Friday, March 25, 2016

ወያኔን ፕሮፓጋንዳ ፊልም ቦይኮት ያድርጉ! ‪#‎BoycottBezaFilm‬ =========================== ሰላም ወዲ ተስፋይ ( ሄኖክ የሺጥላ )



ስለዚ'ች ልጅ ትንሽ ኣውቃለሁ ። ቤተሰቦቿ የኣዜብ መስፍን የቅርብ ዘመዶች ናቸው ። ራሷ ኣርቲስቷ ኣዜብ መስፍን ተወልዳ ካደገችበት ኣካባቢ ተወልዳ ያደገች ልጅ ነች ። የመለስ ዜናዊ ልጅ (የሰመሃል መለስ ) የቅርብ ጓደኛ ስለመሆኗም ኣውቃለሁ። ራሷም ባንድ ወቅት ስትናገር ሰምቻለሁ ። ምናልባት ኢሉዥን ከሰማሃል መለስ ጋ ጥንብዝ ብለው ሰክረው በወታደር ኦራል ፥ በኣዜብ ጎላ ጋርዶች በሸክም ሲወሰዱም ኣይቻለሁ ። ስለዚህ ይህችን ልጅ ይህንን ፊልም እንድትተውን መምረጣቸው ብዙም ኣይገርምም ።
ስለ ፊልሙ
ወያኔ የጠላውን በዶክመንተሪ የወደደውን በትሪ እየጋበዘ ሲያቀርብልን ኣይተናል ።ያም ሆኖ መጠየቅ ያለብን ኣብይ ጥያቄ ያ «ተራራውን ያንቀጠቀጠው ትውልድ» ዛሬ እንደ ኣዲስ ምን ብቅ ኣደረገው ? የሚለውን ነው። እንደሚመስለኝ ይህንን ፊልም የሰሩት በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት ኣይመስለኝም ፥ ኣይደለም ፊልም እውር ቢያበሩ፥ ሽባ ቢተረትሩ ፥ውሃውን ወይን ፥ ሁለቱን እንጀራ 90 ሚሊዮን መሶብ እንጀራ ቢያደርጉት የሚከተላቸው ፃድቅ ኣይደለም መናፍቅ ኣያገኙም። ይህንን እነሱም ያውቃሉ እኛም እናውቃለን ። ትናንት ኣይደለም ዛሬ እያደረሱ ያለውን ጭካኔ የተሞላበት ኢ ሰብዓዊ እና ዘግናኝ የሆነ የ ጅምላ የዘር ማጥፋት ወንጀልም በዚህ ፊልም ሊቀድሱትም ኣስበው ኣይመስለኝም። ህዝቡ የብሶት ጫፍ ላይ ባለበት ሆኔታ፥ ፍፁም በተጠሉበት እና ብሎም የመውደቂያቸው ዋዜማ በሆነበት ስዓት ግን ይህንን ፊልም ያሰራቸው እንደ እኔ ሁለት ምክንያቶች ይመስሉኛል ። ኣንድኛውን እነሱም ኣያውቁትም ።
ምክንያቶቹ
1ኛ ስለ ጀግንነታቸው እና መስዕዋትነት በማውራት ፥ የህዝቡን ስነ ልቦና ለመስለብ ። 
2ኛ የኣምባ ገነኖች ዘረ መል ( DNA ) መሰላል የተያያዘው በግብዝነት ስለሆነ የግብዝነታቸውም ውጤት ስለሆነ።

