትና ዝግጅት የሚጠይቅ ቢሆንም) ይቻላል።
— የሥርዓቱ አገልጋዮች የሚያሸሹትን ገንዘብ እየተከታተሉ ማጋለጥ ሌላው መበረታታት ያለበት ዘርፍ ነው። በኔ rapid assessement መሠረት ለንደን ከተማ ውስጥ ባሉ የግል የገንዘብ ላኪዎች አማካይነት ብቻ በየቀኑ በአማካይ 400,000 የእንግሊዝ ፓውንድ ከኢትዮጵያ ወጥቶ ለንደን ይገባል። እኛ በተለምዶ “ገንዘብ ከእንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ ላክን” እንላለን እንጂ በተግባር የሚፈፀው እኛን ተጠቅመው እነሱ ናቸው ገንዘብ ከኢትዮጵያ ወደ እንግሊዝ ነው የሚልኩት - እነሱ እዚያ በብር ከፍለው እንግሊዝ በፓውንድ ይቀመጥላቸዋል፤ አሊያም በሌላ አገር ለገዙት ሸቀጥ ይከፈልላቸዋል። ይህ ስሌት ሩቅ ምስራቅ አገሮችን ተዟዙሮ በኢንቨርስትመት ባንክ አማካይነት የሚመጣው በርካታ ሚሊዮች ፓውንዶችን ሳይጨምር ነው። እኔ የእንግሊዝ አገሩን ብቻ ነው ያነሳሁት፤ የአሜሪካው ሀቅ የዚህ ብዙ ጊዜ እጥፍ ይሆናል። ወደ ጀርመን፣ ኖርዌይና ስዊድን የሚፈሰው የኢትዮጵያ ሀብት መጠኑ ከፍተኛ ነው። በ10 ዓመታት ውስጥ 17 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከኢትዮጵያ መውጣቱ ዓለም ዓቀፍ ፋይናንሺያል ኢንተግሪቲ መግለጹ እዚህ ላይ ማስታወሱ ይጠቅማል፤ ይህ እነሱ የደረሱበት ነው እንጂ ሀቁ የዚህ ብዙ ጊዜ እጥፍ ነው። 8 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ያወጣል በተባለው “ላም አለኝ በሰማይ” ግድብ ሳቢያ ስንት ሕዝብ ጾሙን እንዳደረ፤ ስንቱ በፕሮፖጋንዳ ጆሮው እንደደነቆረ እያሰብን የሥርዓቱ አገልጋዮች የሚያሸሹትን ገንዘብ ስናሰላ ምሬቱ አንጀታችን ውስጥ ዘልቆ ይሰማናል። በዚህ ዓይን አውጣ ዘረፋ ላይ ጦርነት መክፈት ፍትሀዊ ነው።

2. የሸማቾች አድማ - በግዢ ላይ እቅባ የማድረግ ልምዳችን እምብዛም የሚያወላዳ አይደለም፤ ሆኖም ግን በቶሎ ልንማረው የምንችለው የኢኮኖሚ ጦርነት ስልት ነው። በምርጫ 97 ዋዜማ እና ማግስት በዳሽን ቢራና በፔፕሲ ላይ ተጠርተው የነበሩ የግዢ እቀባዎች በመጠኑም ቢሆን ውጤታማ ነበሩ። እኔን ጨምሮ አንዳንድ ሸማቾች እነዚህን ሸቀጦች እንደጠሉ ናቸው። ከዚህ በተረፈ በአንዳንድ የዘፈን ኮንሰርቶች እና የስነስሁፍ ውጤቶች ላይ የተጠሩ ማዕቀቦችን አስተውያለሁ። ከዚህ ያለፈ የአገዛዝ ሥርዓትቱ ያንገዳገደ የሸማቾች አድማ መትተን አናውቅም። አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉት ሁኔታዎች ለተባበረ እርምጃ (Collective Action) የተመቹ በመሆናቸው የተከበሩ ሰዎችና ድርጅቶች የግዢ ማዕቀብ አድማ ቢጠሩ የመሳካት እድል አለው ብዬ አምናለሁ። በቀላሉ ሰሚ ጆሮ ያገኛሉ ብዬ የማስባቸው የማዕቀብ ዓይነቶች
— ሰላም አውቶቡሶች ላይ አለመሳፈር፤ 
— የአገዛዙ ቀንደኛ አባላት የሆኑ ነጋዴዎች ንብረት በሆኑ ቡና ቤቶችና ምግብ ቤቶች አለመጠቀም፤ 
— በአገዛዙ ሰዎች ንብረትነት በተያዙ የግል ኮሌጆች አለመማር፣
— በአገዛዙ ሰዎች ሆስፒታሎችና የግል ክሊኒኮቻቸው አለመታከም፤ 
ውጋጋን፣ አንበሳና አባይ ባንኮችንና ኢንሹራንሶቻቸውን አለመጠቀም።

