ጊዜው በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት ነበር።ወያኔ የሚይዘው የሚጨብጠው በጠፋበት በዚያ የጭንቅ ቀን ራቁታቸውን ያሰናብውታቸውን የቀድሞወ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ከየቦታው ሲሰበስብ ጨርቅ ብሎ ያዋረደውን ባንዲራ ከተጣለበት ትቢያ አንስቶ በማራገፍ የሀገር ፍቅር ያለው ለመምሰል ሞከረ።የክሱም ሀውልት ለውላይታው ምኑ ነው የተባለው ህዝብም ዛሬ ሀገርህ ተወረረች ደርሰህ ታደራት የሚል ነገሪት ተጎሰመ።ሁሌም ለእስራት እና ለገደያ ለሰደት የሚታጩት የኦሮሞ እና የአማራ ተወላጆችም ሀገራቸውን ይከላከሉ ዘንድ በወጉ ጥሪው ቀረበላቸው።አርቲስቶች እና ታዋቂ ሰዎችም እንዲሁ።እኔም ከመሰራበት መስሪያ ቤት በግዴታ እንደዘምት ትእዛዝ ተላለፈልኝ።ይህን ያስተላለፈው የወረዳው አደረጃጀት ሀላፊ ግን የእርሱ ሀገር እንዳልሆነች ሁሉ እኔ ሂጀ በምሰዋው ህይወት እሱና ህወአት ስልጣን ላይ ለመቆየር ሲመኝ ለመዝመት ግን ፍላጎት የለውም ነበር።በዚህም የተነሳ ግማሽ ቀን የፈጀ ክርክር አድርጌ የማልሄድ ከሆነ ከስራ እንድሰናበት ወሰኑብኝ።እኔ ግን ለጊዜው በእነሱ ውሳኔ ስራየን ከምለቅ እስከመጨረሻው ያለውን ሁኔታ ባሉት መንገድ ተጉዠ መከታተሉን መረጥኩ።ወደ ሁርሶ ማሰልጠኛም ገባሁ።እዚህ ማሰልጠኛ ምንም አይነት አካዳሚያዊ ብቃት የሌላቸው የአንድ ብሄር ሰዎች የተሰበሰቡበት የአሰልጣኝነት ስነምግባር የጎደላቸው ሰዎች መሆናቸውን በነበረኝ ቆይታ ለማረጋገጥ ችያለሁ።
ወደ ማሰልጠኛው ለመሄድ ዋንኛው ምክንያቴ በኔ የህይወት መስዋእትነት መለስ እና ጀሌዎቹን ስልጣን ላይ ለማቆየት አልነበረም።ስራየን ሳላጣ እንዴት መቆየት እችላለሁ የሚለው እንጂ።በዚህ መሰረት ሶስት አመራጭ መንገዶች ተለምኩ።የመጀመሪያው ከስልጠናው ቦታ ለመዝመት ፈቃደኝነት እንደሌለኝ የመጣሁት ተገድጄ መሆኑን በማስረዳት እንዲመልሱኝ እና ወደ ሰራየ እንድመለስ እድል ይኖረኛል ከሚል ነበር።ይህ ሙከራ ሳይሳካ ቀረ።ስልጠናውንም ተከታትየ ጨረስኩ።ቀሪው ምደባ ነው።በምደባም የተሻለ ቦታ ካለ እዚያው እየሰራሁ ወላጆቼን አግዛለሁ የሚል እሳቤ ነበረኝ።ይህ እቅደም አልተሳካም።ቀሪ ሁለት እቅዶች አሉ።በምንም መልኩ ለማላምንበት ጦርነት የህይወት መስዋእትነት መክፈል እንደሌለብኝ ወስኛልሁ።በዚህም መሰረት ከተሳካ ለመንገድ ላይ ለመጥፋት ካልተቻለ ለመማረክ ካልሆነ ደግሞ በሚሰጠኝ መሳሪያ የስርአቱ ታማኝ ወታደራዊ ባለስልጣኖችን አጥፍቼ ለመጥፋት ውጥን ሀሳቤን ይዠ ከአዲስ አበባ ተነስተን ወደ ትግራይ ጉዞ ተጀመረ።እኔም የተሰጠኝን ወታደራዊ ልብስ ቀደም ብየ ውሃ ነከርኩት።በጠዋት ሁሉም ወታደራዊ ልብሱን ለብሶ ወደተመደበበት አውቶቡስ ሲገባ እኔ በውሃ የራሴ ፋቲኬን በኩርቱ ፔስታል ግጥም አደርጌ አስሬ በሲቭል ልብስ ወደአውቶቡሱ ሳመራ በጥያቄ አዋከቡኝ።እኔም አጥቤው ስለነበር እንዳለደረቀልኝ ነገርኳቸው።እነሱ ግን ጥያቄያቸው ሲደጋገም ልብሳችን ሳይሆን ልባችን ነው መመሳሰል ያለበት አልኳቸው።የልብስ መመሳሰል ምንም ጥቅም እንደሌለው ስነግራቸው ተቀበሉት።ጉዞውም ተጀመረ።እኔም በእቅዴ መሰረት ከሚሴ ላይ ለአዳር ከመኪናችን ስንወርድ ጉዞየን ወደ ኮንቦልቻ በሌሊት ብቻየኝ ጀመርኩ።ብዙ ከተጓዝኩ በኋላ አንድ ከአዲስ አበባ የሚመጣ መኪና አስቁሜ ትብብር ጥይቄው ውቧ ኮንቦልቻ አደረሰኝ።ይህ ሰው ምግብ እና ቢራም ግብዞኛል።እድሜህን ያርዝመው።በበነጋታውም በታክሲ ተሳፍሬ ደሴ ገባሁ።ከደሴ ባህርዳር።ደህና ሁኝ ወያኔ ብየ ተለያየን።ይኸው ያኔ የተቀደደው የኔና የወያኔ የጋብቻ ወረቀት እስካሁን ቀጥሏል።ዛሬ በዚያ ሰራዊት ውስጥ ስንት ልብሱ ብቻ የሚመሳሰል ሀሳቡ የተለያየ የሰራዊት አባል ይኖር ይሆን?እስከ መቼ ነው በይሉኝታ ተሸብበን ወገናችንን እየገደልን በኛ ህይወት እነሱ የተንደላቀቁ ህይወት እንዲኖሩ የምንፈቅደላቸው?
No comments:
Post a Comment