Monday, March 21, 2016

ሰበር ዜና – በዳንሻ ግጭት ተፈጥሯል። በትግራይ ልዩ ፖሊስና በወልቃይቶች መሀል የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል በትግራይ ልዩ ፖሊስና በወልቃይቶች መሀል የተኩስ ልውውጥ ተደርጓል መንገዶች ተዘግተዋል። በአቅራቢያ ባሉ መንደሮች የሚገኙ የወልቃይት ነዋሪዎች ተቃውሞ እያሰሙ ነው።


አቶ ሲሳይ ብርሃኔ የተባለ ወጣት ከሁለት ቀናቶች በፊት ከሚኖርበት ዳንሻ ከተማ በታጣቂዎች ታፍኖ መወሰዱን የሰሙት የወልቃይት ጠገዴና የአካባቢው ህዝብ ሲሳይ የተወሰደበትንና የሚገኝበትን ሁኔታ የዳንሻ ከተማ አስተዳደርን ሲጠይቁ ቆይተዋል፡፡ባለትዳርና የሁለት ልጆች አባት መሆኑ የተነገረለት ሲሳይ የወልቃይትን አማራነት በይፋ በመናገር ለወቅታዊው እንቅስቃሴም ድጋፉን እንደሚሰጥ መታወቁ ለአፈናው ምክንያት ሳይሆነው እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡
ከዛሬ ረፋድ ጀምሮም በሲሳይ ጉዳይ ምላሽ ከአስተዳደሩ ያጡ የወልቃይትና የአካባቢው ነዋሪዎች ወደ ዳንሻ በማምራት የከተማይቱን አስተዳደርና የፖሊስ ጣብያዎችን መውረራቸውን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ወደከተማይቱ የሚያስገቡ መንገዶች በተቃውሞ ምክንያት የተዘጉ ሲሆን ተቃውሞውን ለመቀላቀል ከአርማጭሆ ጭምር በዛ ያሉ ሰዎች ወደዳንሻ ለመምጣት እንቅስቃሴ መጀመራቸው ይነገራል፡፡
sisay
አቶ ሲሳይ ብርሃኔ
በዳንሻና ሶሮቃ ማምሻውን የታጠቁ የትግራይ ክልል ፖሊሶችና ሚሊሻዎች በብዛት በመግባታቸውም ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገ መሆኑን ከአካባቢው የተገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ዳንሻዎች በስርዓቱ ያልታጠቁ ከዚህ ቀደም ነበራቸውንም ትጥቅ በመፍታት ሰላማዊ ኑሮ የጀመሩ በመሆናቸው ምሽቱን የገባውን ታጣቂ ኃይል መከላከል አለመቻላቸውም ተነግሯል፡፡

አካባቢው ከወልቃይት የማንነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ ከፍተኛ ውጥረት የነገሰበት በመሆኑም የዛሬው የዳንሻና ሶሮቃ የተኩስ ልውውጥና የወጣቱ ታፍኖ መወሰድ ውጥረቱን ሊያፈነዳው እንደሚችል ይገመታል፡፡

No comments:

Post a Comment