3. የመግሥት ግብር አለመክፈል - በአምባገነን ሥርዓት ውስጥ ግብር የመዝረፊያ መሳሪያ ነው። እንደህወሓት በግብር የተጫወተ አገዛዝ ማግኘት ከባድ ነው። አንድ ሰው በሽሙጥ መልክ እንደገለፀው ኢትዮጵያ ውስጥ የራስ፣ የቤት ልጅ፣ የዳር ልጅ፣ እና የእንግዴ ልጅ የሚባሉ አራት የግብር ዓይነቶች አሉ። የኤፈርት ድርጅቶች የራስ ልጆች ናቸው ቁጥራቸው ከ100 በላይ ነው። እነዚህ ኩባንያዎች ልዩ እንክብካቤ የሚደረግላቸው ናቸው፤ የመንግስት ቤት፣ የህዝብ ቦታ፣ ንብረት ሁሉ በቅሚያም ሆነ በዝርፊያ እንዲያም ሲል በወረራ ይሰጣቸዋል። ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ያለ ምንም መያዣ የፈለጉትን ያህል የገንዘብ ብድር ይሰጣቸዋል፤ ተበዳሪዎቹ በተመቻቸው ጊዜ ብድር መክፈል ይችላሉ፤ መክፈል ከከበዳቸውም ብድሩ ይሰረዝላቸዋል። የግብር ሸክም እነሱ ጋ የለም። የቤት ልጆች የሚባሉት ደግሞ ሚድሮክ፣ የብአዴን፣ የኦህዴድ፣ የደህዴን ኩባንያዎች ናቸው። እነዚህ ብዙ ጥቅም ያገኛሉ፤ ብድር ግን አይሰረዝላቸውም። የዳር ልጆች የሚባሉት እየተለማመጡ፣ እየተሞዳሞዱ የሚኖሩ ነጋዴዎች - ቴሌቶን በሚኖርበት ጊዜ ታማኝነታቸውን ለማስመስከር የሚሯሯጡ - ለዚህም ካሳ እንዲሆናቸው አንዳንዴ “ልማታዊ ባለሀብት” ተብለው ሲወደሱ ሌላ ጊዜ ደግሞ በታክስ ማጭበርበር ቃሊቲ የሚላኩ። የእንግዴ ልጆች ደግሞ የታክስ ሥርዓቱ የሚያባትታቸው፣ የሚያስጨንቃቸውና የሚያሳድዳቸው ናቸው። እንዲህ “ግብር” በተሰኘ ሽፋን የሚሰራ የዘረፋ ሥርዓት መቃወም ፍትሀዊ ነው። ግብር ያለመክፈል አድማ በተወሰኑ የአማራ ወረዳዎች ተሞክሯል፤ መበረታታት ያለበት ነገር ነው። የአባይ ቦንድ መዋጮ እና የኢህአዴግ የአባልነት መዋጮ አንከፍልም ያሉ መምህራን አሉ። ይህን ማጠናከር ይገባል። ቀድሞውኑ እጁ ውስጥ ስለማይገባ ደመወዝ ተከፋይ በግብር ላይ የወሰን ሥልጣን የለውም። ግብር ከፋይ የሆኑ አነስተኛ ቢስነሶች ግን ይህ እድል አላቸው። በሚቻለው ሁሉ ግብርን ማዘግየት፣ ማዛባት፣ አልከፍልም ማለት ፍትሃዊ ነው። በሰበብ አስባቡ የሚመጡ መዋጮዎችን አለመክፈል የኢኮኖሚ ጦርነቱ አንዱ ስልት ነው።

