በውጭ ሃገር 2 ሥራ ጭምር እየሰራ ያጠራቀመውን ጥሪት አሟጦ በሃገሬ ላይ ሰርቼ እለወጣለው በሚል ሕልም ወደኢትዮጵያ ጠቅልለው የገቡ ዲያስፖራዎች በምሬት ወደመጡበት ሃገር እየተመለሱ መሆኑ ተሰማ::
ዘ-ሐበሻ ያነጋገረቻቸውና ወደኢትዮጵያ ጠቅልለው ገብተው የነበሩ ዲያስፖራዎች በኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሰርቶ መለወጥ የማይታሰብ ነገር ነው ይላሉ::
አቶ በሪሁን ገብሬ የተሰኙና በሰሜን አሜሪካ ለ24 ዓመታት ኖረው በኋላም በሃገሪቱ ውስጥ እድገት አለ የሚለውን ወሬ ሰምተው ወደ ኢትዮጵያ ቤተሰባቸውን ይዘው የገቡት ባለሃብት ከኢትዮጵያ ወደ አሜሪካ ተመልሰው ከመጡ በኋላ ለዘ-ሐበሻ በሰጡት አስተያየት “የውጭ ንግድ ላይ ለመሰማራት ሞክሬ ነበር:: ሆኖም ግን በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት አይቻለልም:: ሌተር ኦፍ ክሬዲት (ኤልሲ) ለማግኘት ከ24 ወራት በላይ ለመጠበቅ ከመቸገሬም በላይ የሚያሰራ ሁኔታ በሃገሪቱ ውስጥ የለም” ብለዋል::
በተለይ በኢትዮጵያ ውስጥ በተፈጠረው የውጭ ምንዛሬ እጥረት ሌተር ኦፍ ክሬዲት (ኤል ሲ) ማግኘት ከተቸገሩ ዲያስፖራዎች መካከል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉና በአሁኑ ወቅት በጅቡቲ ወደብ ያስመጧቸው የኮንስትራክሽን እቃዎች ተይዞባቸው የሚገኙት አንድ ነጋዴ ለዘ-ሐበሻ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ በሰጡት አስተያየት “አሁን ወደ አሜሪካ የመጣሁት ቤተሰቦቼን ለማድረስ ነው:: ኢትዮጵያ ተመልሼ ሄጄ የኮንስራክሽን እቃዎቹን ከሸጥኩ በኋላ እኔም ኑሮዬን እዚሁ አሜሪካ ለማድረግ ወስኛለሁ” ብለውናል:: እንደ እኚሁ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ነጋዴ ገለጻ “በሃገሪቱ ውስጥ በተንሰራፋው የአንድ ቡድን የበላይነት የውጭ ምንዛሬውን እንኳን ለማግኘት የዛ ቡድን አባል መሆን ያስፈልጋል:: እነዚህ የኮንስትራክሽን እቃዎቼ ጅቡቲ ወደብ ከመቀመጣቸውም በላይ እየበሰበሱ ሲሆን በክራይ እና በአንዳንድ ሰበባሰበብ የሚወጣው ገንዘብ የግል ንብረቴን እያራቆተው ይገኛል:: እንደውም ካሁን በኋላ እነዚህን የኮንስትራክሽ እቃዎች ምንዛሬው ተገኝቶ አውጥቼ ብሸጣቸው እንኳ ዋናዬን የማገኝ አመስለኝም” ሲሉ አምርረዋል::
በኢትዮጵያ ውስጥ የውጭ ምንዛሬው እጥረት በውጭ ንግድ ዘርፍ የተሰማሩ ነጋዴዎችን እጅጉን እያከሰራቸው እንደሚገኙ የሚገልጹት ሌላዋ ዲያስፖራ ወይዘሮ እሌኒ ማንያህልሃል “ከ4 ዓመት በፊት ነበር ኢትዮጵያ ጠቅልዬ የገባሁት:: በኪሳራ ምንክያት ወደመጣሁበት አሜሪካ ለመመለስ ተገድጃለሁ” ብለውናል::
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የዲያስፖራ ነጋዴዎች ስም የወጣላቸው ሲሆን “ፎር ጉድ” ብለው ወደ ሃገር ቤት የገቡ ወገኖች “ወይጉድ” እያሉ እየተመለሱ ነው እየተባለም ይhttp://www.zehabesha.com/amharic/archives/51603ቀለድባቸዋል::
No comments:
Post a Comment