Tuesday, March 29, 2016

# By ሳተናው ሰበር ዜና- በታላቋ ትግራይ ከተማ ህወሓቶች አስቸኳይ እና ድብቅ ስብሰባ




ለአማራ ህዝብ ታላቅ የማንቂያ ደውል ተደወለ !!!
Woyaneይህ ትኩስ ዜና በታላቅ አፅንኦት ሊታይ የሚገባው የማንኛውም አገር ወዳድ ዜጋ ጉዳይ ቢሆንም ለአማራው ግን ትልቅ የማንቂያ ደዎል ነውና እንሆ !!! በባለፈው ሀሙስ ማለትም መጋቢት15 /2008 ዓ.ም በታላቋ ትግራይ ከተማ ህወሓቶች አስቸኳይ እና ድብቅ ስብሰባ ያደረጉ ሲሆን ዋናው አጀንዳቸውም በወልቃኢት ፀገዴ የማንነት ጥያቄ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ ለመድፋት ከማሰብ የመነጨ ሲሆን ነገሮች ሁሉ ለአማራ ህዝብ ጭለማ እንዲሆኑ ታስቦ የተጠራ ስብሰባ ነበር፡፡
በመሆኑም በዚህ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ አካላት 300 የተመረጡ የትግራይ ተወላጅ መምህራኖች፣123 የተመረጡ ተማሪዎች፣
ኢንቨስተሮች፣ካድሬዎች፣ሚኒሻዎች፣የተመረጡ የብሄራዊ ወታደሮች ከተለያየ አገሪቷ ዳር ድንበር የተውጣጡ የህውሃት ወሮ በሎች ሲሆኑ ዋናው አጀንዳቸውም የወልቃኢት ፀገዴን የማንነት ጥያቄ ለመቀልበስና ጥላሸት ለመቀባት ታስቦ የተጠራ ነው፡፡
ስብሰባውን ሲመሩ የነበሩ ግለሰቦችም
1ኛ, አቶ ተክለወይኒ
2ኛ,አቶ ዘነበ ሀዱሽ
3ኛ፡የአረና ፓርቲ መሪ አቶ አሰግድ ገ/ስላሴ
4ኛ, አቶ አባይ ወልዱ
5ኛ,ዘፅዓት ትክክለኛ ስሙ ዶ/ር ጎይቶም የማነ ገብረአናንያ የህክምና ዶክተር ሲሆን በአሁን ስዓትም እየሰራበት ያለው አይደር ሪፈራል መቀሌ ጤና ኮሌጅ የሆነ እናም ሶዎስት የቀድሞው የህውሃት መስራች ግለሰቦች ይገኙበታል፡፡
☞የስብሰባው ዋና ጭብጥ ✔
ሁሉም የትግራይ መምህራኖችና ተማሪዎች እንዲሁም በትግራይ ህዝብ ታላቅ ቅቡልነት ያላቸው ምሁራኖች ስለ ቅማንትና ትግራይ ህዝበቦች ያሉ ታሪካዊ እና ማህበራዊ ግንኙነቶች ለትግራይ ህዝብ በሚጠቅም መልኩ አድርገው ፅሁፎችን እንዲፅፉና የወልቃኢት ፀገዴን የማንነት ጥያቄ እንዲዳፈን ለማድረግ ሲሆን ከዚህ በመቀጠልም የአማራና የቅማንት የማንነት ልዩነቶች ተመልሶ ሊጠገን በማይችል መልኩ ከፍተኛ ልዩነቶችን በመፍጠር ሁለቱ አካሎችም ሊፈታ የማይችል ቁርሾ ውስጥ በማስገባ ማጋጨት መቻል የሚሉ ናቸው፡፡ ይህ አጀንጃ በጭራሽ ሊቀለበስ በማይችልበት መልኩ ለሚቀጥሉት 6 (ስድስት) ወሮች ሁሉም የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ምሁራንና ባለሞያዎች እንደየ ሞያቸው ድርሻ ጉዳዩን ወደተግባር እንዲቀይሩ ትላት ማለትም ቅዳሜ ለት ተወስኑዋል፡፡
ወደዚህ ስብሰባ ለመግባት ምንም አይነት ሞባይልም ሆነ መቅረፀ ድምፆች እንዳይገቡ በጥብቅ የተከለከለ ሲሆን የህወሓት ከፍተኛ ባለስልጣኖች ብቻ ይዘው እንዲገቡ ለራሳቸው ፈቅደዋል፡፡
ስብሰባው እስከዛሬ እሁድ 18/7/2008 ዓ.ም የምሳ ስዓት ድረስ የተካሄደ ሲሆን አረናና ህውሃቶች በጥምረት እንዲሰሩ ውሳኔ ተላልፏል፡፡ ሌላው ቀርቶ አቶ አረጋዊ እና አቶ ብስራት አማረ በሚቀጥሉት ሁለት ሳምቶች ውስጥ የስካይፒ (skype ) ስብሰባ እንደሚያካሂዱ ታውቋል የዚህም ዋና የስብሰባ አጀንዳ አማራንና ቅማንትን ከወትሮው በተለየ ሁነኔታ ወደማያባራ ግጭት ውስጥ መክተት ስለማስቻል ሲሆን አቶ አለምነው መኮንን አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ከፍተኛ ጫና በመፍጠር ችልተኛ ሆነው እንዲቀጥሉ ሙሉ አላፊነቱን ለአቶ አለምነው መኮንን ተሰጥቷል፡፡
እንግዲህ ውድ ያገሬ ሰው ሆይ ይሄንን እኩይ ሴራ ከወዲሁ ተረድተህ እራስክን ከጥፋትና ከመከራ ትታደግ ዘንድ የማስጠንቀቂያ ደውል ተደውሎልሃል፡፡
ማሳሰቢያ
———-
ሁሉም አማራ አቀፍ ድርጅቶች በአስቸኳይ ወደ አንድ ጥላ ስር ተሰባስበው በዚህ ጉዳይ ላይ እንዲመክሩ ለማሳሰብ እወዳለሁ፡፡
Ethiopia ለዘላለም በክብር ትኑር።

No comments:

Post a Comment