4. “ኢንቨስተሮችን” ማዋከብ - የሀገራችን አርሶ አደሮች ቁራጭ መሬት አጥተው ቤተሰቦቻቸውን መቀለብ አቅቷቸው እያለ፤ “ኢንቨስተር፣ ልማታዊ ባለሀብት” እየተባለ የሚቆላመጡ ቱጃሮች በ 100 ሺህ ሄክታር የሚገመት ለም መሬት ነፃ በሚባል ዋጋ ይሰጣቸዋል። ወገኖቻችን በአንዱ ክልል ወደ አንዱ ተሻግረው በማረሳቸው ባዕድ ተደርገው ሲባረሩ፤ ባህር አቋርጠው ለመጡ ቱጃሮች መሬት ብቻ ሳይሆን ብድር እየተሰጣቸው ባለሥልጣናቱ ያሸረግዱላቸዋል። ይህንና የተያያዘውን ሁሉ በአንድነት ስናስተውል በኢንቬስትመንት ስም ለም መሬቶችን የሚዘርፉ፤ ድሆችን የሚያፈናቅሉ የሥርዓቱ አገልጋዮች የኢኮኖሚ ጦርነት ዒላማዎች መሆናቸው ፍትሀዊ መሆኑን እንገነዘባለን። የኢንቨስተሮችን ሀብት መዝረፍና ለትግል ማዋል፤ መዝረፍ ካልተቻለ ማቃጠል፣ ማበላሸት ይገባል።
5. ዓለም ዓቀፍ እርዳታዎችና ብድሮች እንዳይሰጡ በለጋሽ አገሮች ላይ ጫና ማድረግ - እንደ ህወሓት አገዛዝ የውጭ እርዳታ ያገኘ መንግሥት ኢትዮጵያ ውስጥ የለም። እርግጥ ነው ርዳታዎች የአገዛዙን ሰዎች ኑሮ አሻሽለዋል፤ የድሀውን ሕይወት ግን በከፍተኛ ሁኔታ ጎድተዋል። ርዳታ የገዢዎች መሣሪያ ሆኗል። 500 ሚሊዮን የእርዳታ ገንዘብ የት እንደገባ አለመታወቁ በቅርቡ ብዙ ክርክር አስነስቶ እንደነበር የምናውቀው ነው። አሜሪካና እንግሊዝ በሚሰጡት የመሣሪያና የስልጠና እርዳታ ኢትዮጵያዊ ድሀ ይደበደብበታል፤ ይገደልበታል። በእንግሊዝ ርዳታ የሰለጠኑ የህወሓት ሰላዮች የኢትዮጵያን ሕዝን ቁም ስቅሉን ያሳዩታል። በዚህ ሁኔታ ዓለም ዓቀፍ ርዳታን በድፍረት መቃወም ፍትሀዊ ነው። ለጋሽ አገሮች የሚሰጡት ገንዘብ ከምን ተግባር ላይ እየዋለ እንደሆነ እንዲያጣሩ መወትወት አይበቃም፤ እነሱ በሚሰጡን ርዳታ ምን ያህል እየተጎዳን እንደሆነ መንገር ይኖርብናል።
+++ ይቀጥላል +++

No comments:

Post a Comment