ከላይ የጠቀስኩትን እና በተራ ቁጥር 1 ና 2 ላይ ያስቀመጥኩትን ምክንያት እንደ ወያኔ ሁሉ ደርግም ተጠቅሞበታል ። በ 10ኛው የኣብዮት በዓል ላይ ደርግ ( በ ወቅቱ የኣቢዮት ኣደባባይ) እየተባለ በሚጠራው ቦታ ላይ ለኣለም ህዝብ ኣውጥቶ ያሳየው የጦር መሳሪያ እና መሰል ተግባሮች ፥ የደርግን ጥንካሬ ሳይሆን ግብዝነት ያሳየ ስለመሆኑ ለመረዳት 7 ኣመት ነው የወሰደብን ። ይህ በሊቢያም ጋዳፊን ከቤተ መንግስት ኣውጥቶ ጉድጓድ ውስጥ የደበቀው ግብዝነት መገለጫ ባህሪ ነው ፥ ይህ የህወሓት ( ወያኔ) ባህሪ ባይሆን ኖር ምናልባት ያሳስብ ነበር ።
ስለዚህም የዚህ ፊልም በዚህ ሰዓት ተሰርቶ ለህዝብ መቅረብ ዋነኛ ኣላማውም ፥ ህዝብን ለማስፈራራት ፥ ብረት ለበስ ሰውነታቸውን በህዝቡ ህሊና ውስጥ ለመሙላት ነው ። 
ይህ ፊልም ከጀግንነታቸው ይልቅ ስለ እውነት ያስታወሰኝ ነገር ኣንድ ባደኩበት ኣካባቢ ፥ ያረጀ የሰፈር ( የመንደር ) ጉልቤ ያደርግ የነበረውን ነው ። ይህ ጉልቤ ( ጉልበተኛ ለሚለው ኣህፅሮት ነው ) ፥ በጉብዝና ወራቱ የኣካል ብቃቱ እጅግ የሚገርም ፥ ጠንካራ እና ብርቱ የነበረ ሰው ነበር ። ኋላ ላይ ሲያረጅ ፥ በጉልበተኝነቱ ይደመሙ የነበሩ ሰዎችን ኣስማምቶ ጫት ቤት ከፈተ ። በዚያ ጫት ቤት ውስጥ በጉልበተኝነት ዘመኑ ጥርሳቸውን ያረገፋቸውን ሰዎች ሰብስቦ ፥ ግድግዳው ላይ የወጣትነት ዘመን ጡንቻውን የሚያሳይ ፎቶ ለጥፎ ፥ በኮሰመነ እና በመነመነ ተክለሰውነቱ እየፎከረ ሲቅም የሚውል ና በተሸናፊዎች ተከቦ ፥ በዚያች የበሬ ግንባር በምታክል ጫት ቤት ውስጥ « ኣንተ እኮ!» እየተባለ ሲወደስ ና ሲሞገስ የሚኖር ሰው ነበር ። ለኔ ህውሓት ከዚህ ካረጀ ጉልበተኛ በምንም ኣይለይም ። ፊልሙም እንደዚሁ ጉልበተኛ ግድግዳ ላይ የተለጠፈ የጫት ቤት ስዕል እንጂ ሌላ ምንም ሊሆን ኣይችልም ።

እርግጥ ትግላቸውን ያመልኩታል ። እናውቃለን ! መታገል ለመታለል የሆነብን እኛ ግን እነሱም ፥ ቁምጣቸውም ፥ እንደማይረቡ እናውቃለን ! እንደውም እንናገር ከተባለ ወያኔ ኣዲስ ኣበባ ሲገባ ይዞ ከገባው ና ትክክለኛ የራሱ ንብረት እና የማንነታቸው መገለጫ የምንለው እኛ « ቅማላቸውን» ብቻ ነው ። ሌላው በሙሉ የተዘረፈ ነው ። ይህንን ደሞ በፊልም ቀባብቶ ማሳመር የሚቻል ኣይመስለኝም!
ለምሳሌ 
ኣንድ ሰው ዶክተር ስለሆነ ብቻ ህይወቱ እና ማንነቱ ስሙር ነው ማለት ኣይቻለም ። ምክንያቱም በገንዘብ እና ለገንዘብ ሲሉ ውርጃ የሚያካሂዱ ፥ የተበላሸ መድሃኒት የሚያሻሽጡ ፥ የሰውነት ኣካል የሚሰርቁ ፥ መርዝ የሚሰጡ ዶክተሮችን እናውቃለን ። ታጋይ ስለሆነ ብቻ ጀግና ነው ማለትም እንዲሁ ነው ።

ይህንን ፊልም በመናቅ ኢትዮጵያዊነቶን ያሳዩ!

No comments:

Post a Comment