Monday, March 7, 2016

በመላው ዓለም የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግና የአቤቱታ ፊርማ በአስቸኳይ መሰብሰብ አለበት።

የዲሞክራሲና የነጻነት ሃይሎች በተለይ በማህበራዊ ሚዲያዎች የምትሳተፉ ይህንን የኢትዮጵያውያን ውርደት በዝምታና ከንፈር በመምጠጥ የምናልፈው አይደለም። የህወሀት የፌስቡክ ሰራዊት ይህን ሃጢያታቸውን ለማድበስበስ ፎቶግራፉ የደቡብ ሱዳን ነው የሚል ልፍስፍስ መከራከሪያ እያመጡ ሲያደናቁሩ አብረን በቀደዱት ቦይ መፍሰሳችንን አቁመን ለወገኖቻችን ድምጽ እንሁናቸው። ታዲያ ኢትዮጵያዊነት ምንድን ነው? እንደ ባሪያ አንገታቸው ላይ ገመድ ታስሮ ደም ከአፍና ከአፍንጫቸው እየፈሰሰ እያየን ምን እንጠብቃለን? በመላው ዓለም የሚገኙ የህወሀት ኤምባሲዎች በቁጣ መንቀጥቀጥ አለባቸው። የስኳሩን ፕሮጀክት ጨምሮ ወገኖቻችን ከመሬታቸው እንዲፈናቀሉ በገንዘባቸው እየደገፉ ላሉት ምእራባውያን ቁጣችንን ልንገልጽ ይገባል ። ሰሞኑን በዚህ ላይ ሰፊ ቅስቀሳ ማድረግ ይጠበቅብናል። በየከተሞቹ የምትገኙት የኢትዮጵያ ኮሚኒቶዎች አስቸኳይ ጥሪ አድርጉ። ውርደትን እየለመድነው ከዚህ ግፍ ላይ ደርሰናል።
መሳይ መኮንን

No comments:

Post a Comment