Monday, March 21, 2016

-በደቡብ ኦሞ መሬት የወሰዱት የህወሃት አባላት በአካባቢው ብቅ ብለው እንደማያውቁ ተነገረ



በደቡብ ኦሞ ዞን መሬትና የባንክ ብድር ከወሰዱት ባለሃብቶች መካከል ከ98 በመቶ በላይ የሚሆኑት የህወሃት አባላት መሆናቸውን በሚመለከት ኢሳት ዜና መዘገቡን ተከትሎ፣የደቡብ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ህብረት ሊቀመንበር አቶ ግርማ በቀለ እንደተናገሩት፣ መረጃው ሙሉ በሙሉ ትክክል እንደሆነና ድርጅታቸው በቅርብ የሚያውቀው ጉዳይ መሆኑን ግልጸዋል።መሬቱን የወሰዱት የትግራይ ተወላጅ የህወሃት አባላትና ደጋፊዎች፣ ወደ አካባቢው ብቅ ብለው ታይተው እንደማያውቁ፣ ነገር ግን የባንክና የሌሎችን ብድሮች የሚያገኙት እንሱ በወከሉዋቸው ሰዎች አማካኝነት መሆኑን ገልጸዋል። ከ2006 ዓም ጀምሮ በደቡብ ክልል፣ በደቡብ ኦሞ ዞን 20 ኢንቨስተሮች ያሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ መካከል 16 ቱ ወይም80 በመቶው የህወሃት አባላት ወይም ደጋፊ የትግራይ ተወላጆች ሲሆኑ፣ 4ቱ ወይም 20 በመቶው ብቻ የአካባቢው ተወላጆች ናቸው። በክልሉ ለልማት በሚል ከተከፋፈለው 106 ሺ 997 . 7 ሄክታር መሬት ውስጥ 105 ሺ 914.6 ወይም 98.9 በመቶውን የህወሃት አባላትና ደጋፊ የጥቅም ተጋሪዎች የተቀራመቱት ሲሆን፣ የአካባቢው ተወላጅ ባለሀብቶች 1083 ሄክታር ወይም 1 በመቶ ብቻ የሚሆነውን መሬት ወስደዋል። በዞን ደረጃ ያሉ የኢቨስትመንት ባለስልጣናት ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ ማስፈራሪያ እየደረሳቸው መሆኑን አቶ ግርማ ገልጸዋል። በዞኑ በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ከፍተኛ መሬት የወሰዱት የህወሃት ድርጅቶችና የህወሃት ሸሪኮች ፣ በናጸማይ ወረዳ ኦሞ ሸለቆ አግሮ እንዱስትሪ፣ በኛንጋቶም ወረዳ፣ ሲሳይ ተስፋዬ አግሮ እንዱስትሪ እና ናሩስ ባዮ ቴክኖሎጂ፣ በዳሰነች ወረዳ ሉሲ እርሻ ልማት፣ በሳላመነ ወረዳ ኤኤቲ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እና ጂ ዋይ ቢ ኤስ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ በናማጸይ ወረዳ ሳግላ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ በማሌ ወረዳ ኤን ቲ ኤስ ኢንተርናሽናል ፣ በዳሰነች ወረዳ ዳንኤል ፋሲል፣ በደቡብ አሪ ወረዳ አቶ አማኑኤል ገብረመድህን፣ በሃመር ወረዳ አቶ ረታ ሃይለምርያም፣ በዳሰነች ወረዳ መላ እርሻ ልማት፣ በኛንጋቶም ወረዳ ዶ/ር ጣችመ ሃጎስ፣ በኛንጋቶም ወረዳ አዳማ ዴቨሎፕመንት፣ በሳላማበ ወረዳ ሳትኮን ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል እርሻ ናቸው። በአካባቢው ተወላጆች የተያዙት የእርሻ ድርጅቶች ጂንካ ደንና ቅመማ ቅመም፣ ገበየሁ ምናሉ፣ ተፈሪና ልጆቹ እርሻ ልማት እና ሱዳሜል እርሻ ብቻ ናቸው። ባለሀብቶቹ መሬቱን አስይዘው ብድር ከመውሰድ ውጭ ይህ ነው የሚባል የልማት ስራ አለመስራታቸውንም አቶ ግርማ ገልጸዋል። መረጃውን በተመለከተ የዞኑ አስተዳደር አስተያየቱን እንዲያካፍለን በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ሊሳካልን አልቻለም።
http://amharic.ethsat.com/%

No comments:

Post a Comment