Friday, March 11, 2016

ከአዲስ አበባ ወደ ወልዲያና ወደ መቀሌ የሚጓዙ አውቶቡሶች ላይ ጥቃት ደረሰ

sky busአንድ ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ በስርዓቱ የተማረረ የተባለ ኢትዮጵያዊ በወሎ ሰንበቴ በተባለ ቦታ በሁለት የሕወሓት ባለስልጣናት ንብረት በሆኑ አውቶቡሶች ላይ በድንጋይ ጥቃት አደረሰ:: የአውቶቡሶቹን መስታወትም በድንጋይ መሰባበሩ ተሰማ::
አ.አ ወልዲያ በሚጓዝ ሰላም ባስ ና ከአ.አ ወደ መቀሌ በሚጓዝ ስካይ ባስ በመጋቢት 29/08 ተከታትለው ሲጓዙ በነበሩ ሁለቱም ባሶች ላይ በአንድ ለግዜው ማንነቱ ባልታወቀ ግለሰብ ወሎ ሰንበቴ በተባለ አካባቢ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ ጥቃት ያደረሰው ግለሰብ መታሰሩ ተሰምቷል::
የዓይን እማኞች በፎቶ ግራፍ ለዘ-ሐበሻ በላኩት መረጃ መሠረት ስካይ ባስ ከፊት ስለነበረ በሰባት ድንጋይ የግንባር መስተዋቱ ከጥቅም ውጪ ሆኗል።
ከ3,400 በላይ ሼር ሆልደሮች አሉኝ የሚለው ስካይ ባስ በቀጥታ በሕወሓት ሰዎች የሚመራና አብዛኛው ሼርም በነርሱ የተያዘ መሆኑን የቅርብ ሰዎች ይናገራሉ::

No comments:

Post a Comment